You are currently viewing ከአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ:- ነሐሴ 23/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) መዘናጋት ሳይኖርብን የመጣብንን በጋራ እንመክት የአማራ ህዝብ አሁን እየደረሱበት ያሉ…

ከአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ:- ነሐሴ 23/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) መዘናጋት ሳይኖርብን የመጣብንን በጋራ እንመክት የአማራ ህዝብ አሁን እየደረሱበት ያሉ…

ከአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ:- ነሐሴ 23/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) መዘናጋት ሳይኖርብን የመጣብንን በጋራ እንመክት የአማራ ህዝብ አሁን እየደረሱበት ያሉትን ችግሮች እያሳለፈ ያለው ለስልጣን ማራዘሚያ ጨቋኝ ነው፣ገዢ መደብ ነው፣ ታሪክ እምነት አጥባቂ ነው በሚል ስም በሰጡት ምዕራባውያን እና በስራ አስፈፃሚያቸው በአሸባሪው ትህነግ ወያኔ ነው።ህውሀት የአማራን ህዝብ ታሪካዊ ጥላት በማድረግ እምነቱ፣ባህሉ፣ታሪኩ እንዲጠፋ የማድረግ ስራ በስልጣን በቆየባቸው ጊዜም ሰርቷል። በ1992 ዓ.ም በተቆጠረው የህዝብ ቆጠራ እስታቲክስ ተሰርቶ 2.5 ሚሊየን ህዝብ ከምድረ ገፅ አጥፍቶ በአለም የሰበአዊ መብት ድርጅት ሲጠየቅ በመሪው በአቶ መለስ ዜናዊ በኤች አይ ቪ የሞቱ ናቸው የሚል ቀልድ እንደተቀለደ የሚታወቅ ነው በታሪክ ማህደ…ር የሌለ ተረት ተረት በመፋጠር በህዝቦች መካከል የጥላቻ ዘር ሲዘራ የነበረ አንድን ትምክተኛ ሌላውን ጠባብ እራሱን ቅድስ አድርጎ የሚቆጥር ሲሆን የግፍ ቀንበሩ በዝቶ በኢትዮጵያውያን የጋራ ትግል ከስልጣን ቢወርድም እኔ የማላስተዳድራት ሀገር አትኖርም በማለት ከአራት ኪሎ ከወጣ በኋላም ትግራይ መሽጎ ለሀገር ሉዓላዊነት ዳር ድንበር የሚጠብቅ፣አዛውንቶችን የሚያግዝ አጋዥ የሌላቸውን ህፃናት የሚረዳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ላይ የሀገር ከሃዲነቱን በትር ሰነዘረ ነገር ግን በጀግናው መከላከያ በአማራ ልዩ ሃይል እና ፋኖ ተደምስሶ “የንስሀ ጊዜ ቢሰጠውም” የአማራ ህዝብ ላይ የምናወራርደው ሒሳብ አለ በማለት አማራ ህዝብ ላይ የጥላቻውን ነጋሪት በድጋሜ ይጎስም ጀመረ በብዙ መስዕዋትነት ድጋሜ ወደመጣበት ሸኝቶ ይቅር ባዩ ህዝባችን የተራቡትን አጠጥቶ የቆሰሉትን አክሞ በህዝቦቹ መካከል ምንም አይነት ችግር እንደሌለ እና አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ይቅር አለው።ነገር ግን” እፀድቅ ብዬ ባዝላት ተንጠልጥላ ቀረች”! እንደሚባለው ህዝባችንን በጠላትነት ፈርጆ ለሶስተኛ ጊዜ ጥቃቱን ፈፅሟል። ስለዚህ ይህን አሸባሪ ቡድን ለማጥፋት የአማራ ህዝብ በአንድነት መረባረብ ይኖርበታል። ከዚህ በፊት ይህ አሸባሪ ቡድን የፈፀማቸውን ጥቃቶች ግፎች የምናውቃቸው ናቸው። የአማራን ህዝብ ተደራጅ የሚሉ የነቁ የምንላቸውን የአማራ ልጆች የአፄውን ስርዓት ናፋቂ፣ ትምክተኛ ነፍጠኛ እያለ የማሸማቀቅ ስራ ሲሰራ ሲያስር ሲገል የኖረ አሸባሪ ቡድን ነው። የመጣው ሁሉ አማራን ጥላት በማድረግ የመከራ ዶፍ እየወረደበት የሚገኘው በተዘራው የህውሀት የአረም ዘር መሆኑን እየገለፅን ይህን ሁሉ መከራ፣ ስቃይ፣ ሞት፣ መፈናቀል፣ሀብት ንብረቱ መውደሙ እየደረሰበት ያለው፦ ጎጃም፣ጎንደር፣ወሎ፣ሸዋ ብሎ ሳይሆን አማራ በሚለው የዘር ግንድ በመሆኑ መረዳት ይኖርብናል። ስለዚህ ሁሉም አማራ በሀገር ውስጥ ይሁን ከሀገር ውጪ በአንድነት በጋራ መቆም የመጣውን ወራሪ መመከት ወደ መጣበት መመለስ አማራጭ የሌለው መንገድ ነው።የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ ከትግራይ ህዝብ ጋር ምንም አይነት ችግር አልነበረበትም አይኖርበትም፤ ይልቁንም ተመጋጋቢ የሆኑ በርካታ እሴቶች ያላቸው ህዝቦች ናቸው። ነገር ግን የአማራን መጥፋት የሚፈልገውን ህውሃት በህዝባችን ህልውና ላይ የመጣ በመሆኑ ማህበራችን የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ከፋኖ፣ ሚኒሻ፣ ከአማራ ልዩ ሃይል እና ከሀገር አለኝታው መከላከያ ጎን ማንኛውም የኢትጵያ ህዝብ እንዲቆም ጥሪ እናስተላልፋለን። “ውርደት ለመሸከም የሚችል ትካሻ የለኝም”! የሚሉት የእምዬ ልጆች፣ቤተሰብ ከሀገር አይበልጥም የሚለው የበላይ ዘለቀ ልጆች፣የአንድነት ፈር ቀዳጅ የወንዶቹ ቁና የጀግናው አፄ ቴዎድሮስ ልጆች መካሪ አስታራቂ የሆኑት የሺህ ሁሴን የንጉስ ሚካኤል ልጆች የበረሃው መብረቅ የኡመር ሰመትር ልጆች የአባጅፋር ልጆች የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ እና ሀገርን በእጅ አዙር ለምዕራባውያን የማስገዛት አላማን እምቢ ብለን በጋራ እንመክት ማለት እንወዳለን። በዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ለወደፊት ተፅፎ የአንድ ሀገር ዜጎች ወንድማማቾች እርስ በእርሳቸው ተጠፋፍተው ነበር በመባል ታሪካችን እንዳይፃፍ በማወቅም ባለማወቅም የዚህ ቡድን ተባባሪ የሆኑትን ህፃናት፣አዛውንቶች የተማረኩ ወታደሮች በኢትዮጵያዊነት ለዛ እንደ አባታችን ዳግማዊ ምኒልክ በይቅር ባይነት ልንይዛቸው ይገባል።የአባታችን ልብ ለጣሊያን ራርቶ ምርኮኛን ተንከባክቦ ሸኝቶ ነበርና።በመጨረሻም የትግራይ ተወላጆች በሀገር ውስጥ ከሀገር ውጭ የምትኖሩ ከእውነት ጎን በመቆም በህዝባችሁ፣ በወገናችሁ እና በሀገር ላይ የሚደርሰውን ጥፋት የዛሬ 20 ዓመት ወደኋላ ቀርተው የሚያስቡ ከራሳቸው ውጭ ለህዝብ ደንታ ለሌላቸው የአሸባሪው ቡድን አባላት መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ታሪካዊ ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ በማለት ማሳሰብ እንወዳለን። የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ! 👉ድል ለእኩልነት 👉 ድል ለነፃነት 👉 ድል ለፍትህ ጉዞ ምኒልክን ይዞ ! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!! ነሐሴ 23/2014 ዓ.ም ደ/ብረሃን ኢትዮጵያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply