ከናዝሬት በቅርብ ርቀት ጮሬ በተባለ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ አሸባሪ ኦነጋዊያን በ3 አማራዎች ላይ እገታ ሲፈጽሙ አንደኛውን በጥይት ቀጥቅጠው ገደሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 23 ቀ…

ከናዝሬት በቅርብ ርቀት ጮሬ በተባለ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ አሸባሪ ኦነጋዊያን በ3 አማራዎች ላይ እገታ ሲፈጽሙ አንደኛውን በጥይት ቀጥቅጠው ገደሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 23 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ሸዋ ዞን ከናዝሬት በቅርብ ርቀት በምትገኘው ጮሬ በተባለች አካባቢ ነዋሪ የሆነው ደረጀ በላይነህ ገብረ ዮሃንስ በመኖሪያ ቤቱ በተኛበት በአሸባሪ ኦነጋዊያን ከበባ ተደርጎ በ30 ጥይት ቀጥቅጠው በግፍ የገደሉት ስለመሆኑ ቤተሰቦቹ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል። አሳዛኝ ግድያው የተፈጸመውም መጋቢት 18/2015 ከሌሊቱ 5 ሰዓት ላይ መሆኑ ታውቋል። በአልሞትባይ ተጋዳይነት ወቅትም አቶ ደረጀ በላይነህ አሰቃቂ ግድያ ከፈጸሙት መካከል አንዱን ይዞ መውደቁ ወይም መግደሉ ተሰምቷል። ሟች አቶ ደረጀ በላይነህ ገብረ ዮሃንስ ዕድሜው 36 ዓመት ሲሆን የ3 እና የ11 ዓመት ልጆች አባት መሆኑ ተገልጧል። ስርዓተ ቀብሩም በእለተ ማክሰኞ መጋቢት 19/2015 ተፈጽሟል። በጮሬ አካባቢ ከ5 ቀናት በፊት በተመሳሳይ ሌሎች 3 አማራዎችዎ በመኖሪያ ቤታቸው እያሉ መዋቅራዊ ድጋፍ ባላቸው በእነዚህ አሸባሪ ኦነጎች ታግተው ወደ ጫካ መወሰዳቸው እና ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አድራሻቸው አልታወቀም ሲሉ ነዋሪዎች ለአሚማ ተናግረዋል። ከተደራጁ ነፍሰ ገዳዮች መካከልም አንዱን ይዞ መውደቁ ወይም አንዱን መግደሉ ታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply