ከነገ ጀምሮ ለአንድ ወር ወደ አንድነት ፓርክ የሚወስደው መንገድ በግንባታ ምክንያት ይዘጋል ተባለ፡፡በታላቁ ቤተመንግስት ወደ አንድነት ፓርክ የሚወስደው መንገድ ግንባታ ሰለሚጀመር አሽከርካ…

https://cdn4.telesco.pe/file/AcL0rkmhhpW8fpH_x2YcjS9HMU00ffmOzcZHokh-lqwDDocqvITAgSV71q-QYduMfsRqN2aqZ62QBDR-TddAwicpZuJm4MMvO6S8vsofN1m-x7VH9iYQ50E5bujo7mESl1JQwoXELG7PexB7Te1eGd1fRGigXMLNm2_Z4-1h4hMLuI6p8ueJCqf_10mY8zwf4oaR72Pl8qrvfxUlnwncEu4f5LUOGQ622cX-dtUffMJFf2uZWiEuaE4tFJWK7hRwP0tZNv93FgzGEX9vEImrmKb6Zut5Cdh3BoAw27QvFsc2e2FNjxKqtXQLPqK-lUqdxU0GmFjlLWcJS-uqKiVY0g.jpg

ከነገ ጀምሮ ለአንድ ወር ወደ አንድነት ፓርክ የሚወስደው መንገድ በግንባታ ምክንያት ይዘጋል ተባለ፡፡

በታላቁ ቤተመንግስት ወደ አንድነት ፓርክ የሚወስደው መንገድ ግንባታ ሰለሚጀመር አሽከርካሪዎች አመራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የታላቁ ቤተመንግስት አንድነት ፓርክን ያለ ትራፊክ መጨናነቅ መጎብኘት የሚያስችል የውስጥ ለውስጥ ዋሻ ግንባታ ምክኒያት ከነገ ህዳር08/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የተወሰኑ መንገዶችን ዝግ እንደሚሆኑ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

ለዚሁ ስራ ሲባል ለአንድ ወር የሚቆይ የተወሰኑ መንገዶችን የሚዘጉ ሲሆን ከሂልተን ሆቴል ተነስቶ ወደ ቀኝ የሚታጠፉ ተሸከርካሪዎች እና ከካሳንችስ ወደ 4 ኪሎ የሚያስወጣው መንገድ ከነገ ህዳር08/2013 ዓ.ም ጀምሮ የሚዘጋ በመሆኑ አሽከርካሪዎችም ኢንተርኮንትኔታል ሆቴል በንግድ ሚንስቴር በሂልተን ሆቴል ወደ 4 ኪሎ እና ከካሳንቺስ መለስ አካዳሚ ሴቶች አደባባይ አቧሬ አድርገው ወደ 4 ኪሎ መውጣት እንደሚችሉ ኤጀንሲው ገልጿል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply