
ከአማራ ወጣቶች ማህበር የተላለፈ መልዕክት‼️ ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በአማራ ክልል በሸዋ አጣዬ እና አካባቢው ማለትም ጀውሃ፣ሸዋሮቢት እና አካባቢው በአማራ ልዩ ሀይል ላይ ሆን ተብሎ በተቀነባበረ መልኩ ጥቃት ተፈፅሟል::በዚህም ከፍተኛ ቁጭት ተሰምቶናል ። በጫካው የኦነግ ቡችሎች እና በመንግስታዊው የኦነግ ሀይሎች በተቀነባበረው ሴራ የአማራ ልዩ ሀይል መሳሪያ እንዲጠረንፍ ከአስደረጉ በኋላ በተናበበ መልኩ ጥቃቱ ተፈፅሟል በጥቃቱ የተወሰኑ የልዩ ሀይል አባላት ተሰውተዋል። ይህም ሆኖ እያለ ጥቃቱን ወደ ህዝብ አዙረው በእጅ አዙር ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ የመንግስት አመራሮች የሚደገፈው የኦነግ ሀይል በህዝብና በፀጥታ አካላት እንዲሁም ፋኖ ላይ እያደረሰ ያለው ጥቃት አራተኛ ቀኑን አስቆጥሯል። ይህ ጥቃት የሸዋ አማራን ብሎም መላ የአማራን ህዝብ እረፍት ለመንሳት እየተሰራ ያለ ፣ከዚህ ቀደም ታቅዶ በመዋቅር በሰፊው ሲሰራ የነበረ አማራን የማጥፋት ስራ በተስፋፊው የኦነግ ከፍተኛ ባለስልጣናት እየተደገፈ ላለፉት 5(ዓምስት ዓመታት) የቀጠለ ፤በችግር ላይ ችግር እየተደራረበ ሰላም መንሳቱ በኢኮኖሚ ማዳከሙ ቀጥሏል። ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ላይ የተፈፀመውን ክህደት ፣እጅግ አስነዋሪ ተግባር ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ታላቅ አገራዊ አጀንዳ ለማስቀየስ ሌላ የአጀንዳ ማስቀየሪያ ጥቃት ነው። ይህ የመንግስት እንዝላልነት እና የአማራን ህዝብ የማዳከም ተግባር በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጭምር የተደገፈ መሆኑን ተረድተን መላው የአማራ ህዝብ ከወንድሞቻችሁ ከአማራ ልዩ ሀይል ፣ከአማራ ፋኖ ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታደርጉ እየጠየቅን የአማራ ወጣቶች ማህበር ከወንድሞቻችን ጎን የቆምን ፣ጉዳታችሁ ጉዳታችን መሆኑን እንገልፃለን። አማራነት ወይ ሞት‼️ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post