ከትናንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ፌስቡክ፣ ሜሴንጀር፣ ኢንስታግራም እና የተወሰኑ የዋትስአፕ እና ቴሌግራም መገናኛ ዘዴዎች እንደማይሰሩ የሀገራትን ኢንተርኔት የሚከታተለው ኔትብሎክስ የተሰኘው ድርጅት…

ከትናንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ፌስቡክ፣ ሜሴንጀር፣ ኢንስታግራም እና የተወሰኑ የዋትስአፕ እና ቴሌግራም መገናኛ ዘዴዎች እንደማይሰሩ የሀገራትን ኢንተርኔት የሚከታተለው ኔትብሎክስ የተሰኘው ድርጅት ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎቹ አገልግሎት ያቋረጠው፣ ትናንት የተጀመረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ወረቀት ተሰርቋል የሚሉ መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ እንደሆነ ድርጅቱ ገልጧል። መንግሥት ግን ፈተናው ተሰርቆ ወጥቷል መባሉን አስተባብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply