
በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ውስጥ ጉልህ ሚና የነበራቸው የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል መውጣትን በተመለከተ አስካሁን እርስ በእርሱ የሚቃረን መረጃ እየወጣ ነው። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንን ባለፈው አርብ ጥር 19/2015 ዓ.ም. በትግራይ ውስጥ ከፌደራሉ ጦር ውጪ በትግራይ ክልል ውስጥ ሌላ ኃይል የለም ያሉ ሲሆን፣ አንዲት የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት ግን የኤርትራ ሠራዊት አሁንም ትግራይ ውስጥ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።
Source: Link to the Post