ከአማራ የተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዘማቾች አሸባሪዎችንና ወራሪዎችን ለመመከት ብሎም ለመደምሰስ ወደ ግንባር እየተንቀሳቀሱ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 26…

ከአማራ የተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዘማቾች አሸባሪዎችንና ወራሪዎችን ለመመከት ብሎም ለመደምሰስ ወደ ግንባር እየተንቀሳቀሱ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 26 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአማራ የተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዘማቾች አሸባሪዎችንና ወራሪዎችን ለመመከት ብሎም ለመደምሰስ ወደ ግንባር እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ተገልጧል። እንደአብነትም ከደቡብ ጎንደር የተወጣጣው ሕዝባዊ ሠራዊት የቀረበለትን የክተት ጥሪ ተቀብሎ ወደ ግንባር መክተቱ ተገልጧል። ማንነቱን፣ ባሕሉን፣ ሀገሩን እና ክብሩን ዳግም ለባንዳ አሳልፎ ላይሰጥ ቃል የገቡ ዘማቾች ወደ ግንባር ሲያቀኑ ደማቅ ሽኝት ተደርጎላቸዋል። ሀገርን እና የአማራን ሕዝብ ነጻ ለማውጣት የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ተቋቁሞ በጽናት መዋጋትና ማሸነፍ ብቸኛው አማራጭ ነው መሆኑም ተመላክቷል። የሁሉም ወረዳ የፖለቲካ መሪዎች፣ ሚሊሻዎች፣ የፖሊስ አባላት እና ልምድ ያላቸው ምልስ የሠራዊት አባላት የመሪነት ሚናውን በአግባቡ እንደሚወጡም ጥሪ ቀርቧል። “ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል ደጃችን እስኪደርስ አንጠብቅም፤ ካለበት ሄደን እናጠፋዋለን” ያሉት ደግሞ የሰሜን ጎንደር ዞን ዘማቾች ናቸው። ዘማቾቹ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በሕዝቡ ላይ የጅምላ ጭፍጨፋና ዘረፋ እየፈፀመ የሚገኘውን ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል እስከ መጨረሻው ለማጥፋት ቆርጠው መነሳታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ “በደባርቅና ዳባት ወረዳ የተዋጋነው ከተማችንን ከዝርፊያ፣ ሕዝባችንን ከጅምላ ጭፍጨፋ ለመታደግ ነበር፤ አሁን እየዘመትን ያለነው ግን ጠላትን እስከመጨረሻው አጥፍተን ኢትዮጵያን ነፃ ለማውጣት ነው” ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ❝ጠላታችንን ሳንቀብር ላንመለስ ቃል ገብተን ተነስተናል❞ ሲሉ የሸዋ ዘማቾች አቋማቸውን አስታውቀዋል። ከሰሜን ሸዋ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ ዘማቾች ከጠላት ጋር ለመፋለም ነው ወደ ግንባር የተሸኙት፡፡ “አማራን በማጥፋት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እኩይ ተግባሩን እየፈጸመ ያለውን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ለመደምሰስ ከፍተኛ ተጋድሎ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በተያያዘ “አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ኀይልን በከፍተኛ ሕዝባዊ ማዕበል እየደመሰስነው ነው” ሲሉ የአበርገሌ ወረዳ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የዋግና አካባቢው ነዋሪዎች ዛሬም እንደ ትናንቱ ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር በመሆን በጠላት የተለመደውን ጀብድ እየፈጸሙ መሆናቸውን ተጠቅሷል። የአበርገሌ፣ የፃግብጂ፣ የዳህና፣ የሳህላ ሰየምት፣ የዝቋላ፣ የሰቆጣ እና የጋዝጊብላ ወረዳ ነዋሪዎች በየአቅጣጫው እየተመመ ከሚገኘው ወገን ጋር በመሆን አሸባሪውን ኀይል እየቀጡት ስለመሆኑ ተጠቁሟል። ለዘገባው አሚኮን በምንጭነት ተጠቅመናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply