You are currently viewing ከአማራ ህብረት ሙኒክ/ ባቫሪያ/ጀርመን የተሰጠ የአቋም መግለጫ ! ስሆክሆልም :- ሐምሌ 27/2014 ዓ.ም           አሻራ ሚዲያ የአማራን ህልውና መታደግ የኢትዮጵያን…

ከአማራ ህብረት ሙኒክ/ ባቫሪያ/ጀርመን የተሰጠ የአቋም መግለጫ ! ስሆክሆልም :- ሐምሌ 27/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የአማራን ህልውና መታደግ የኢትዮጵያን…

ከአማራ ህብረት ሙኒክ/ ባቫሪያ/ጀርመን የተሰጠ የአቋም መግለጫ ! ስሆክሆልም :- ሐምሌ 27/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የአማራን ህልውና መታደግ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት መታደግ ነው! ለአገር ህልውና ዋጋ የከፈለ ፣ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ተሰባጥሮ የሚኖር ፣ በሌሎች ህዝቦች ጥቃት የሚታመም ፣ የትልልቅ እሴቶች ባለቤት የሆነው የአማራ ህዝብ ዛሬ ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበት ፣ ወንጀሉ በህግ የማያስጠይቅ፣ ሞቱ እውቅና የማይሰጥበት፣ ሃዘኑንም ሞቱንም መግለጽ የማይችልበት ፣ አልፎ ተርፎ እንወክለዋለን የሚሉ ፖለቲከኞች በሞቱ የሚሳለቁበትና የሚያዋርዱት ግዜ ላይ ደርሷል ። “በመንግስት መዋቅር ድጋፍ የሚደረግ ግድያና ጭፍጨፋን እንደ ቁማር ጨዋታ የቆጠሩ ፖለቲከኞች ፣ በዜግነት እንኑር ስትላቸው ኢትዮጵያ በብሄር ብሄረሰቦች ነው የተሰራችው ፣ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት ለመደፍጠጥ ነው እንዲህ የምትለው ይሉሃል ። ሞተህ ግን ፣ በማንነት የተገደለው አማራ ነው ስትል ዜጎች ናቸው የሞቱት ብለው ይሳለቁብሃል።” በዚህ መንገድ አማራው ማህበራዊ እረፍት እንዳያገኝና ለከፋ ድህነት እንዲጋለጥ እየተደረገ ስለሆነ ፣ እንደ ማህበረሰብ የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ፣ በአማራ ላይ የሚፈጸመውን ዘግናኝ የዘር ፍጅት ፣ (Genocide) የዘር ማጽዳት (Ethnic cleansing) ወንጀልና ማንነትን መሰረት ያደረገ ዘርፈ ብዙ የመብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ለማድረግ ፣ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሳወቅ ድምጽ ለመሆን ፣ ስጋት ላለባቸው ወገኖቻችን ልሳን ለመሆን ፣ ከሞት ለተረፉ ሰለባዎች እርዳታ ለማድረግና የህልውና ትግሉን ለማገዝ እንዲሁም ከሌሎች መሰል የአማራ ማህበራት ጋር በመቀናጀት እገዛ ለማድረግ፣ እኛ በሙኒክና አካባቢው ( ባቫሪያ -ጀርመን) የምንኖር ትውልደ ኢትዮጵያዊ አማራዎች፣ ይህንን የአማራ ህብረት በዛሬው ዕለተ ቅዳሜ ሐምሌ 30.2022 (እ.አ.አ) መስርተናል ። በዚህ የምስረታ ጉባዔያችን ዕለት መስራች አባላት ወቅታዊ የአገራችን ሁኔታ ላይ በሰፊው በመወያየት የሚከተለውን የአቋም መግለጫም አስተላልፏል ። 1ኛ. ከ30 ዓመት በላይ ያስቆጠረው በመላው ኢትዮጵያ በአማራ ላይ ሲፈፀም የኖረውንና አሁንም የቀጠለውን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ተግባር መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ ወንጀሉን በስሙ በመጥራት የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤ በገለልተኛ አጣሪ ኮሚቴ ተጣርቶ ጭፍጨፋውን ፈጻሚና አስፈጻሚዎች ለፍርድ እንዲቁርቡ እንጠይቃለን። ብሄራዊ የሀዘን ቀን ታውጆ በመላው ኢትዮጵያ ህዝቡ ሀዘኑን በይፋ እንዲገልጽ ፣ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብና ወንጀሉ በተፈጸመባቸው ቦታዎች የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሚዲያ ባለሞያዎች ፣ እንዲሁም የሰባዊ መብት ተቋማት በተገኙበት ፣ በየቦታው ወዳድቀው የቀሩ ከአውሬ የተረፉ አጽሞች ተሰብስበው በክብር እንዲያርፉና የጅምላ መቃብር ቦታዎች ተለይተው እና ታውቀው፣ መታሰቢያ ሃውልት እንዲቆምላቸው እንጠይቃለን። 2ኛ. ለረዥም ግዜ ከአማራው ፊቱን አዙሮ የነበረው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የአማራው ሰቆቃ እንዳሳሰበውና የዘር ፍጅቱ በገለልተኛ አካል እንዲመረመር መጠየቅ መጀመሩን የሚያመላክቱ ሁኔታዎች አስተውለናል ። ቢዘገይም ጅማሮውን እያደነቅን መሬት ላይ የወረደ ስራ ያልተጀመረ በመሆኑ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመሰጠት የዘር ማጥፋቱ አድማስ ከመስፋቱ በፊት ለማስቆም ያላሰለስ ጥረት እንዲያደርግ እንጠይቃለን። 3ኛ. በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ ለተፈጸመው የዘር ፍጅት የኦሮሚያ፣የቢኒሻንጉል ክልሎች እና የፌደራል መንግስቱ ሀላፊነት በመውሰድ ለተጎጂ ቤተሰቦች ከሳ ፣ ለተፈናቃዮች የህግ ከለላ እና የስነልቦና ህክምና እንዲያገኙ በማድረግ በአስቸኳይ የመልሶ ማቋቋም ስራ ተስርቶ እንዲመለሱ እንዲደረግና ይህን መሰል ችግር ዳግም እንዳይከሰት መዋቅራዊ ማስተካከያ እንዲደረግ እንጠይቃለን። 4ኛ. አማራ ጠል የሆነው ህገ መንግሥትና እሱን መሰረት አድርጎ የተቋቋመው ህዝብ አጫራሽ የሆነው የጎሳ ፌደራሊዝም ተወግዶ ህዝብ የተወያየበትና ያመነበት ህገመንግስት እና አስተዳደራዊ መዋቅር እንዲመሰረት እንጠይቃለን። 5ኛ. አማራ ከሚባለው ክልል ውጭ የሚገኘው የአማራ ተወላጅ ፍታዊና አካታች የሆነ ሕገ መንግሥት እስከሚኖር ድረስ ባለው ህገ መንግሥት መሰረት የፖለቲካ ውክልና ኖሮት መብቱን ህጋዊ በሆነ መንገድ የሚያስከብርብት እኩል መደላድል እንዲፈጥር ፤ የፌደራሉም ሆነ የክልል መንግሥታት ተቀዳሚ ተግባራቸው ሰላምና ጸጥታ ማስፈን በመሆኑ ዜጎች የፈለጉበት ቦታ የመስራትና የመኖር መብታቸው እንዲጠበቅ የመድረግ ኃላፊነትና ጊዴታ አለባቸው ። 6ኛ. የትግራይ ወራሪ ሀይል በፈጸመው ወረራ የወደሙ ከተሞች፣መሰረተ ልማቶች መልሶ ግንባታ በበቂ ሁኔታ እየተሰራ እንዳልሆነ እንረዳለን ። የፌደራል መንግስቱ ከለጋሽ ሃገሮችና ድርጅቶች ጋር በመተባበር ክልሉ ከደረሰበት የኢኮኖሚ ድቀት እንዲያገግምና አፋጣኝ የመልሶ ግንባታ ስራ እንዲሰራ እንጠይቃለን። 7ኛ. ፋኖነት ለአማራ ህዝብ ደምና አጥንት የተገበረለት የአባቶቻችን ዉርስ፣ ዛሬም ያለ ወደፊትም ከአማራ ህዝብ ጋር ህያው ሆኖ የሚኖር ስሪታችን ነው ። መንግስት “በህግ ማስከበር ” ስም ለአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ የሆነውንና በህልውና ዘመቻው ግንባር ድረስ በመዝመት ሀገርን ከመፍረስ የታደገውን የፋኖ አባላትንና አመራሮችን ያለምንም የፍርድቤት ማዘዣ በወታደራዊ ካምፖችና በስውር ቦታዎች በጅምላ እያሰሩ ይገኛል ። መንግስት ባመነው እንኳን ከ5000 በላይ የአማራ ተወላጆችን አስሮ እንደሚገኝ ጥምር ግብረሃይል ብሎ ያሰማራው ሀይል በኩል አሳውቋል ። ይህ የጅምላ እስር የህልውና አደጋ የተጋረጠበትን አማራ የበለጠ የጥቃት ተጋላጭ ለማድረግ እና በህልውና ዘመቻው በአዋጅ ራሱን እንዲከላከል ተፈቅዶለት ማርኮ በእጁ ያስገባውን ለማስፈታት የተጀመረው ዘመቻ እጅግ አደገኛና ውጤቱ የከፋ እንደሚሆን እያስጠነቀቅን፣ በዚህ አጋጣሚ የፋኖ ትግል አማራን ብሎም ኢትዮጵያን የመከላከልና የነጻነት ተጋድሎ በመሆኑ በዚሁ ድጋፋችን እንደማይለየው ማረጋገጥ እንወዳለን ። 8ኛ. አዲስ አበባ ራሷን የቻለች በቻርተር የምትተዳደር የፌደራል መንግስቱ መቀመጫ መሆኗን በህገ መንግስቱ ቢደነገግም ከዚህ በተጻራሪ የኦሮሚያን ህገ-መንግስት አዲስ አበባ ላይ ለመተግበርና የኦሮሚያን ከፋፋይ የክልል መዝሙር ነፍስ ባላወቁ ህጻናት ላይ በኃይል ለመጫን ፣የአንድን ክልል ባንዲራ በተለየ መልኩ አዲስ አበባ ውስጥ እንዲሰቀል ማድረግ ፍጽም የለየለት ህገ-ወጥነትና ሌሎችን ብሄርብሄረሰቦች መናቅና ህገመንግስቱንም መናድ በመሆኑ ይህን በፌደራልና በኦሮሚያ መንግስት የተጀመረውን አዲስ አበባን የመስልቀጥና ጥንታዊቷን ኢትዮጵያን በማፈራረስ ኦሮሙማን የመመስረት ህገ ወጥ ተግባር በጽኑ እያወገዝን መላው ኡትዮጵያዊም ይህን ተግባር እንዲቃወም ጥሪያችንን እናስተላፋለን። የአዲስ አበባ ህዝብ ቆጥቦ ባጠራቀመው ገንዘብ የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶችች ከህግ ወጪ እንዲተላለፉ ፣ የመሬት ወረራ እንዲስፋፋ እና ህገወጥ ዘረፋ እንዲካሄድ ያደረጉት ካንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ያለመከሰስ መብታቸው ተንስቶ ጉዳያቸው በህግ እንዲታይ እንጠይቃለን። 9ኛ. መንግስት ከትሕነግ ጋር የጀመረው ድርድርም ሆነ ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ከፓርቲ ፖለቲካ እና ከአንድ አንባገነናዊ ግለሰብ ፈላጭ ቆራጭነት እና ሁሉን ነገር ከመቆጣጠር አባዜ ተላቆ ህዝብ ያመነባቸው ፣ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ፣ እውቀቱ እና ቁርጠኝነቱ ባለቸው የህዝብን ዘላቂ ሰላም እና ጥቅም በሚያስጠብቁ እውነተኛ ወኪሎች እንዲመራ እንፈልጋለን። በዚህ መሰረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በፌደራል መንግስቱ በኩል የተወከሉ ተደራዳሪዎች የአማራን ጥቅም ሊያስጠብቁ የማይችሉና ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ የአማራን ጥቅም አሳልፈው የሰጡ በመሆኑ ህዝባዊ አመኔታ የሚጣልባቸው ባለመሆኑ በምትካቸው በቀጥታ አማራን ሊወክሉ የሚችሉ ከአማራ ምሁራን ፣ ከህግ ባለሞያዎች ፣ ከታሪክ ተመራማሪዎች ፣ ከአካባቢው ነዋሪዎች የተወጣጡ እውነተኛ ወኪሎች እንዲወከሉ እንጠይቃለን ፤ በድርድር ስም አንድ ስንዝር የአማራ መሬት ለማንም አሳልፎ መስጠት እንደማይቻል አበክረን ማስገንዝብ እንወዳለን ። 10ኛ. አማራ የገጠመውን የህልውና አደጋ መቀልበስና አንደ ህዝብ መቀጠል የሚችለው እጅ ለእጅ ተያይዞ በጋራ ለአማራዊ እንድነት መቆም ሲቻል ነው ብለን እናምናለን። በሌላ በኩል አማራው ብቻ እየሞተላት የምትድን አገር ስለማትኖርና ዛሬ በአማራው ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ ለሌሎችም ህዝቦች ሊዳረስ የሚችል የጋራ አደጋ መሆኑን በመገንዘብ መላው ኢትዮጵያዊ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በስሙ በመጥራት “የአማራን የዘር ፍጅት” እንዲያወግዝና ከአማራ ጎን ቆሞ የትግሉ አካል እንዲሆን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። አንድነት ኃይል ነው !!! አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ !!! ሀምሌ 27/2014 ዓ.ም ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply