ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ **** ፍትሕ በሐሰት ትርክትና የጥላቻ ስሜት የጅምላ ጭፍጨፋ ሰለባ ለሆኑ ወገኖቻችን! አሸባሪውና ዘረኛው ትሕነግ የሽምቅ ተዋጊ በነበረበት…

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ **** ፍትሕ በሐሰት ትርክትና የጥላቻ ስሜት የጅምላ ጭፍጨፋ ሰለባ ለሆኑ ወገኖቻችን! አሸባሪውና ዘረኛው ትሕነግ የሽምቅ ተዋጊ በነበረበት ጊዜ ጀምሮ ወልቃይትና ጠገዴ አካባቢ ያለውን ስትራቴጅያዊ ጠቀሜታና ሀብት በመገንዘብ አካባቢውን ለመቆጣጠር ወጣ ገባ ማለት ከጀመረበት 1972 ዓ.ም ጀምሮ በተለይም አካባቢውን ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠረበት 1983 ዓ.ም ጀምሮ በወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ የአማራ ሕዝብ ላይ መጠነ ሰፊ ግድያ፣ ማፈናቀልና አፈና ሲፈፅም ቆይቷል:: በዚህም በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ማንነታቸው ወንጀል ሆኖባቸው እንደወጡ ቀርተዋል፡፡ በጥቅሉ፣ ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ዓለም ጀሮ የነፈገው የዘር ማጥፋት ወንጀል በወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ ላይ ተፈጽሟል፡፡ ጥቅምት 24/ 2013 ዓ.ም አሸባሪውና ዘረኛው ትሕነግ በሰሜን ዕዝ ልዩ ልዩ የጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት ማድረሱን እና በሁለት አቅጣጫ ደግሞ አማራ ክልል ላይ የጦር ወረራ መፈፀሙን ተከትሎ በሕግ ማስከበር ዘመቻው በደረሰበት የመልስ ምት፣ ቡድኑ አካባቢውን ለቆ እንዲሄድ የተደረገ ሲሆን፤ በሚያፈገፍግበት ወቅት ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም. በማይካድራ ከተማ በሺህ የሚቆጠሩ አማሮችን፤ በተመሳሳይ ሕዳር 03/ 2013 ከሁመራ ከተማ አርባ ኪሎ ሜትር በምትርቀው ‹እድሪስ› የተባለች የገጠር ቀበሌ/ከተማ ላይ የተመረጡ የአማራ ባለሀብቶችን ጨፍጭፎ መሄዱ የሁሉንም ልብ የሰበረ ክስተት እንደነበር ይታወሳል፡፡ አሸባሪው ቡድን ከወልቃይት፣ ጠገዴና ሁመራ አካባቢ ተመትቶ መልቀቁን ተከትሎ የሁመራ ኤርፖርት በቁጥጥር ስር ሲውል በዙሪያው የጅምላ መቃብሮች የተገኙ ሲሆን፤ በዚሁ ቀጠና በተለያየ ጊዜ የተለያየ ቦታ ላይም በርካታ የጀምላ መቃብሮች ተገኝተዋል:: ከሰሞኑ በወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ አካባቢ ለአስራ ስድስት ወራት ጥናት ሲሰራ የቆየው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የጥናት ቡድን የአካባቢው ማኅበረሰብ “ገሃነም” እያለ በሚጠራው የትሕነግ ድብቅ የማሳቃያ፣ መግደያና ማሰሪያ ቦታ እጅግ አስደንጋጭ የሆነ የጅምላ መቃብር ተገኝቷል:: ትህነግ በሐሰት ትርክት ከቆመበት ተፈጥሯዊ የጭካኔ ባህሪውና በአካባቢው ሲፈጽማቸው ከኖሩ ዓለማቀፍ ወንጀሎች አኳያ ተጨማሪ ምርመራ ቢደረግ አያሌ የጅምላ መቃብሮች እንደሚገኙ አያጠራጥርም:: ስለሆነም:- ፩. የፌደራል መንግሥቱ በተለይም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ የአማራ ክልል መንግሥት ጥናቱን ቀድመ ብሎ ከጀመረው የጎንደር ዩኒቨርሲቲና መሰል የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር ይኸን መዋቅራዊ ሆኖ ለሦስት አስርት ዓመታት የዘለቀ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲጣራ እንዲያደርጉ፣ ይህን ዓለማቀፍ ወንጀል የፈፀሙ የትህነግ ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች ላይ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ሁሉን አቀፍ (ሙያዊና ተቋማዊ) ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ አብን አጥብቆ ይጠይቃል:: ፪. የአማራ ሕዝብ አሁንም በተለይ በምዕራብ ኦሮሚያ (ወለጋና አካባቢው) የጅምላ ፍጅት ሰለባ ሆኖ የቀጠለ ስለሆነ መንግሥት የጅምላ ፍጅቱን እንዲያስቆም እየጠየቅን፣ የወንጀሉ ተባባሪና አቀናባሪ የሆኑ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት ኃላፊዎችን ጨምሮ ወንጀል ፈፃሚዎችን ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ለሕግ እንዲያቀርብ በጥብቅ እንጠይቃለን:: የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ በዜጎች የሰብዓዊ መብት ዙሪያ የሚሰሩ ሀገር በቀልና የውጭ ተቋማት በእነዚህ አካባቢዎች የተፈፀሙ መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋዎችን እንዲያጣሩና ተጠያቂነትም እንዲሰፍን የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ እንጠይቃለን:: ፍትሕ በሐሰት ትርክትና የጥላቻ ስሜት የጅምላ ጭፍጨፋ ሰለባ ለሆኑ ወገኖቻችን! መጋቢት 26/ 2014 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Source: Link to the Post

Leave a Reply