ከአማራ ፋኖ በባህር ዳር የተላለፈ መልክት:- መከፋፈሉ ለምን አላም እንደሆነ እናውቃለን ❗️ ፍትህ የሚሰፍነው መላው የአማራ ፋኖዎች ሲለቀቁ ነው ። ሰላማዊ ትግሉ ይቀጥላል ።… ======…

ከአማራ ፋኖ በባህር ዳር የተላለፈ መልክት:- መከፋፈሉ ለምን አላም እንደሆነ እናውቃለን ❗️ ፍትህ የሚሰፍነው መላው የአማራ ፋኖዎች ሲለቀቁ ነው ። ሰላማዊ ትግሉ ይቀጥላል ።… ======================= በእነ ፋኖ ቴዎድሮስ ጌታቸው መዝገብ የተከሰሱት ዘጠኙ ተከሳሾች ዛሬ ተፈተዋል ‼️ ~~ በእስር ላይ የነበሩት የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አመራሮች በእነ ፋኖ ቴዎድሮስ ጌታቸው መዝገብ የሚገኙት ፦ 1).ቴዎድሮስ ጌታቸው 2).መንግስቱ አማረ 3).ማንችሎት እሱባለው 4).ኖላዊት ይልሃል 5).ሀብታሙ ማንደፍሮ 6).ያሬድ መንግስቱ 7).ምትኩ ጠብቀው 8).ያስችላል ጌጤ 9).ኃይለማሪያም ተባባል የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኞች በ20 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ከወሰኑበት እና የዋስትና ገንዘቡ ከተከፈለበት ካለፈው አርብ ዕለት ጀምሮ ከማረሚያ ቤቱ እንዲወጡ የተጠየቁ ቢሆንም ፤እኛ በእነ ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ መዝገብ የሚገኙ መላው ፋኖዎች የማይለቀቁ ከሆነ አንወጣም በማለት እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ አብረው ቆይተዋል ። በዛሬው ዕለት ግን የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አመራሮች ከእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ ጋር ተነጋግረው ከሰባታሚት ማረሚያ ቤት ወጥተዋል። ነገር ግን በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ የሚገኙት አስራ አራቱ(14) ፋኖወች ግን አልወጡም።በዚህ መዝገብ የሚገኙት የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ መሰረት በ25 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ብይን የተሰጠ ቢሆንም የፌዴራሉ መንግስት እኔ እፈልጋቸዋለሁ በማለት አፍኖ ለመሰውድ ባለፉት ቀናት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ መቆየቱ የሚታወቅ ነው ።ይሁንና በታራሚዎች ተጋድሎ እና ከማረሚያ ቤቱ ውጭ በተገኘው የከተማችን ብርቱ ወጣቶች አፍኖ ለመውሰድ የተደረገው ጥረት አልተሳካም ። ያልተፈቱት 14ቱ ፋኖወች ሳይለቀቁ ሰላማዊ ትግላችንን አናቆምም ያሉት የባህርዳር ወጣቶች እና ፋኖወች የክረምቱ ብርድ እና ዝናብ ሳይበግራቸው በሰባታሚት ማረሚያ ቤት በር ላይ ናቸው። ትግሉ ይቀጥላል ። የትግላችን መዳረሻ የአማራ ነፃነት ነው‼️ ሰ.ሜሪካ :- ሐምሌ 25/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply