#ከነቀምቴ እስከ አንገር ጉትን ባሉ መስመሮች የስራ ማቆም አድማ ተጀመረ! ከምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና መቀመጫ ከሆነችው የነቀምቴ ከተማ ጀምሮ እስከ አንገር ጉትን ከተማ ባለው መንገድ…

#ከነቀምቴ እስከ አንገር ጉትን ባሉ መስመሮች የስራ ማቆም አድማ ተጀመረ! ከምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና መቀመጫ ከሆነችው የነቀምቴ ከተማ ጀምሮ እስከ አንገር ጉትን ከተማ ባለው መንገድ ላይ እየተፈጸመ በሚገኘው እገታ፣ ዝርፊያ እና ግድያ የተነሳ የትራንስፖርት ሰጭ አካላት በሙሉ የስራ ማቆም አድማ አደረጉ። ከነቀምቴ ጉትን መስመር መኪናዎች ስራ የማቆም አድማ ለማድረግ የተገደዱበት ዋነኛ ምክንያት የተባለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በመነሳቱና መሰመሩ በሸኔዎች ቁጥጥር በመሆኑ ነው፤ ሲሉ በምሬት ለአጉልዞ ጥያቄ ገልፀዋል።… ይህ በንዴህ እንደለ በተሽከርካሪዎች የሚፈጸመው ** አፈና ** ዘረፋ እና ** ግድያ ሰለበዛባቸው ነው ሲሉ በትራንስፖርት እጦት በነቀምቴ ከተማ መነሐሪያ ውስጥ የሚጉላሉ የአንገር ጉትንና የዙሪያዋ የአከባቢው የኦሮሞ ተወላጆች ለአጉልዞ ጥያቄ ገልጸዋል። በመጨረሻም በአንገር ጉትን ከተማና በዙሪያው የሚገኙ የየትኛውም የማህበረሰብ ክፍሎች በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከመንቀሳቀስ ተቆጥበው ለተሻለ ነገ ለአንድነት መስራትና የጋራ ጥላታችን የሆነውን በጋራ ልንታገለው ይገባል ሲሉ ለህዝቡ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። © አጉልዞ ጥያቄ ሰ.ሜሪካ :- ነሀሴ 03/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply