
#ከአማራ ክልል ታፍነው ከኤርትራ በቅርብ ርቀት በአፋር ክልል ሱላ በርሃ ማጎሪያ ካምፕ እየተሰቃዩ ያሉ ፋኖዎች በረሃብ እያለቁ መሆኑ ተገለፀ! ግንቦት 09 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በዶ/ር ይልቃል ከፋለ ይሁንታ ተላልፈው በአደራ የተሰጡ በአፋር ክልል ከ1500 በላይ በተለያዩ እስር ቤቶች ታስረው የሚሰቃዩ ፋኖዎች ሬሽን በመቋረጡ ህይወታቸው አደጋ ላይ መሆኑን አሻራ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በዚህ ሳምንት ብቻ አምስት ታራሚወች በረሃብ መሞታቸው የተገለፀ ሲሆን በተለይ በኤርትራ 40 ኪ.ሜ ርቀት የሚገኘው ሱላ ማጎሪያ ጣቢያ ከረሃብ በተጨማሪም ቦታው የሙቀቱን መጨመር ተከትሎ ለተያያዥ በሽታወች መዳረጋቸው ተረጋግጧል። ለእስር የተዳረጉትም ፋኖን አሰልጥናችኋል ተብለው የተወነጀሉ ከ1500 በላይ የሚሆኑ የአማራ ተወላጆች በፊት የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበሩ ሲሆኑ በቁጥር ብዙ የሆኑት ደግሞ የአማራ ልዩ ሃይል እና የፌደራል ፖሊስ አባል የነበሩ ናቸው ተብሏል።በአጠቃላይ ከ20 ሺ በላይ ፋኖዎች እና የአማራ ልዩ ኃይሎች በተለያዩ ክልሎች እደታሰሩ ይታወቃል። ከእነዚህም ውስጥ 1500 በላይ በአፋር ክልል የታሰሩ አማራወች በጣም እየተሰቃዩ እደሆነም ተናግረዋል። ድምፅም ሁኑን ሲሉ ለአሻራ ሚዲያ የተናገሩ ሲሆን ብአዴን ከ20ሺ በላይ በተለያየ ክልል አስረሮ የሚታሰቃያቸውን የአማራን ብርቅየ እንቁ ልጆች ካለምንም ቅድመሁኔታ ባስቸኳይ ይፍታ ሲሉ አስተያየት ሰጭዎችም በተለያየ ጊዜ ተናግረዋል። ካልተፈቱ መቼም ቢሆን የአማራ ህዝብ ልጆች ስለሆኑ ህዝቡም ዝም አይልም ተብሏል። በግንቦት 10ሩ የባህርዳሩ ፋኖን የመምታት ዝግ ስብሰባ ተጨማሪ ጥፋት ከማምጣት ከአሁን በፊት በማንአለብኝነት የታፈኑ አማራዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ቢታሰብበት ሲሉ ተጨማሪ አስተያየት ለአሻራ ሚዲያ ሰጥተዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post