#ከአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ! የአማራ አርበኝነት ተጋድሎ (ፋኖነት) አንዳንድ የታሪክ ድርሳናት በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን በአፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት የተጀመረ፣…

#ከአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ! የአማራ አርበኝነት ተጋድሎ (ፋኖነት) አንዳንድ የታሪክ ድርሳናት በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን በአፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት የተጀመረ፣ ለሀገሩ ለህዝቡ ነፃነትና ሉአላዊነት በራሱ ወኔና ፍፁም ፍላጎት ትጥቁንና ስንቁን አሟልቶ በነፃ ቤዛ ለመሆን የትጥቅ ትግል የሚያደርጉ ጀግኖች መጠሪያ “አርበኛ-ፋኖ” ይሰኛል፡፡ የፋኖ አርበኝነት በሀገራችን ኢትዩጵያ የውጭና የውስጥ ወራሪና ግፈኛ ቅኝ ገዥዎችን እና የሀገር ጠላቶችን የእብሪት ክንድ አልፈስፍሶ በማጥፋት የሀገርንና ህዝብን ክብርና ነፃነት የሚጠብቅ ስለመሆኑ የሀገራችን ታሪክ ያረጋግጣል፡፡ ባለፉት 30 ዓመታት የሀገሪቱን መንበረ ስልጣን በሀይል መቆጣጠር የቻለው ግፈኛውና ጨቋኝ አድሏዊ የአፓርታይድ አገዛዝ ህዝባችን ላይ የጫነው ትህነግ እያረደሰ ያለውን ከፍ…ተኛ ግፍና በደል ለመቀልበስ የፋኖ የአርበኝነት ተጋድሎና የወጣቶች የመብት ጥያቄ ከፍተኛ ሚና እንደነበረው እሙን ነው፡፡ በቅርብ ወራትም ከማዕከላዊ መንግስት ፈላጭ ቆራጭ ስልጣን በህዝብ ትግል ገሸሽ የተደረገው ግፈኛው ትህነግ ሀገር ለማፍረስ፣ ለመዝረፍ፣ እናቶችን ለመድፈር፣ ዜጎችን ለመግደል፣ለማፈናቀልና የአካልና የስነ-ልቦና ጉዳት ለማድረስ ራሱን አደራጅቶ ወደ መሃል ሀገር ወረራ በፈፀመበት ጊዜ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች በሁሉም ጦር ግንባሮች ተሰልፈው ከጠላት ጋር በመፋለም ከሌሎች የመንግስት ጥምር የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን እጅግ አኩሪ ድል በመጎናፀፍ ሀገርን ከመበተን ህዝቦቿንም ከስቃይና ውርደት መታደግ መቻሉ የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡ በዚህም ከህዝብ አብራክ የወጣው የፋኖ አርበኝነት የመንፈስና የስነ-ልቦና ውቅር ከዘመን ወደ ዘመን ከትውልድም ወደ ትውልድ እሴቱንና ታሪኩን ጠብቆ እያስተላለፈ ለሚገኘው ለመላው ህዝባችን በተለይም ለአማራ ህዝብ ምስጋና ያቀርባል፡፡ሆኖም የፋኖ አርበኝነት ትግል በተበጣጠሰ ሁኔታ በየአካባቢው በጎበዘ አለቃ የሚመራና ያልተማከለ መሆኑ ለሀገርና ህዝብ መስጠት የሚገባውን ሁሉ ለመወጣት ተግዳሮት ሁኖ እንደቆየም ይታወቃል፡፡ ተበትኖ የቆየው የአማራ ፋኖ አንድነትን ለማምጣትና የሰራዊቱንና የደጋፊውን እንዲሁም ግልፅ የአላማ አንድነት ለማፅናት በርካት ተግባራት እየተካሔደ ያለበት ወቅት ላይ ስንሆን በጎንደር የሚገኙ 5/አምስት/ ዞን አስተዳደር ስር እና በጎንደር ከተማ አስተዳደር ስር መቀመጫቸውን ያደረጉ ፋኖዎችና መሪዎቻቸውን ውህደት በመፈፀም ከዛሬ ጀምሮ “የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር” የተሰኘ አንድነት ላይ መድረሳችንን እያበሰርን ውድ የሀገራችን ህዝቦች፣ መላው የፋኖ ዓባላትና የትግሉ ቤተሰቦች በቀጣይ እንደ አማራ ወጥ የሆነ አንድነት ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተረድተን እጅግ በርካታ አባላት ያለው የጎንደር ቀጠና ፋኖ በአንድነት ተዋቅሮ መቅረቡን ተገንዝባችሁ ሁሉም ወገን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር እንዲደግፍና በዓባልነት ተመዝግቦ መታገል እንደሚችን እናሳውቃለን፡፡ ፋኖ የውስጥ የአላማና የአደረጃጀት አንድነቱን በማረጋገጥ የጠላትን ወረራ ለማምከንና በጠላት ወረራ ስር የሚገኙ ህዝባችንና አካባቢዎች ነፃ ለማውጣት የሚረዳ መሆኑን ስለታመነበትና ህዝባችን ፋኖ አንድ ይሁንልን ሲል በተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ለወራት የውስጥ የውይይት ሂደቶችን በማለፍ ሙሉ መግባባት ላይ በመደረስ ወጥ በሆነ ተቋማዊ የፋኖ አንድነት ውህደት ላይ በመድረሱ መላው የአማራ ህዝብና የሀገራችን ልጆች፣ ዓባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ/ እንኳን ደስ አለን/ እያልን በቀጣይ በአባላት የስነ-ምግባርና የሙያ ጥራት ላይ ትኩረት አድርገን ህዝባችንና ወዳጆቻችን እንዲሁም ሀገራችን በሚፈልጉት ትክክለኛ ቁመና ላይ ለመድረስ አበክረን እንደምንሰራ ቃል እየገባን የወገናችን ሙሉ ድጋፍ እንዳይለየን አደራ እንላለን፡፡ የአማራ ፋኖ በሚያደረገው የህልውና ጦርነት ትግል እስከ ዛሬ አብረውን ተሰልፈው በጀግንነት ለህዝብና ሀገራቸው እየታገሉ ለቆዩና እየታገሉ ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይል፣ ሚሊሻ፣ ፖሊስና ህብረተሰቡ፣ ለአፋር ልዩ ሀይልና ለታጋዩ ህብረተሰብ በሙሉ ጀግኖችና አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር በጦርነቱ ላበረከቱ አባላት ሁሉ፣ ለፌደራል ሙህራን፣ መሪዎች፣ ነጋዴዎች፣ የማህበረሰቡ አንቂዎች፣ አርሶ አደሩና ተማሪው፣ ወጣቶች ዲያስፖራዎች፣ የሃይማኖት ተቋማትና ለመላው ታጋይ የህብረተሰብ ክፍል የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ምስጋና እያቀረብን በቀጣይ አብረን ለመስራት የበለጠ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡ በየትኛውም የሀገራችን ክፍል ዘርና ማንነትን መሰረት ያደረገ የንፁሀን አማራና ሌላው ወገናችን ማንኛውንም ጥቃትና ጭፍጨፋ አጥብቀን እናወግዛለን፡፡ የማንነት ተጠቂ ወገኖቻችን ደህንነት ለማስከበር ማንኛውንም መስዋትነት በመክፈል ለማረጋገጥ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሰራ እናረጋግጣለን፡፡ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ለህዝብና ለሀገር ሉዑላዊነትና ደህንነት፣ ፍታዊነት፣ ለሀገርና ህዝብ ጥቅም መከበርና የማንነትና ርዕስት መብት መከበር በቅንነት ከሚሰራ ማንኛውም አካል ጋር በአጋርነት ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡ በጠላት ወረራና ተላላኪ ተቀፅላ አሸባሪ ሃይሎች አረመኔያዊ ተግባር ህይወታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ አካላቸውን ላጡና የስነልቦና ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ወገኖቻችን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ልባዊ ሀዘኑን እየገለፀ አሁንም በጠላት ግፈኛ አሸባሪ ቡድን የግፍ ግዞት ስር ለምትገኙ ወገኖቻችን ለፀሀይ በታች ማንኛውንም ትግል በማድረግ ነፃ ለማውጣት እንደምንታገል እናረጋግጣለን፡፡ ጠላት ዝግጅት በማድረግ ለተጨማሪ ወረራ እየተዘጋጀ መሆኑን ተገንዝበን የሀገራችን ህዝቦችና መንግስት የጠላትን አስኳል ለመጨረሻ ጊዜ ለማምከን እንዲዘጋጅና የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር በተሸላ ቁመና አብሮ እንደሚሰለፍ እናሳውቃለን፡፡ 1ኛ- ሀገርና (ህዝቦቿ) ከህልውና ስጋት ፈፅሞ ያልወጣ መሆኑን ተገንዝበን የወገንን ውሳጣዊ አንድነትና ትብብር በመቻቻልና በሆደሰፊነት አንድነቱን እንድናፀና ጥሪ እናደርጋለን። 2ኛ- የአማራ የማንነትና ወሰን ጥያቄና ጠላት በወረራ በግፍ የያዛቸው አካባቢዎች ከጠላት ወረራ ነፃ እንዲወጡና አፋጣኝ ህጋዊ ውሳኔ እንዲሰጣቸው 3ኛ- በወረራ የተፈናቀሉ፣ ሰብአዊና ቁሳዊ እንዲሁም ስነ-ልቦናዊ ጥቃት የደረሰባቸው ወገኖቻችን አስፈላጊ ድጋፍ እንዲደረግላቸው 4ኛ. የአማራ ፋኖ በመምሰል የሚደረጉ የህዝብ ሞራል የማይፈቅዳቸው ኢ ሞራላዊ ስርአት አልበኝነቶችና ሃላፊነት የጎደለው የተናጠል እኩይ ድርጊቶችን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር አጥብቆ ያወግዛል፡፡ ህዝባችን የማይፈልጋቸውን ድርጊቶች የሚፈፅሙ አባሎችን ካገኘ በመተ.ደንባችን መሰረት እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እየገፅን በተከበረው የአማራ ፋኖ ጭምብል ከአላማ የወጣ እኩይ ተግባር የሚፈፅሙ የተቋማችን አባል ያልሆኑ አካሎችን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መላው ህዝባችንና የመንግስት የፀጥታ መዋቅር ትብብር እንዲያደርግልን ጥሪ እናቀርባለን። 5ኛ. በህዝባዊና ሃገራዊ ትግል የህይወትና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው፣ ለጠፉ በህይወት የሚገኙ ጠንካራ ተጋዮችና ከማሃበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወት ለተነጠሉ የአማራ ፋኖ አባሎች መንግስትና ህዝባችን አስፈላጊውን ድጋፍና እውቅና እንዲያደርጉ እናሳስባለን ፡፡ 6ኛ- በጥቃቅን ጉዳዮች ለእስር የተዳረጉ ለቀጣይ የህልውና ትግል አስፈላጊ የሆኑ ታጋዮች ይቅርታና ምህረት በማድረግ ትግሉ እንዲቀላቀሉ እንዲደረግ 7ኛ- መላው የአማራ ፋኖ አባል ለቆመለት ህዝባዊ አላማ አደራ እንዲገዛና ከአላማ ውጭ በማያገባን ጉዳይ ሁሉ ጣልቃ እንዳንገባና የአላማ ስነ ምግባር እንድንጠብቅ እያሳሰብን የመንግስት የፀጥታ ሃይልም አጋር መሆናችንን ተገንዝቦ በሚከሰቱ ጥቃቅን ጉዳዮች ሁሉ ያልተፈለገ ግጭትና ትርምስ እንዳይፈጠር ሃላፊነት ተሰምቶን በማስተዋልና በአንድነት መንፈስ የሚያጋጥሙ ጥቃቅን ክስተቶችን እድንፈታ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ 8ኛ. ጠላት በማንኛውም ጊዜ ሊወረን እንደሚችል ተገንዝበን ሳንዘናጋ ማንኛውንም ዝግጅት እድናደርግ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡ 9ኛ- በአፈሰስነው ደማችን፤ በከሰከስነው አጥንታችን ወደ መንበረ ስልጣን የመጣው መንግስት ሀ) በኦሮሚያ ክልል በግፍ የተፈናቀሉና የዘር ጭፍጨፋ እየተፈፀመባቸው ላሉ አማራዎች ወገኖቻችን ሊታደግ ይገባልለ) በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በአማራዎች ላይ የተፈፀመው ነውረኛና ዘግናኝ ግድያ እናወግዛለን የዚህ እኩይ ድርጊት ባለቤት የሆኑ አካላት በህግ ጥላ ስር እንዲውሉ እንጠይቃለን፡፡ 10ኛ- አሁናዊ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት ስናይ ትውልድ እንደማምከን የሚቆጠር እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ ስለሆነም ትምህርት ሚኒስተር የማሻሻያ መፍትሔ እንዲያቀርብ በአፅኖት እንጠይቃለን፡፡ 11ኛ- እኛ የአማራ ፋኖዎች ሀገርና ህዝብ አደጋ ላይ በሆኑበት ወቅት ጦረኛ : በሠላም ጊዜ የልማት አርበኛ መሆናችን ይታወቃል። ስለሆነም የሀገርን ዳር ድንበር እየጠበቅ ማልማት የምንችልበትን የልማት አማራጮች እንዲመቻችልን ስንል እንጠይቃለን። 12ኛ- የአማራ ፋኖ የከፈለውን ዋጋ በመካድ በአማራ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ላይ በፋኖ አባላት ላይ የሚደረግ ወከባ : ማሳደድ እና የግድያ ዘመቻ ሊቆም ይገባል። 13ኛ- በቀጣይ የመላው የአማራ ፋኖ አንድነት ተቋማዊ ውህደት እውን እንዲሆን ትብብርና ድጋፍ እንዳይለየን ጥሪያችንን እናቀርባለን። “ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታቶች !! መጋቢት 11/2014 ዓ.ም የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ኢትዮጵያ !

Source: Link to the Post

Leave a Reply