ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ አዴሃን የተሠጠ መግለጫ       //       አሻራ ሚዲያ   ጥቅምት 27/2013ዓ.ም       ባህርዳር……

ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ አዴሃን የተሠጠ መግለጫ // አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 27/2013ዓ.ም ባህርዳር……

ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ አዴሃን የተሠጠ መግለጫ // አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 27/2013ዓ.ም ባህርዳር… // የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዛሬ አባል በሆነው ፓርቲዎች ስም ያወጣውን መግለጫ የማናውቀው እና መግለጫውን ለመስጠት የተደረገ ውይይት ላይ ያልተገኘን እና የኛን አቋም የማያፀባርቅ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን። የጋራ ምክር ቤቱን የተቋቋመው በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚኖረውን ግንኙነት እና በተናጠል የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች የሚገዛ የአሠራር ሥርዓት ቃል ኪዳን ሰነድ አንቀፅ 17.3 እና 17.4 በግልጽ እንደሚያስቀምጠው የጋራ ምክር ቤቱ የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች ላይ በስምምነት (Consensus) ለመወሰን ተገቢውን ሁሉ እንደሚደረግ ነገር ግን ይህ የማይሳካ ከሆነ በውይይቱ የተገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች 3/4ኛ ድምፅ ውሳኔ ይሰጣል። ይላልይሁን እንጅ ዛሬ በጋራ ምክር ቤቱ ስም የተላለፈው መግለጫ ይህን ስምምነት የጣሰ እና የምክር ቤቱ አባል የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት ሳያደርጉበት የወጣ በመሆኑ እኛም የማናውቀው በመሆኑ አንቀበለውም። ጥቅምት 27 2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply