ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ ከተማ በሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ላይ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት አንድ ሾፌር ሲገደል የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 8 ቀን 201…

ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ ከተማ በሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ላይ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት አንድ ሾፌር ሲገደል የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 8 ቀን 201…

ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ ከተማ በሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ላይ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት አንድ ሾፌር ሲገደል የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 8 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ ከተማ ዛሬ ጥር 8 ቀን 2013 ዓ.ም ሲጓዙ በነበሩ አንድ ሲኖትራክ እና ተሳቢ ላይ የጉምዝ ታጣቂዎች ጥቃት ፈፅመዋል። በጦር መሳሪያ የታገዘ ጥቃቱን የፈፀሙት ተሽከርካሪዎቹ ማንዱራ ወረዳ ኤዲዳ በተባለ አካባቢ እንደደረሱ ከረፋዱ 4:30 ሰዓት ላይ ነው። የተሳቢው ሾፌር ሲገድል፣ ረዳቱ እና የሲኖ ትራኩ አሽከርካሪም መቁሰላቸው ተነግሯል። ይህን አሰቃቂ ጭፍጨፋ እየፈፀሙ ያሉ አካላት እነማን እንደሆኑ ይታወቃል ያሉት ምንጫችን በተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ሲፈፅሙ ከአሁኑ ጋር ለአራተኛ ጊዜ መሆኑን ገልፀዋል። ኤዲዳ ወይም ቁጥር 2 ለግልገል በለስ ከተማ በጣም ቅርብ መሆኗን ገልፀው አሰቃቂ ጥቃት ፈጻሚዎች ጉዳቱን አድርሰው የሚገቡበት የቀርቀሃ ጫካ የት እንደሆነም ይታወቃል ነው ያሉት። እነዚህን የጭካኔ ወንጀል እየፈፀሙ ያሉ ጨፍጫፊዎችን ለመያዝ አምስት ሰው ይበቃል ያሉት ነዋሪው መንግስት ስለምን በህግ ቁጥጥር ማዋል እንዳልፈለገ አልገባኝም ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply