You are currently viewing ከአማራ ህዝባዊ ኮሚቴ የተላለፈ መልዕክት '' መጋቢት 24 እና አማራው'' መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባለፉት 60 ዓመታት ውስጥ የዘውገኞች ጥቃት ማዕከል ሆኖ የቀጠለው አ…

ከአማራ ህዝባዊ ኮሚቴ የተላለፈ መልዕክት '' መጋቢት 24 እና አማራው'' መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባለፉት 60 ዓመታት ውስጥ የዘውገኞች ጥቃት ማዕከል ሆኖ የቀጠለው አ…

ከአማራ ህዝባዊ ኮሚቴ የተላለፈ መልዕክት ” መጋቢት 24 እና አማራው” መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባለፉት 60 ዓመታት ውስጥ የዘውገኞች ጥቃት ማዕከል ሆኖ የቀጠለው አማራ፤ ግማሹን ዘመን በትርክት ፣ ቀሪውን ዘመን በአገራዊ ስርዓታዊ ስሪት ሲጠበስ የኖረው የአማራ ሕዝብ ደግሞ ዛሬ ላይ ከፍተኛ የማጥቃት እድገት በፈጠረ የዘረኞች አስተሳሰብና ትርክት የሕልውና አደጋ ላይ ይገኛል። እጅግ የከፋው አማራ ተኮር የጅምላ ጭፍጨፋ እና ዘር ማፅዳት ስርዓታዊ ጥቃት ደግሞ ራሱ አማራው ታግሎ እና ደግፎት ለስልጣን ባበቃው እና የወያኔ/ኢሕአዴግ አላማ ወራሽ በሆነው የኦነግ/ብልፅግና አገዛዝ ተባብሶ ቀጥሏል። ሀ) መጋቢት 24 ለአማራው ምን አመጣለት ? አማራ፡ ከአምስት አመት በፊት፡ ስናይፐር ፊት ቆሞ በደሙ ያመጣው ለውጥ ፣ የሥልጣን ደረጃ እና አይነት ሳይመርጥ በተቀበለው ፣ የለውጥ መሪዎች ጎሳ እና ኃይማኖት ሳይመርጥ ተቀብሎ የደገፋቸው ሹመኞች ያመጡለት የታገለለትን ተስፋ ሳይሆን ያልጠበቀውን የግፍ መከራ ነው። መጋቢት 24 ያመጣልን፤ በጅምላ መጨፍጨፍ ፤ በጅምላ መፈናቀል ፣ በጅምላ መሰደድ ነው። መጋቢት 24 ለአማራዎች ፤ በአገራችን በተፈናቃይነት የምንባዝንባት ፣ መኖርም መንቀሳቀስስም የተከለከልንባት አገር አውርሶናል !! መጋቢት 24 ያወረሰን፣ ትምህርት ቤት መዋል የነበረባቸው ልጆቻችን እና ወጣቶቻችን በተፈናቃይ ጣቢያዎች ተሰብስበው እርዳታ ጠባቂ የሆንባትን አገር ነው!! መጋቢት 24 ለአማራዎች ያተረፈልን በታሪክ ወደር በማይገኝለት የጦርነት አዙሪት መጨፍጨፍን ፣ የወገናችን ሀብትና ንብረት መውደምን ነው። የእናቶቻችን እና እህቶቻችን መደፈርና የጦርነት ወንጀል ሰለባ መሆንን ነው!! መጋቢት 24 ለአማራዎች ያተረፈልን ፣ ከግንቦት 20ም ፣ ከመስከረም 2ም የባሰ የዘረኛ ጨቋኞች የግፍ በትር ነው!! ለ) ዛሬ ምን ላይ ነን? እኛ አማራዎች ዛሬ ላይ ያለነው፡ የዛሬ አምስት አመት በትግላችን ያመጣነው ለውጥ በአሳሳች ዘረኞች ጨንግፎ እና ተጠልፎ የባሰ አደጋ ላይ ነው። ዛሬ ላይ ያለነው ፤ የኢሕአዴግን ከፋፋይ አምባገነን ስርዓት ሲታገሉ የጥይት አረር የፈጃቸው የጎንደር ፣ የጎጃም ፣ የወሎ ፣ የሸዋ ፣ የዋግኸምና አዊ ታጋዮችን ደም ያራከሱ ተረኛ ጨፍጫፊዎች ፊት ነው !! ዛሬ ፤ መጋቢት 24 ባወረሰን ፀረ-ሕዝብ አላማዎች፣ ከመስከረም ሁለትም ፣ ከግንቦት ሃያም የባሰውን ሰብዓዊ ውድመት እያስተናገድን ነው። ዛሬ ላይ ያለነው፤ ከቀደሙት ስህተቶች የሚማር ሳይሆን የቀደሙት አገዛዞች የሔዱበትን መንገድ የእነሱን ጫማ አባብሶ የሚረግጥ ፣ ሰብዓዊ ስቃይን እና ማህበራዊ ምስቅልቅልን የፖለቲካ ስልት ያደረገ አምባገነን ተጭኖን ነው። አማራዎች ዛሬ ላይ የምንገኘው፤ አማራነትን መካድ የመዳኛ መንገድ እንዲሆን ባስገደደ፣ ሰው በላ አገዛዝ ስር ነው። ዛሬ የምንገኝበት ሁኔታ፤ በጅምላ መጨፍጨፍ ፣ በጅምላ መፈናቀልን የሠርክ ተግባር ያደረገ ሥርዓት በሚሠራው የዘር ማፅዳት ተግባር ወቅት ነው። አማራዎች ያለንበት ወቅት ፤ የመንቀሳቀስ ፣ የማምለክ ፣ ሀብት ንብረት የማፍራት ፣ በፈቀድነው የአገር ክፍል የመኖር መብታችን እንዲሁም በሕይወት የመኖር ተፈጥሯዊ መብታችን በኦሮሞ ገዢ ቡድኖች በሚፈፀምበት ወቅት ነው። እኛ አማራዎች ዛሬ ላይ የምንገኘው ፣ አገር በመውደዳችን፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነትን በማስቀደማችን የጠሉን ጠላቶች በከፈቱብን የመጨረሻ የጥፋት አዋጅ ላይ ነው!! እናም የአማራ ሕዝብ እጅግ ወሳኝ ወቅት ላይ ይገኛል። አሁን ላይ አማራዎች የምንገኝበት ምዕራፍ፣ የታወጀብንን የዘር ማፅዳት እና ዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ለመመከት ቆርጠን መተባበር እና መደራጀት የሚገባን ትግል ወቅት ነው!! የአማራ ሕዝብ ለ60 ዓመታት የተሰበከ እና የሠራ ፖለቲካ እያደረሰበት ያለው ጥቃት፤ ዳግም የጥቃት ምንጭ እንዳይሆን አድርጎ የመታገል እጅግ አንገብጋቢ ሁኔታ ላይ ነው። አማራዎች ዛሬ የቦታ ርቀት ፣ የሙያ ዘርፍ ፣ የሥራ ሁኔታ እና አመለካከት ሳይገድበን በሁሉም ሥፍራ ፣ በሁሉም ሁኔታ በአንድነት ቆመን ጠላትን መታገል የሚገባን ምዕራፍ ላይ ነን!! አማራ አሁን፣ የዛሬ አምስት አመት የተካደው እና በከፋ ሁኔታ የቀጠለው የዘረኞች አካሔድ ከዚህ በላይ ማጥቃቱን እንዳይቀጥል ማድረግ የሚያስችለውን ሁለንተናዊ ትግል ማድረግ የሚገባው ጊዜ ላይ ነው።በዚህ አምስት አመት ውስጥ የተደረገብንን ግፍ አንድ በአንድ ነቅሰን አውጥተን ስናስታውሰው ለነፃነታችን የምናደርገው የትግል ጉዞ ፈጣን ይሆናል፡፡መጋቢት 24 ቀንም በአማራው ታሪክ ውስጥ በጥቁር መዝገብ ውስጥ የሚመዘገብ ነው፡፡ በመሆኑም መጋቢት 24 ቀን በአማራ ክልል ከተሞች በሚደረገው በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ አማራው በበዘር ተኮር ጭፍጨፋው ያለቁ ወገኖቹን ይዘክራል፣ ለነፃነቱ ሲፋሙ የወደቁት ፋኖዎቹን ይዘክራል፣ለነፃነቱ ሲታገሉ ወደ እስር ቤት የተወረወሩ ፋኖ ልጆቹ እንዲፈቱ አበክሮ ያስጠነቅቃል፡፡ በተጨማሪም መጋቢት 24 ቀን በአማራ ክልል ከተሞች በሚደረገው ሰልፍ የአማራ ህዝብ የህልውና ትግሉን ወደፊት ለማራመድ ህዝባቸንን የምናነቃቃበት ይሆናል፡፡ የአማራ ህዝባዊ ኮሚቴ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply