ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በጓሕ ጽዮን በኩል ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ አማራዎች የሚፈጸምባቸው እንግልት በአሳሳቢነቱ እንደቀጠለ ነው፤ወጣት ጭናችኋል የተባሉ ከአስር በላይ መኪናዎች እ…

ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በጓሕ ጽዮን በኩል ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ አማራዎች የሚፈጸምባቸው እንግልት በአሳሳቢነቱ እንደቀጠለ ነው፤ወጣት ጭናችኋል የተባሉ ከአስር በላይ መኪናዎች እንዲመለሱ መደረጉ ተሰምቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 7 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በጓሕ ጽዮን በኩል ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ አማራዎች በኦሮሚያ ክልል የጸጥታ አካላት በየጊዜው ወከባ፣ እንግልትና በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ሲገልጹ ይሰማል። ይህ ችግር በተለይም:_ 1) በጎንደር ጎጃም መስመር ጓሕ ጽዮን እና አካባቢው፣ 2) በወሎ ሸዋ መስመር እንዲሁም 3) ከወለጋ ተፈናቅለው ወደ አዲስ አበባ ዙሪያ ሲደርሱ መታወቂያ ታይቶ የተለያዩ ያልተገቡ ምክንያቶችን በመፍጠር ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ሲደረግ ተስተውሏል። የሰሞኑን ብንጠቅስ እንኳ ታህሳስ 5/2015 ከ6 ያላነሱ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባ አታልፉም በመባላቸው ተሳፋሪዎችን ይዘው ጓሕ ጽዮን ላይ እንዲመለሱ ስለመደረጉ መዘገባችን ይታወቃል። መታወቂያ ታይቶ “ወጣቶች ናችሁ” በሚል ምክንያት ተፈጥሮአዊ የሆነውን ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብትን የገደበው ይህ የተበላሸ አካሄድ እንዲስተካከል በተደጋጋሚ እየተጠየቀ ቢሆንም ከማስተካከል ይልቅ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጧል። በአማራዎች ላይ የሚፈጸመው ሁለንተናዊ ግፍ እንደቀጠለ መሆኑን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የተናገሩት ምንጮች ሴቶች እና ሽማግሌዎች በመሆናቸው ብቻ እንዲያልፉ ተፈቅዶላቸው ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ነው። ከአስር በላይ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች ግን ወጣት ጭናችኋል በሚል ከጓሕ ጽዮን እንዲመለሱ ስለመደረጋቸው መስክረዋል። ታህሳስ 7/2015 ከረፋዱ 4:30 አካባቢ ከጎንደር እና ጎጃም የተለያዩ አካባቢዎች የተሳፈሩ በርካታ ተሽከርካሪዎች ጓሕ ጽዮን ከተማ ኬላ ከመድረሳቸው እነሱ የተሳፈሩበት መኪና ወጣት ጭነሃል በሚል ተመልሶ ወደ ባ/ዳር እንዲሄድ ሲታዘዝ የተሳፈሩ ወጣቶችን አስወርዶ በሌላ ተሽከርካሪ እንዲመለሱ ማድረጉን በመግለጽ የኦሮሚያ ልዩ ኃይሎችንና የትራፊክ ፖሊሶችን በመማጸኑ እንድናልፍ ተፈቅዶልናል ትላለች አሚማ ያነጋገራት ተጓዥ። ይህ በአማራዎች ላይ እየተፈጸመ ያለ ሁለንተናዊ ግፍ መፍትሄ ይበጅለት ዘንድ ጥሪ ቀርቧል። ፎቶ_ፋይል

Source: Link to the Post

Leave a Reply