ከአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ የበዛ ትዕግስት ብዙ ዋጋ አስከፍሎናል!! ሲደርስብን በነበረው ግፍ ጫንቃችን ክፉኛ ሲዝል ኑሯል!!            አሻራ ሚዲያ……

ከአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ የበዛ ትዕግስት ብዙ ዋጋ አስከፍሎናል!! ሲደርስብን በነበረው ግፍ ጫንቃችን ክፉኛ ሲዝል ኑሯል!! አሻራ ሚዲያ……

ከአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ የበዛ ትዕግስት ብዙ ዋጋ አስከፍሎናል!! ሲደርስብን በነበረው ግፍ ጫንቃችን ክፉኛ ሲዝል ኑሯል!! አሻራ ሚዲያ… ጥቅምት 27/2013ዓ.ም ባህርዳር አሁን ገዳዮቻችን ሞት ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚረዱበት ጊዜ ነው:: ህዝባችን ለአመታት በማንነቱ ምክንያት በየአካባቢው እየወደቀ በጨካኞች እየተጨፈጨፈ የበዛ ትዕግስታችን ብዙ ዋጋ ሲያስከፍለን ኑሯል። በዚህም የህዝባችን ስሜት በእጅጉ ተጎድቷል። እኛም ከህዝብ የወጣን መሪወች ነንና ስሜታችን ያዝ አድርገን በእልህ እና በጥንቃቄ ከገጠመን ችግር ጋር ፊት ለፊት ለመጋፈጥ ሞከርን እንጂ በየቀኑ በምንሰማቸው አስደንጋጭ የወገኖቻችን የሞት ዜናዎች ጫንቃችን ዝሎ ከርሟል። በመሰረቱ ብዙ የታገስነው ለህዝባችን ስለማንቆረቆር አልነበረም፤ ለአንዳንድ ወንድሞቻችን ጭምር ስህተት የመሰሏቸውን ተግባራት የፈፀምነው ለህዝባችን ሰላምና ደህንነት አስበን እንጂ ሌላ የተደበቀ ፍላጎት ኑሮን አልነበረም። የሆነ ሁኖ ጠላት በሀገር ህልውና ላይ ክህደት በመፈፀም በጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችንና በአማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢ ግልፅ ጥቃት ፈፅሞብናል። የኢትዩጵያ ህዝቦች ካልወጋሁ ብሎ የጦርነት ነጋሪት ጎስሟል። እኛም በየአቅጣጫው እንደ በግ የታረዱ እና ደማቸው በከንቱ የፈሰሰ ወገኖቻችን ደም ይፋረደን ብለን የጠላትን አከርካሪ ለመምታት ከሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ጋር በደጀንነት ከጎን ቁመናል። ስሩ ሲነቀል ቅርንጫፎቹ ሁሉ ይረግፋሉ የሚል እምነት ይዘን ስሩን ለመንቀል የሚደረገውን ጥረት እስከ ህይወት መስዋዕትነት ጭምር ለመፋለም ተነስተናል። ከወራት በፊት ” እኛ ከበሮ እየመታንና ምሽግ እየቆፈርን አንፎክርም ብለናል” አሁንም ለፉከራ እና ለቀረርቶ አልተነሳንም። ራሳችንን ለመከላከል እንጂ። በዚህ ሂደት መላው የአማራ ህዝብ ፤ልዩ ሀይላችንና ሚሊሻዎቻችን ላሳያችሁት ጀግንነት የተሞለበት አኩሪ ተግባር ምስጋናየ ይድረሳችሁ። ምሁራን፣ የማህበረሰብ አንቂ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ገና ከጅምሩ እያሳያችሁት ላለው አንድነትና ትብብር ላቅ ያለ ምስጋናየን ሳቀርብላችሁ በታላቅ ወንድማዊ ኩራት ነው። በሁላችንም ዘንድ የአካባቢያችንን ሰላም የመጠበቅ ሀላፊነት እጃችን ላይ ወድቋልና ይህ መተባበርና አንድነት የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። ድል ሳይወድ ተገዶ ወደጦርነት ለገባው የመከላከያ ኃይላችን ! ድል የእብሪተኞች የንቀት ማጥቃት ደጋግሞ ለተሰነዘረበት ህዝባችንና ልዩ ኃይላችንና ሚሊሻችን ! አቶ አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ

Source: Link to the Post

Leave a Reply