You are currently viewing ከአማራ አንድነት ማህበር በእስራኤል የተሰጠ መግለጫ፥ እስራኤል! የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በሃገራችን የተከሰተውና እየተፈፀመ ያለው ሃገር የማፍረስ ብሎም ህዝብን ከህዝብ…

ከአማራ አንድነት ማህበር በእስራኤል የተሰጠ መግለጫ፥ እስራኤል! የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በሃገራችን የተከሰተውና እየተፈፀመ ያለው ሃገር የማፍረስ ብሎም ህዝብን ከህዝብ…

ከአማራ አንድነት ማህበር በእስራኤል የተሰጠ መግለጫ፥ እስራኤል! የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በሃገራችን የተከሰተውና እየተፈፀመ ያለው ሃገር የማፍረስ ብሎም ህዝብን ከህዝብ የመከፋፈልና የመለያየት የ50 አመታት የፖለቲካ ሸፍጥ ሴራ መሆኑ አለም የሚያውቀው እውነታ ነው:: አሁን ላይ የምንሰማውና የምንመለከተው በመንግስታዊ መዋቅር የሚታገዘው የሐይማኖት ጦርነት ጉሰማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ቀኖናዊ ስነ ባህሪ የተዳፈረ ብሎም የጣሰ ነው:: በግልፅ የሚታይ ሐይማኖታዊ ዘረፋንና ተቋሟን እንደተቋም ለማውደም እየሰራበት ያለውን የአገዛዙን የሰከረና የከሰረ ፖለቲካ አካሄድ አጉቶ የሚያሳይ ነው:: አፈሙዝንና ስልጣንን በመጠቀም የራስን የግል ሐይማኖት ለማግዘፍ የተሄደበት አደገኛ አካሄድን በመመልከቱ ማህበራችን እጅጉን አሳዝኖታል:: መላው ምዕመናኑንም ያስቆጣ መሆኑን ያምናል። ስለሆነም ማህበራችን የአማራ አንድነት ማህበር በእስራኤል ከመላው የኦርቶዶክስ ምዕመናንና ከቤተክርስቲያኗ ጎን የቆመ መሆኑን እየገለፀ የሚከተሉትን ባለ አምስት(5) ነጥቦች የአቋም መግለጫዎችን ያስተላልፋል ። 1) በሃገራችን ኢትዮጵያ በተፈጠረው የፖለቲካ ሴራና ሸፍጥ በአጋጠመው ቀውስ የሰው ልጆች በሰላም በእናት ሃገራቸው እንዳይኖሩ በመንግስታዊ መራሹ ታጣቂዎችና በሃገር አፍራሽ ቡድኖች ሰዎች በግፍና በጭካኔ እየተጨፈጨፉ ; እየተገደሉ ; አስከሬናቸው ለዱር አውሬ እራት ሆኗል:: በህይወት የተረፉትም መቸ እንደሚጨፈጨፉና እንደሚረሸኑ የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው:: ለዚህም የወገኖቻችን እልቂት የአብይ አህመድ አረመኔያዊ አገዛዝ በዋናነት በቀጥታ ተጠያቂ መሆኑን ማህበራችን ያምናል ለዚህ እኩይ ተግባሩም አጥብቆ የሚታገለው መሆኑን ማህበራችን ይገልፅል ። 2) ማህበራችን በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ በደረሰባት ሁለተናዊ ጥቃትና መከራ በእጅጉ አዝኗል:: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኝ ምዕመናንና ብሎም በቤተ ክርስቲያኗ ተቋም ላይ በሴራና በሸፍጥ በመንግስታዊ ጣልቃገብነትና ጫና ለተፈፀመባት ክህደት; የማፍረስ የመዝረፍና የማዘረፍ ክስተቶች ሙሉ በሙሉ አገዛዙ ተጣያቂ መሆኑን በግልፅ እየተፈፀመ ያለው እውነታ ምስክር ነው።ለዚህም የቤተ ክርስቲያኗን ቀኖና ባላከበረ መልኩ ህዝቦቿን ልጆቿን ብሎም ለዘመናት የገነባችው የሃገር ማፅናት የሃገር መገንባትና ከትውልድ ወደ ትውልድ; ከዘመን ዘመን የማሸጋገር በጎ እሴቿን ለመደፍጠጥና ጠቅላላውን ለማጥፋት በታሰበ ሁኔታ ህገወጥ ግለሰቦችን በአገዛዙ ሹመኞች አድራጊ ፋላጭ ቆራጭነት ግለሰቦችን የጵጵስና ሹመት መስጠት ከድፍረትም ባሻገር የማፍረስ አንዱ የአገዛዙ ተልዕኮ መሆኑን ማህበራችን ያምናል:: ይህን ተግባርም ያወግዛል; ይቀዋወማል። 3) ማህበራችን በተለይም በኦሮምያ ክልል በመንግስት ጭምር ድጋፍ እንደሚደረግለት በሚታመነው በኦነግ የአሸባሪ ታጣቂዎችና በራሱ በኦሮሚያ የክልል መንግስታዊ ልዮ ሃይል በተቀናጀ ሁኔታ በማንነታቸው ብቻ ተለይተው እየተጨፈጨፉ በሚገኙት የአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈፀመውን የዘር ማጥፋት አጥብቆ የሚቃወም ከመሆኑም በላይ በልዩ ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ የሚታገልበት መሆኑንም ማህበራችን መግለፅ ይወዳል ። 4) እንደሚታወቀውበአማራ ክልል በህዝባችን ላይ መጠነ ሰፊ የሆነ የእስርና የግድያ; የማዋከብና የእግልት ሁኔታዎች እያየን እየሰማን ነው:: ይህንም በዋናነት እያስፈፀመ ያለው የክልሉ አምባ ገነኖች መሆናቸው አለም ያወቀው ሃቅ ነው:: ስለሆነም የማንኛውም ሰው በህይወት የመኖርና አለመኖር የፈጣሪ ሆኖ ሳለ በአብይ አህመድ የአገዛዝ ሰለባ የወደቀው የአማራ ህዝብ በአሁኑ ስአት በህይወት እንዳይኖር ተፈርዶበት በመጨፍጨፍ ላይ ይገኛል:: ከዚህ በተጨመሪ ስልታዊ በሆነ አካሄድ የአማራን ህዝብ በኢኮኖሚ; በጤና በትምህርት እጦት እያደቀቀው ይገኛል:: የሰባዊ ጥሰቶችም በከፍተኛ ሁኔታ እየፈፀመበት እንደሚገኝ አለም ያወቀውና በግልፅ የሚታይ እውነታ ነው:: ለዚህም እንደ ምሳሌ በተደጋጋሚ የሰሜን ሽዋና አካባቢው ህዝብ በተደጋጋሚ የሚያደስበትን በደል መመልከት በቂነው:: እንደዚህ አይነቱን ፀረ አማራ ትርክትና አስፈፃሚዎቹን ማህበራችን በፅኑ የሚፀየፋና እና አምርሮ የሚታገላቸው መሆኑን ይገልፃል ። 5) ሃገርን ለማፍረስ; ህዝባችን ለማዋረድ በየትኛውም አቅጣጫ የመጣን ወራሪ ሐይልና ባንዳ ለመከላከል ቤቴን ንብረቴን; ቤተሰቤን; ሳይል በራሱ ስንቅና ትጥቅ በብርድ በረሃብና ቁር ሳይበገር ለሃገርና ለህዝብ በተዋደቀው የአማራ ፋኖ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የእስር; የግድያና የአፈና መንግስታዊ ሽብር ማህበራችን ፈፅሞ በዝምታየማንመለከተው መሆኑን እየገለፀ ሁሌም ከፋኖዎቻችን ጎን ነን:: የአማራ ህዝብ ነፃነቱን ለማረጋገጥ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም አማራጩ የአማራን ፋኖ ማጠናከርና ማገዝ የማህበራችን ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን እያረጋገጥን ማንኛውንም ሁለተናዊ የአማራ የትግል መስመር እንደየ ሁኔታው በአንክሮ የምናየው መሆኑን እንገልፃለን ። የአማራ አንድነት ማህበር በእስራኤል የካቲት 06/06/2015 ዓ ም “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply