ከአማራ ፋኖ በባህር ዳር የተሰጠ መግለጫ የብአዴን የአማራ ፋኖን ማሳደዱ እንቅስቃሴ በቃ ሊባል ይገባል ==================== በዛሬው ዕለት የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ለማድረግ የ…

ከአማራ ፋኖ በባህር ዳር የተሰጠ መግለጫ የብአዴን የአማራ ፋኖን ማሳደዱ እንቅስቃሴ በቃ ሊባል ይገባል ==================== በዛሬው ዕለት የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ለማድረግ የታሰበውን ጠቅላላ ጉባኤ በአድር ባዩ ፤በአጎብዳጁ ብአዴን ተከለከለን ።… የባ/ዳር ከተማ አስተዳደር ሰላም እና ደህንነት ፅ/ቤት እውቅና ሰጦን አስፈላጊውን የድጋፍ ደብዳቤውን አስገብተን ፍቃድ አግኝተን ፤አስፈላጊውን ቅደመ ዝግጅት ፤ጥሪ አድርገን በዛሬው ዕለት ጠዋት ወደ ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ስንደርስ የገጠመን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአድማ ብተና ፣የፓሊስ ሃይልና እና የደህንነት ሰዎች አሰልፎ መሰብሰብ አትችሉም ተብለናል ።የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ኮሚቴ እና አባላትም ነገሮችን በሰከነ መንገድ በመመልከት ወደ አላስፈላጊ ግጭት ባለመግባት ፤ ከወንድሞቻችን ከአማራ ልዩ ሃይል አባላት ፤ከአድማ ብተና አባላት እና ከባህር ዳር ከተማ የፓሊስ አባላት ጋር ለመፍጠር ታስቦ የነበረው ብአዴንዊ ተንኮል ፤ብአዴን ሰራሽ ወንድም ከወንድሙ ጋር የማጋጨት የቆዬ ውርስ ባህል እና ብአዴናዊ አድርባይነት ፥ሎሌነት ተግባርን በመረዳት እኛ ከወንድምቻችን ጋር አንጋጭም እናንተን ያዘዘው ማን ነው? በማለት ነበር ጥያቄ ያቀረብነው ። በምላሹም ከበላይ አካል ታዘን ነው የሚል ተለምዷዊ ምላሽ ነበር ያገኘነው ።ነገር ግን እኛ ለማጣራት እንደሞከርነው ይህንን ትዕዛዝ ያዘዘው #መንገሻ አውራሪስ የተባለ ግለሰብ እንደሆነ ተረድተናል ።በተደጋጋሚ የተከለከለበት ምክንያት ለመጠየቅ የእጅ ስልኩ ላይ በመደወል ለመጠየቅ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም ። በመሆኑም የአማራ ፋኖ በባህር ዳር በጋሸና ግንባር ታላቅ ጀብድ የፈፀመ ፤በከተማው አስተዳደሩ በክብር ተሸኝቶ በድል የተመለሰ ሰራዊት ፤ምንም ዓይነት የስነ ምግባር ግድፈት የሌለበት የፋኖ አባላት ሆኖ ሳለ ስብሰባ ማድረግ አትችሉም በማለት ተከልክለናል ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደጋጋሚ በጎጃም ፥በወሎ የሚደረገው በፋኖ ላይ የሚደረግ ማዋክብ ፣እስር እና ማሳደድ ፤እንዲሁም የፋኖ ስም ማጥፋትና ፍረጃ የብአዴን አድር ባዮች ተግባር ከትላንቱ የቀጠለው ሎሌነት እና አሽከርነት እንደሆነ ተገንዝበናል ።ይህም አድርባይነት ፣አሸከርነት እና ለመጣ ለሄደው አጎብዳጅነት የአማራን ህዝብ ምን ያህል መከራ ውስጥ እንደከተተው የአደባባይ ሃቅ ነው ።የአማራ ፋኖ በባህርዳር በህዝባችን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ እንግልት ፤የህዝባችን መፈናቀል ፥ ስደት ፤በደምና አጥንታቸው ቀደምት አባቶቻችን ባቆዩልን ምድር ባይተዋር ፣ተሳዳጅ ፣ተቅበዝባዥ መሆን መነስኤው የእናንተው አድርባይነት እንደሆነ ከተገነዘብን ሰንብተናል ።ከዚህ በኃላ ይህ የእናንተ አድርባይነት ፣ሎሌነት እና ለመጣ ለሄደው አሽከርነት የሚሸከም ፣የሚታገስ የአማራ ፋኖ ሰራዊት እንዲሁም የአማራ ህዝብ አይኖርም ። በመሆኑም ለመላው የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላት እና ደጋፊዎች ፤ለመላው የባህርዳር ከተማ ህዝብ እንዲሁም ለመላው የአማራ ህዝብ ከዚህ በኃላ ለምናደርገው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከጎናችን እንድትሆኑ ፤ለምናደርገው ሁለን አቀፍ ትግል ፥ መሬት ላይ የወረደ ትግል ከጎናችን እንድትሆኑ በማለት ጥሪያችን እናስተላልፋለን ። በመጨረሻም ለመላው የአማራ ልዩ ሀይል ፣አድማ ብተና እና ፓሊስ በሙሉ እኛ ከእናንተ ከወንድሞቻችን ጋር ምን አይነት ፀብ የለንም ፤እናንተን ከእኛ ጋር ለማጋጫት ከሚታትሩት ጋር እንጅ ፤ስለሆነም ለምናደርገው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከጎናችን ትሆኑ ዘንድ በአማራዊ ወንድምነት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። አንድ አማራ አንድ አማራ ፋኖ

Source: Link to the Post

Leave a Reply