ከአማራ ወጣቶች ማህበር በደምበጫ የተሰጠ መግለጫ መስከረም 22/2015 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) የአማራ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ በሀገር ገምባታ ሂደት የጎላ ሚና የተጫወተ ታላቅ ህዝብ ነው ይህ ህዝ…

ከአማራ ወጣቶች ማህበር በደምበጫ የተሰጠ መግለጫ መስከረም 22/2015 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) የአማራ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ በሀገር ገምባታ ሂደት የጎላ ሚና የተጫወተ ታላቅ ህዝብ ነው ይህ ህዝብ የራሱ የሆነ ባህል፣ ሀይማኖት ፣ወግ፣ ሰርዓት እና የአኖኗኗር ዘይቤ ያለው ሀገር ወዳድ ህዝብ ነው… የአማራ ህዝብ በኪነ ህንፃ በሰነጥበብ በትምህርት እንዲሁም በሌሎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተግባራት ትልቅ ሚና የተጫወተ እና እየተጫወተ ያለ ህዝብ ነው። በኪነ ህንፃው እረገድ እንደነ ፣አክሱም ላሊበላ፣ ፋሲል ግምብ ወ.ዘ.ተ አሻራውን አኑሮ ላለው ትውልድ ጠብቆ እያሸጋገረ ይገኛል። በሰነ ጥበቡ ዘርፍም በሙዚቃ፣ ፣በተውኔት፣በሰነግጥም፣በሰነፅሁፍ እረገድ ያደረገው አሰተዋፆ ታላቅ ነው። የአማራ ህዝብ ሀገር በጠላት በተወረረችባቸው ጊዚያት ታላቅ መሰዕዋትነት በመክፈልና ድልንም በማሰመዝገብ ከሌሎች እህት ወንድሞች ጋር የኖረ ህዝብ ነው። በመሆኑም ከ 16ኛው መቶ ክፍለዘመን ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት ትላልቅ ፈተናወችን እያሰተናገደ የመጣ ቢሆንም ካለፉት ሃምሳ አመታት ይህ ፈተና በጅጉ በዝቶበት የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈመበት ይገኛል። ባለፉት ሃምሳ አመታት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ጅምላ ጭፍጨፋ፣መፈናቀል፣እንግልት፣የንብረት ውድመት እያሰተናገደ ይገኛል። ሰለሆነም በገዛ ሀገሩ ባይተዋር ሁኗል። የህፃናት መታረድ፣የነፍሰጡሮች መከራ፣ በሴት እህቶቻችን ላይ የሚፈፀመው ኢ-ሰብዓዊድርጊት፣የቤተሰብ መበተን፣ ወ.ዘ.ተ ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለይም ባለፉት አራት አመታት በተቀናጀመልኩ እየታሰረ ይገኛል። በአንድ በኩል ይህን ህዝብ ለመታደግ የሚነሱ ቁርጠኛ ልጆችን በመሰዋት ፣በማሰርና በማንገላታት፣በሌላ በኩል የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅምን በመንፈግ የአማራ ህዝብን መከራ ከድጡ ወደ ማጡ አድርገውታል። በተለይም ደግሞ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች የሆኑትን ጀግኖች የመሰዕዋት በግ አድርጎ የሚያቀርበው ሆዳምና ሰልጣን ፈላጊ አማራወች መሆናቸውን ሰናሰብ ልቦናችን በጥልቅ ያዝናል። ህዝቡን በሀገር ደረጃ ከሚደርሰበት ጅምላ ግድያና ጅምላ መቃብር ለመታደግ በቂ እንቅሰቃሴ ማድረግ ያልቻለው የአማራ ክልል መንግሰት! የደምበጫን ወጣት ባህር ዳር እንዳይገባ መከልከል የወለጋው ጨፍጫፊ አራጅ አሳዳጅ እንጅ አማራን ወክሎ የሚሰራ መንግሰትም አለ ብለን አናምንም። አሁንም አንድ ጥያቄ አለን ይህን የምታሰፈፅሙ የውሰጥ ባንዳዎች ጥቁር አሻራችሁ ይታያችኋል ? የአማራ ህዝብ ምልክት የሆነውን ፍኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን እንዳለፉት ጀግኖቻችን ልትቀሙን ሰትቋምጡ መክረማችሁ ይታወቃል። ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል ነው እና የመግለጫ እና የዜና ድንፋታችሁ በሁሉም አማራ ህዝብ ላይ እንደሆነ እናንተም ታውቃላችሁ። ሰለሆነም በመላው የ አማራ ወጣት እራሱን በማደራጀት የህልውና ትግሉን እንዲቀላቀል እናሳሰባለን። እኛ የ አማራ ወጣቶች በደምበጫ፥ 1 አረበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴን እና ሌሎች ውድ የአማራ ልጆች በአሰቸኳይ እንዲፈቱ እናሳሰባለን ። 2 ሀገር እሚያፈርሱትንና በህዝባችን ላይ ጅምላ ጭፍጨፋ ያወጁብንን ከመታገል ይልቅ ለህዝባችን የቆሙትን ምልክቶቻችንን መሰዋትና ማንገላታት መቆም አለበት። 3 ለህዝባችን ተቆርቋሪ የሆናችሁ አመራሮች ባለድርሻ አካላት ህዝባችሁን በማሰተባበር ህልውናችንን እናሰቀጥል። 4 መላው የዲያሰፖራ አባላት ይህን ትግል ከአማራ ህዝብ ጎን በመቆም እንድትደግፉንና በጋራ ለህዝባችን እንድንቆም እንጠይቃለን። 5 የአማራ ህዝብ እሴት መጣሰ ምክንያት የሆነው የክልሉን መንግሰት አምርረን እናወግዛለን። በመጨረሻም ዘመነ የዘመነው የአማራ ትውልድ ምልክት ነው። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply