You are currently viewing ከነቀምት ወደ ኪረሞ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል መግባቱ ለከፍተኛ ጭንቀት የዳረጋቸው መሆኑን የሀሮ አዲስ ዓለም ነዋሪዎች ተናገሩ፤ አስፈላጊው ጥንቃቄ ሁሉ እንዲደረግም ጥሪ ቀርቧ…

ከነቀምት ወደ ኪረሞ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል መግባቱ ለከፍተኛ ጭንቀት የዳረጋቸው መሆኑን የሀሮ አዲስ ዓለም ነዋሪዎች ተናገሩ፤ አስፈላጊው ጥንቃቄ ሁሉ እንዲደረግም ጥሪ ቀርቧ…

ከነቀምት ወደ ኪረሞ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል መግባቱ ለከፍተኛ ጭንቀት የዳረጋቸው መሆኑን የሀሮ አዲስ ዓለም ነዋሪዎች ተናገሩ፤ አስፈላጊው ጥንቃቄ ሁሉ እንዲደረግም ጥሪ ቀርቧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 28 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከሰሞኑ ከነቀምት ወደ ኪረሞ ወረዳ የገባው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በሀሮ አዲስ ዓለም አማራዎች ላይ ተጨማሪ የወረራ ጥቃት ሊፈጽም ዝግጅት እያደረገ ስለመሆኑ ማሳያ ነው የሚሉት በከፍተኛ ጭንቀት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። የዐይን እማኞች እንደሚሉት ታህሳስ 26/2015 አመሻሹን 18 መኪና የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከነቀምት አንገር ጉትን ከዛም ወደ ኪረሞ ከተማ ገብቷል። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ህዳር 9፣10፣10 እና 20/2015 በምስራቅ ወለጋ ዞን የኪረሞ ከተማን ማውደማቸው ይታወሳል፤ የአማራ ቤቶችንም እየለዩ አውድመዋል። ከኪረሞ በ8 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኘው በሀሮ አዲስ ዓለም ቀበሌም ህዳር 21/2015 እና ታህሳስ 14/2015 ይህ የኦሮሚያ መንግስት መር ኃይል በቡድን መሳሪያ ታግዞ በከፈተው ጦርነት በርካታ አማራዎች ተገድለዋል፤ ብዙዎችም ቆስለው በህክምና እጦት ህይወታቸው አልፏል። በሀሮ አዲስ ዓለም ከነዋሪዎች ውጭ ከአንድ መቶ ሽህ በላይ ማንነታቸው እንደ ወንጀል ተቆጥሮ የተፈናቀሉ አማራዎች ብቻ እንዳሉበት ይታወቃል። ይህ ወደ ኪረሞ የገባው በብዙ ሽህ የሚቆጠር የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በሀሮ አዲስ ዓለም ላይ በዓልን አስታኮ በመግባት ዳግማዊ የወረራ ጥቃት ለመፈጸም በዝግጅት ላይ በመሆኑ እባካችሁ መከላከያ በአስቸኳይ ገብቶ ህዝቡን እንዲታደግ ይሁን የሚል ጥሪ ቀርቧል። በተጨማሪም ህዝቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ እንዲደረግም ጥሪ ቀርቧል። አሁን ላይ ለከፍተኛ ጭንቀት መዳረጋቸውን የሚገልጹት አማራዎች ከ87 በላይ ተሽከርካሪ ሙሉ የሀሮ አዲስ ዓለምን ንብረትን ከሰሞኑ ጭነው ወደ ነቀምት ወስደዋል፤ ቀደም ሲልም ከ79 ተሽከርካሪ በላይ ንብረት በልዩ ኃይሉ ተዘርፎ ወደ ነቀምት ተወስዷል ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply