You are currently viewing ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠቅላላ ጉባኤ አመቻች ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ፣ ________ ድርጅታችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ ህዝባዊና ማህበራዊ ንቅ…

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠቅላላ ጉባኤ አመቻች ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ፣ ________ ድርጅታችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ ህዝባዊና ማህበራዊ ንቅ…

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠቅላላ ጉባኤ አመቻች ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ፣ ________ ድርጅታችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ ህዝባዊና ማህበራዊ ንቅናቄዎችን ከመፍጠሩ ባሻገር ህዝባችን ነገን በተስፋ እንዲጠብቅ አዎንታዊ ኃይል የሆነና፤ የአማራ ህዝብ በተለይም የወጣቱ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ከመቸውም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ እንዲጎለብት ያደረገ፤ በተለያዩ ጊዜያት በያዛቸው ፖለቲካዊ አቋሞቹ ሀገርንና ህዝብን መታደግ የቻለ ፓርቲ ነው፡፡ ሆኖም ግን ድርጅታችን አሁን ላይ የገጠሙትን ፈተናወች ለማለፍ ማዕከላዊ ኮሚቴው ችግሮችን በጥልቀት በመገምገም የሀሳብ እና የተግባር አንድነት ያለው ጠንካራ አደረጃጀት ለመፍጠር እና ጊዜውን እና የፖለቲካ ሁኔታውን የሚመጥን ተራማጅ የፖለቲካ ትግል ለማድረግ የሚያስችል አቅም ለመገንባት ይረዳ ዘንድ የአሰራርና የአደረጃጀት እንዲሁም የአመራር ሪፎርም እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፎ የሪፎርም ጉባኤ አመቻች ኮሚቴ አቋቁሞ ተጨባጭ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ኮሚቴውም የተሰጠውን ሃላፊነት በተገቢው መንገድ የተወጣና ስራውን ያጠናቀቀ ሲሆን ድርጅታችን ያጋጠመው የፋይናንስና ሎጀስቲክ ውስንነቶች እንደተስተካከሉ ጉባኤውን በአጭር ጊዜ ውስጥ የምናካሂድ መሆኑን እየገለጽን:- መላው የድርጅታችን አባላት: የአማራ ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎችና የሀገራችን ችግሮች የተራዘመና የተጠናከረ ትግል የሚጠይቁና ጥያቄዎችን ለመድረክ በማብቃት እልባት እንዲያገኙ የሚያስችል መነሻ አማራዊ የፖለቲካ ሀይል ማፅናት መሰረታዊ ትኩረት ተደርጎ ሊከናወን እንደሚገባ በመረዳት ከምንም በላይ መሪ ድርጅታችን አብንን በመጠበቅና በማፅናት እንድትረባረቡ፤ አሁን ያለንበት ነባራዊ ሁኔታ ከመቸውም ጊዜ በላይ አንድነታችን ጠብቀን ህብረታችንን አጠንክረን ለህዝባችን የፍትህና የእኩልነት ጥያቄ በአብሮነት መንፈስ በፅናት የምንታገልበት ታሪካዊ ወቅት ላይ መሆናችንን በመገንዘብ የተለመደ ድርጅታዊ አንድነታችሁን ጠብቃችሁ እንድትሰሩ እናሳስባለን፡፡ በተለያየ ደረጃ ላላችሁ የድርጅታችን አመራሮች፡- የጠቅላላ ጉባኤውን ዝግጅት በተመለከተ በማዕከላዊ ኮሚቴው በኩል ለአመቻች ኮሚቴው የተሰጠ ስልጣን መሆኑን በመገንዘብ ማህበራዊ ሚዲያን ጨምሮ ጉባኤውን የተመለከተና አብን በአጭር ጊዜ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በሳልና ገንቢ ሚና በመጫወት ያገኘውን ህዝባዊ ድጋፍና አመኔታ የሚያሳጣ፤ የህዝባችን ድምፅና ተገቢ የፖለቲካ ሀይል ሆኖ እንዲቀጥል ከተሰጣችሁ አብናዊ ሃላፊነት አባላችንን እና ደጋፊያችንን አላስፈላጊ ጫና ውስጥ ከሚከቱ እና እምነት ከሚያሳጡ እንቅስቃሴዎች እንድትቆጠቡ፤ በተቻለ መጠን ለምንወደውና ቀድመን መስዋዕትነት ልንከፍልለት ለተዘጋጀንለት የህዝባችን አንድነትና ፖለቲካዊ ህልውና አዎንታዊ ሚና እንድትጫወቱ እናሳስባለን፡፡ ለደጋፊዎቻችንና ለመላው የአማራ ህዝብ፡- ምንም እንኳን ከህዝባችን ውስብስብና ሰፊ ችግሮች አንፃር መሰረታዊ የሚባል ለውጥ ባይመጣም ለነበሩን ወሳኝ አቋሞቻችንና የትግል እንቅስቃሴዎች ጉልህ ሚና የነበራችሁ መሆኑን እየገለፅን ካለፈው ይልቅ አሁን አብን የእናንተን ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚሻበት ወቅት በመሆኑ ድጋፋችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የጠቅላላ ጉባኤ አመቻች ኮሚቴ አዲስ አበባ፣ ሸዋ፣ ኢትዮጵያ ሐምሌ 23 ቀን 2014 ዓ.ም.

Source: Link to the Post

Leave a Reply