
በሺዎች የሚቆጠሩ ሕሙማንን ተቀብሎ ያስተናገደው ሆስፒታሉ፣ ባለፈው ሐሙስ በእንክብካቤው ስር የነበሩት ብቸኛ ታካሚ አገግመው ወደ ቤታቸው መሄዳቸውን አሳውቋል። የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ ታካሚው አገግመው ወደ ቤታቸው በመሸኘታቸው ላለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ የኮቪድ-19 የሕክምና ማዕከል ሆኖ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለው ሆስፒታል ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ታካሚ ውሎ አድሯል።
Source: Link to the Post