You are currently viewing ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተይዘው ወደ አዲስ አበባ ፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንዲመጡ የተደረጉ 6 ተጠርጣሪዎች በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበውም ለጥቅምት 30…

ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተይዘው ወደ አዲስ አበባ ፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንዲመጡ የተደረጉ 6 ተጠርጣሪዎች በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበውም ለጥቅምት 30…

ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተይዘው ወደ አዲስ አበባ ፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንዲመጡ የተደረጉ 6 ተጠርጣሪዎች በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበውም ለጥቅምት 30 ተቀጥረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከባህር ዳር፣ ከፍኖተ ሰላም፣ ከደብረ ማርቆስ፣ከጎንደር እና ከደብረ ታቦር ተይዘው ወደ አዲስ አበባ ያለ ቤተሰብ እውቅና በሌሊት እንዲመጡ የተደረጉ 6 ወጣቶች ሜክሲኮ በሚገኘው፣ በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ባለው እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ። እነዚህ በፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ ባለው እስር ቤት ታስረው የሚገኙ 6ቱ ተጠርጣሪዎች ጥቅምት 28/2015 ከሰዓት በኋላ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው ክሱ የተሟላ አይደለም አሻሽላችሁ ቅረቡ ሲል ፍርድ ቤት ለፖሊስ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ጥቅምት 29/2015 ከሰዓት በኋላ ለ2ኛ ጊዜ ቀርበው ነበር። ጥቅምት 29/2015 ፍ/ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎችም:_ 1) ደህናሁን ቤዛ ስመኝ፣ 2) አንማው ሙላት አያሌው፣ 3) ብሩክ አያልነህ መኮንን፣ 4) አምሳያው አዳሙ መለሰ፣ 5) ዳንኤል (ሰጠኝ) ዮሃንስ እጅጉ እና 6) ታሪኩ በላይ ፍሰሃ ናቸው። ደህናሁን ቤዛ እና አምሳያው አዳሙ ከባህር ዳር፣ ታሪኩ በላይ ከጎንደር፣ ዳንኤል (ሰጠኝ) ዮሃንስ ከደብረ ታቦር፣ ብሩክ አያልነህ ከፍኖተ ሰላም፣ አንማው ሙላት ከደብረ ማርቆስ፣ በጸጥታ አካላት ከጥቅምት 23 እና 24/2015 ጀምሮ ተይዘው በሽብር ፈጠራ ወንጀል የተጠረጠሩ እስረኞችን በኃይል ለማስለቀቅ እንዲሁም በበራሪ ወረቀት ቅስቀሳ በማድረግ ወንጀል መጠርጠራቸውን ፖሊስ ገልጧል። በችሎቱ የተገኘው ጠበቃ ሀብተ ማርያም ጸጋዬም ሰዎች በአካባቢያቸው የመዳኘት እና በቤተሰቦቻቸው በቅርብ የመጠየቅ ህገ መንግስታዊ መብታቸው ሊካድ እንደማይገባው፣ ጉዳያቸውም በአማራ ክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት ወይም በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት መታዬት እዬቻለ ወደ ፌደራል መምጣታቸው አግባብ አለመሆኑን ጠቅሶ መከራከሩ ይታወሳል። ፖሊስ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ተጠርጣሪዎችን በኃይል ለማስፈታት በተለያዩ ቦታዎች ሲንቀሳቀሱ እና የተለያዩ በራሪ ወረቀቶችን ሲበትኑ በተደረገ ክትትል በጸጥታ ኃይሎች ከጥቅምት 26/2015 ዓ/ም ጀምሮ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ቢገልጽም ተጠርጣሪዎች እንደሚሉት ግን እነ አርበኛ ዘመነ ካሴን ለማስፈታት ወረቀት በትናችኋል በሚል ከጥቅምት 23 እና 24/2015 ጀምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች እንደያዟቸው ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል። የምርመራ መዝገቡን በሰውና በሰነድ ማስረጃ አጣርተን ለሚመለከተው የህግ አካል ለመላክ እንችል ዘንድ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 59/1 መሰረት የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠን ሲል የፌደራል ፖሊስ የጠየቀ ቢሆንም ክሱ ግልጽ አይደለም እና ተሻሽሎ ይቅረብ ብሎ ትዕዛዝ የሰጠው ችሎቱ ተሻሽሎ ቀርቧል የተባለውን ክስ ከተመለከተ በኋላ ለጥቅምት 30/2015 ከሰዓት ክሱን ለመስማት ቀጠሮ መስጠቱን ጠበቃ ሀብተ ማርያም ጸጋዬ ገልጧል። ተሻሽሎ ቀርቧል የተባለውን የጊዜ ቀጠሮ ማስፈቀጃ ክስን እንዴት አገኘህው ሲል አሚማ የጠየቀው ጠበቃ ሀብተ ማርያም ጸጋዬ በበኩሉ ተጠርጣሪዎች በየት አካባቢ ሲንቀሳቀሱ እንደነበሩ ከመግለጽ ያለፈ የተጨመረበት ነገር የለም ሲል አለመሻሻሉን ጠቁሟል። የአብን የምዕራብ ጎጃም ዞን ጽ/ቤት ሠራተኛ ወጣት ብሩክ አያልነህ ከወንድሙ እና ከእህቱ አማኑኤል አያልነህ እና ሔለን አያልነህ ጋር ጥቅምት 23/2015 ፍኖተ ሰላም ላይ ከታፈኑ በኋላ ጥቅምት 24/2015 ረፋድ ላይ እህቱ ሔለን የተለቀቀች ሲሆን ብሩክ እና አማን ከፍኖተ ሰላም ወደ ባህር ዳር ተወስደው ቀበሌ 14 በ8ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው በነበረበት ወቅት ብሩክ አያልነህን ነጥለው ወደ አዲስ አበባ ማምጣታቸው ይታወሳል። አሚማ እንዳጣራው በባህር ዳር 8ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው የብሩክ አያልነህ ታላቅ ወንድም አማኑኤል አያልነህ በሰው ዋስ ተፈቷል። ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ የተደረጉ 6ቱ ተጠርጣሪዎች ለውጥ ይመጣል በሚል የህወሓት መራሹን ስርዓት ፊት ለፊት በመታገላቸው በተለያዩ ጊዜያት ለረዥም እስር የተዳረጉ እና አያሌ ግፍ እና በደልን ያሳለፉ ናቸው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply