You are currently viewing ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/ የባህር ዳርና አካባቢዋ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ ፤ ************ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ከድር…

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/ የባህር ዳርና አካባቢዋ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ ፤ ************ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ከድር…

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/ የባህር ዳርና አካባቢዋ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ ፤ ************ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ከድርጅቱ ሕገ ደንብና አሰራር ውጪ በመሆን አፍራሽ ድርጊትና የዲሲፕሊን ጥሰት ፈፅመዋል ባላቸው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ላይ ሚያዚያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ተወያይቼ አሳለፍኩት ያለውን ውሳኔ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/ የባህር ዳርና አካባቢዋ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የማይቀበለውና በጽኑ የሚያወግዘው መሆኑን ይገልጻል ። አብን የአማራን ሕዝብ የኅልውና አደጋ በመቀልበስ አማራውን ማዕከል አድርጎ የተሰበከውን ስሁታዊ ትርክት የሚያርቅና የተሰበረውን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሚዛን በማስተካከል ጠንካራ ኢትዮጵያን እውን የማድረግ አላማ ይዞ የተቋቋመ ንቅናቄ ቢሆንም በዚህ ወሳ…ኝ ታሪካዊ የትግል ምዕራፍ ወቅት ከፍተኛ አመራሩ ንቅናቄው ከተቋቋመለት ዓለማ ውጭ ከደንብና መርህ ውጭ በመሆን ሕዝባችንን ለከፋ አደጋ በሚዳርግ መንገድ እየተጓዘ ይገኛል፡፡ ይሄንና በሕዝባችን ላይ ከተጋረጠውና ፋታ ከማይሰጠው የኅልውና አደጋ አኳያ መፋዘዝና ድክመት መኖሩን ሁሉም የንቅናቄያችን መዋቅር በየደረጃው በመገምገም ንቅናቄው የአማራን ሕዝብ ችግር በሚፈታበት ፍጥነትና ቁመና ላይ ይገኝ ዘንድ የመጣበትን መንገድ ጥንካሬና ድክመት ፣ መዳረሻ ግቡንና የአማራ ሕዝብን ብሎም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታን የገመገመ ለውጥ (ሪፎርም) እንዲሁም ተቋሙ መዋቅራዊና የሕገ ደንብ ማሻሻያ እንደሚያስፈልግና ማሻሻያውም ሥራን ፣ ውስጣዊ ድክመትንና ተቋም መገንባትን ማዕከል አድርጎ እንዲከናወን ጠቅላላ ጉባዔው መጋቢት 11 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 3ኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ጠይቋል ። ሆኖም የንቅናቄው ከፍተኛ አመራሮችና የጉባኤው ሰብሳቢዎች በሪፎርም አጀንዳ ላይ ከመወያዬት ይልቅ አጀንዳው እንዳይነሳ ከማፈን ጀምሮ ስብሰባው ሳይጠናቀቅ የጠቅላላ ጉባዔውን ረግጦ በመውጣት እና የተለያዩ መገናኛ ብዙኃንን በመጠቀም እርስ በእርሱ የሚጋጭ መግለጫ በመስጠት ሕዝባችንን ፣ አባላችንንና ደጋፊዎቻችንን ለማደናገር ቢሞክሩም የጠቅላላ ጉባዔ አባላት ተወካዮች ለምርጫ ቦርድ ባቀረቡት አቤቱታ እና የምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች ሪፖርት ጠቅላላ ጉባዔው እስከ ሰኔ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ እንደገና እንዲካሄድና ያልተቋጨው አጀንዳም ውይይት እንዲደረግበትና ፍፃሜ እንዲያገኝ ምርጫ ቦርድ መወሰኑ ይታወቃል። ይህ በዚህ እንዳለ ከፍተኛ አመራሩ የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ተቀብሎ ከማስፈጸም ይልቅ በሌላቸው ሥልጣን የንቅናቄያችንን ጠንካራ አመራሮችና አባላት ላይ የእገዳና ማስጠንቀቂያ እርምጃዎችን ወስኗል፡፡ ውሳኔው የንቅናቄውን ሕገ ደንብ የጣሰ ከመሆኑም ባሻገር ግለሰባዊና የጥቂት ቡድን ፍላጎትን ከድርጅትና ከአማራ ሕዝብ ፍላጎት በማስቀደም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የአማራን ሕዝብ ማኅበራዊ እረፍት የመንሳት የጠላቶቻችን የኖረ የሴራ አካል በመሆን አብንን ለማፍረስና መላው የመዋቅራችንን አመራር፣ አባላትና ደጋፊዎች ብሎም የአማራን ሕዝብ ከመናቅ የመነጨ ውሳኔ እንደሆነ የአብን የባህር ዳርና አካባቢዋ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በጽኑ ያምናል ። በመሆኑም የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባለት የወሰኑትን የእገዳና ማስጠንቀቂያ እርምጃዎችን በጋራ ከገመገመ በኋላ የሚከተለውን አቋም ወስዷል፤ 1. ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የእገዳና ማስጠንቀቂያ እርምጃዎች የመውሰድ ስልጣን የሌለው እና በአብን መተዳደሪያ ደንብም ሆነ በሞራል ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/ የባህር ዳርና አካባቢዋ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለድርጅታችን አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም መላው የአማራ ሕዝብ ይህንን አፍራሽ ውሳኔ በጋራ እንዲታገለው ጥሪያችንን እናቀርባለን ! 2. የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የተቋረጠውን የሪፎርም አጀንዳና ያልተጠናቀቀውን ጉባኤ በድጋሚ በሚካሄደው ጉባኤ ለማጠናቀቅ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ባለመቀበልና የምርጫ ቦርድን ውሳኔ በማደናቀፍ እና ሕዝብን በማጭበርበር የግል ወይም ውስን ቡድን ጥቅምን ለማስጠበቅ ሲባል ከሚደረግ ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠብ በጥብቅ እናሳስባለን ፤ 3. ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚው ለቀረበለት መሰረታዊ የመዋቅር እና የሕዝብ ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ታሪካዊ አደራውን እንዲወጣ ጥሪያችንን እያቀረብን ድርጅቱን አደጋ ላይ የሚጥለውን ግብታዊ ውሳኔ በድጋሚ እንዲያጤነው እንጠይቃለን፤ ለሰራው ስህተትም መላው የአማራን ህዝብ ፣ የንቅናቄያችንን አባላት እና ደጋፊዎችን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ እናሳስባለን ! 4. በመሰል ማስፈራሪያና ዛቻ የጠቅላላ ጉባኤውን የሪፎርም ጥያቄ ማዳፈን የማይቻል በመሆኑ የአብን ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም መላው የአማራ ሕዝብ እውነታውን ተረድቶ አብንን ለማዳን ከሚደረገው ትግል ጎን በመሰለፍ አውንታዊ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ እናቀርባለን። መዋቅራችንም ለዚህ በሙሉ ትኩረት ይሰራል። አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ ! የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/ የባህር ዳርና አካባቢዋ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ግንቦት 3 ቀን 2014 ዓ.ም ባህር ዳር፣ ኢትዮጵያ

Source: Link to the Post

Leave a Reply