ከትግራይ አማፂ የሽብር ቡድን ጥቃት የተረፉ ተጎጅዎች የሽብር ቡድኑ የቡድን አስገድዶ መድፈር ዘረፋ እና አካላዊ ጥቃት እንደፈጸመባቸው ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተናገሩ! የአማራ ሚዲያ ማእከል…

ከትግራይ አማፂ የሽብር ቡድን ጥቃት የተረፉ ተጎጅዎች የሽብር ቡድኑ የቡድን አስገድዶ መድፈር ዘረፋ እና አካላዊ ጥቃት እንደፈጸመባቸው ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተናገሩ! የአማራ ሚዲያ ማእከል ሕዳር 1 2014 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በአማራ ክልል ጋይንት ንፋስ መውጫ የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ ያወጣው ሙሉ ዘገባ! *ሴቶች መሳሪያ ተደግኖባቸው ተደፍረዋል : ተዘርፈዋል: ፃታዊና አካላዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል *የህክምና ጣቢያዎች በመዘረፋቸው የህክምና አገልግሎት ተቋርጧል! በነሀሴ አጋማሽ 16 የነፋስ መውጫ ነዋሪ ሴቶች ራሱን የትግራይ ሰራዊት ብሎ በሚጠራው የሽብር ቡድን የቡድን አስገድዶ መድፈር እንደተፈፀመባቸው ለአምነስቲ መናገራቸውን በዘገባው አጋልጧል:: ከሞት ያመለጡ ተጎጅዎች እንደተናገሩት ወራሪው ሀይል መሳሪያ በመደገን አስገድዶ እንደደፈራቸው : እንደዘረፋቸው እና አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጥቃት እንደፈፀመባቸው ተናግረዋል:: የነፋስ መውጫን የጤና ኬላዎችን ማውደሙን ና መዝረፉን በዚህም ምክንያት ህክምና እንዳላገኙም ገልፀዋል:: ከ16 ሴቶች 14ቱ በቡድን አስገድዶ መድፈር ተፈፅሞባቸዋል:: የትግራይ ወራሪ ሀይል አማራ ጋይንት ነፋስ መውጫን ለ9 ቀን የወረረ ሲሆን በቆየባቸው ቀናት 70 ሴቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው የአካባቢው ባለስልጣናት ለአምነስቲ ገልፀዋል: ወራሪው የሽብር ቡድን የጦር ወንጀል የፈፀመ ሲሆን በሰብአዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጀል : አውሬያዊና ፍፁም ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ተፈፅሟል ሲሉ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሴክረተሪ ጄኔራል ካላማርድ ተናግረዋል:: አምነስቲ 16 አስገድዶ መድፈር የተፈፀመባቸውን ሴቶች በቪዲዮ በተደገፈ ማስረጃ በመያዝ አናግሯል:; በተጨማሪም የንፋስ መውጫ ሆስፒታል ሀላፊ: እንዲሁም የአካባቢው እና የዞን ሀላፊዎችን አናግሯል:: የንፋስ መውጫ የወጣቶች ሴቶች እና ህፃናት ሚኒስቴር የተደፈሩት ሴቶች 70 መሆናቸዉን ሲገልፅ የፌደራል ፍትህ ሚንስትር በበኩል የተደፈሩ ሴቶች 73 እንደሆኑ ይፋ አድርጏል:: ከጥቃቱ የተረፉ ተጎጅዎች ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደነገሩት የትግራይ ወራሪ ሀይል ነሀሴ 3 ቀን ከተማውን እንደተቆጣጠሩ ውድመት ጥቃት እና ዘረፋ መፈፀም መጀመራቸውን ነግረውታል::ፆታዊ ጥቃት ሲፈፅሙ በአማራነታቸውን በመስደብ እና ራሳቸውን እኛ የትህነግ ሰራዊት ነን እያሉ በመግለፅ ጭምር እንደሆነ ተናግረዋል:: በእምነት የተባሉ የ45 አመት የነፋስ መውጫ ነዋሪ እንደገለፁት ነሀሴ 5 ቀን 2013 አም የትግራይ ሽብር ቡድን ታጣቂዎች ወደቤታቸው በመምጣት ቡና እንዲያፈሉ መጠየቃቸውንና ቀጥሎም ለ 3 እንደደፈሯቸው ተናግረዋል:: “ሁኔታዎች ስለገባኝ ሴት ልጄን ከቤት አስወጥቼ ሰደድኳት: ወታደሩ እንዳመጣት ቢጠይቀምኝ መምጣት እንደማትፈልግ ነገርኩት:: እኔን መስድብ ጀመረ:: አማራ አህያ* ነው : አማራ ጥቅም የለውም እያለ መስደብ ጀመረ:: አብረው ከነበሩት አንደኛው እናታችን ትሆናለች መስደብ የለብንም መጉዳት የለብንም ቢላቸውም እሱን አባረው እኔን ለ3 ደፈሩኝ” ማለታቸውን አምነስቲ በዘገባው ይፋ አድርጓል። ገበያነሽ የ30 አመት ወጣት ስትሆን በንፋስ መውጫ ምግብ በመሸጥ ትተዳደራለች:: “ያደረጉብኝን መናገር ከባድ ነው:: ደፈሩኝ:: ልጆቼ እያለቀሱ ለ3 ደፈሩኝ:: ትልቁ 10 ትንሹ 9 አመታቸው ነው:: የትግራይ ወራሪ ሀይሎች ሲደፍሩኝ እያለቀሱ ነበር::ከደፈሩኝ በሗላ ጥለውኝ ሄዱ:: ከመድፈር በተጨማሪ አካላዊ ጥቃት ድብደባ እና ሽሮ እና በርበሬ ሰርቀው ወስደዋል:: በጥፊ እና በእርግጫ መተውኛል:: ” ሀመልማል የ28 አመት ወጣት ስትሆን እንጀራ በመሸጥ ትተዳደራለች:: ነሀሴ 7 ቀን 4 የትግራይ ወራሪ ሀይል ወታደሮች በመኖሪያ ቤቷ በልጆቿ ፊት ለ4 እንደደፈሯት ለአምነስቲ ተናግራለች:: “የ10 እና የ2 አመት ህፃን ልጆች አሉኝ:: ልጆቼን እንዳይገድሉብኝ ፈርቼ ነበር:: ልጆቼን አትግደሉብኝ የፈለጋችሁትን አድርጉ እያልኩ ለመንኳቸው:: ትንሹ ተኝቶ ነበር:: ትልቋ ግን ነቅታ እያየች ነበር:: ያየችውን የመናገር አቅም የለኝም:: ” የትግራይ ወራሪ ሀይሎች አማራነትን መሰረት ያደረገ ስድብ እና ዘለፋ ፈፅመዋል:: አንዳንድ የትግራይ ወራሪ ሀይል ወታደሮች የፌደራል መንግስት የትግራይ ሴቶች ላይ ላደረሰባቸው መድፈር የአማራን ሴት በመድፈር እየተበቀሉ መሆናቸውን የነገሯቸው እንደገለፁ የንፋስ መውጫ ነዋሪዎች ለአምነስቲ ገልፀዋል:: ሀመልማል በ4 የትግራይ ወራሪ ቡድን ወንዶች የተደፈረች ሲሆን መጀመሪያ የደፈራት የቡድኑ መሪ ሲሆን አማራ አ*ያ ነው: አማራ ገብጋ* ነው:: አማራ ትግሬን ገድሏል* መከላከያ ሚስቴን ደፍሯል:: አሁን እኛ እንደፈለግን እንደፍርሻለን እንዳላት ገልፆለች:: መስከረም የተባለችው ወጣት ለ3 ሲደፍሯት “አማራ አ*ያ ነው:: ጠንካራ ናችሁ:: ከዚህም በላይ መሸከም ትችላለችሁ:: እያሉ እየደበደቡ ለ3 ተፈራርቀው እንደደፈሯት ገልፃለች:: የትግራይ ወራሪ ሀይሎች በመድፈር ብቻ አልተገቱም :: የደፈሯቸውን ሴቶች ዘርፈዋል:: አብዛኞቹ ሴቶች ከእጅ ወደአፍ የሆነ ኑሮ የሚኖሩ: ትንንሽ ስራዎችን እየሰሩ ልጆች የሚያሳድጉ እና በድህነት ውስጥ ያሉ ናቸው:: መስከረም ምግብ በመሸጥ ትተዳደራለች:: 4 ወንዶች መጥተው ቤት ውስጥ ያለውን በሙሉ በሉ :ጠጡ:: ሁለቱ ደፈሩኝ:: የአንገትና የእጅ ጌጤንም ወሰዱ ስትል ለአምነስቲ ገልፃለች:: ፍሬህይወት በተደጋጋሚ ግዜ በትግራይ ወራሪ ሀይሎች የተደፈረች ሲሆን ስልክ እና ገንዘብኝ ተዘርፋለች:: ትእግስት የተባለች ሴት እንደገለፀች ደግሞ ነህሴ 4 ቀን ተደፍራ ሱቋም ተዘርፏል:: ወድሟል: ጌጣጌጥ ተወስዶባታል:: ” ንብረቴን ወሰዱት : 4 ካሳ ቢራ ጠጥተው ጠርሙሱን ሰበሩት:: 2 የለስላሳ ካሳ እና የወርቅ ሀብሌን ወሰዱብኝ:: ያለኝን በሙሉ አጥቻለሁ:: መስራት አልችልም: ወድሞብኛል” ከ16 ጥቃት ከደረሰባቸው ሴቶች 15 የሚሆኑት አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል:: በመደፍራቸው ምክንያት ፌስቱላ: የጀርባ ህመም: መንቀሳቀስ አለመቻል እና ድብርት ውሥጥ ገብተዋል የትግራይ ወራሪ ቡድኑ የንፋስ መውጫን የጤና ተቋማት በመዝረፍ እና በማውደሙ የተደፈሩ ሴቶች ምንም አይነት ህክምና እንዳያገኙ ሆነዋል:: የድንገተኛ የወሊድ መቆጣጠሪያ: የኤችአይቭ :በወሲብ የሚተላለፉ በሽታዎች መዳኒት: የማህፀን ህክምና የአእምሮ ህክምና አላገኙም:: አንድ የኤንጅኦ ሀላፊ ለአምነስቲ እንደገለፀው በእነዚህ የጤና አገልግሎት ላይ ቢሰማሩም መንግስት ኤንጅኦች ላይ በጣለው ማእቀብ ምክንያት መስራት እንዳልቻሉ ተናግረዋል:: በእምነት በደረሰባት ጥቃት ምክንያት የጀርባ ህመም እና በመደፈሯ ምክንያት የደረሰ ተያያዥ ህመም እየተሰቃየች ነው:: ሰላማዊት የ20 አመት ወጣት እና የቤት ሰራተኛ ስትሆን በ3 የትግራይ ወራሪ ሀይሎች በመደፈሯ አርግዛለች:: ምንም አይነት የህክምና አገልግሎት አላገኘችም: የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሀላፊ ካላማራድ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ በአስቸኳይ የህክምና እና የስነልቦና ድጋፍ አገልግሎት ማመቻቸት እንዳለበት አሳስበዋል:: የደረሱ ጥቃቶችን በተመለከተ ጥናት ማድረግ እንዳለበትም ገልፀዋል: ተጎጅዎች ፍትህ እንዲያገኙ መስራት እንዳለበት ገልፀዋል::

Source: Link to the Post

Leave a Reply