ከአራት ቀናት በኃላ ዝሆኖቹ ወደ ፓርክ ተመልሰዋል፡፡ከጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ የወጡት 12 ዝሆኖች ወደ ፓርኩ መመለሳቸው ተገልጻል፡፡በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን በሚገኝው የ…

ከአራት ቀናት በኃላ ዝሆኖቹ ወደ ፓርክ ተመልሰዋል፡፡

ከጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ የወጡት 12 ዝሆኖች ወደ ፓርኩ መመለሳቸው ተገልጻል፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን በሚገኝው የጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ የዝሆን መንጋ ከፓርኩ አምልጠው መውጣታቸው ይታወሳል፡፡

ከፓርኩ የወጡት 12 ዝሆኖች በሰዉ እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን የዳውሮ ዞን የከጪ ወረዳ ፖሊስ ጽፍት ቤት ምክትል ኢንስፔክተር ብርሃኑ ጠንክር ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጸዋል፡፡

ከፓርኩ የወጡት ዝሆኖች ጉዳት ያደረሱት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዳዉሮ ዞን ከጪ ወረዳ ኦዳ ጎፋ ቀበሌ ዝግና ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ነዉ።

እንደ ኢንስፔክተር ገለፃ ዝሆኖቹ መጋቢት 09 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ከጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፖርክ አምልጠው ህብረተሰቡ ወደ ሚርበት አካባቢ መውጣታቸው ተናግረዋል፡፡

ከጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ የወጡ በቁጥር 12 የሚሆኑ ዝሆኖች በፓርኩ ስካዉቶች እና በአከባቢዉ ህብረተሰብ የጋራ ርብርብ ወደ ፓርኩ መመለሳቸው ነው የተናገሩት፡፡
የዝሆን መንጋዎቹ በሃያዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚትገኝ ወጣት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸው የተገለጸ ሲሆን

እንደዚሁም ወደ መኖሪያ ቤቷ በመሄድ ላይ የነበረች የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ በዝሆኑ መንጋ ጉዳት ደርሶባት ታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላት እንደሚገኝም ምክትል ኢንስፔክተር ብርሃኑ ጠንክር ለጣበያችን ተናግረዋል፡፡

የዝሆን መንጋዉ በአካባቢው ገበሬዎች ንብረት ላይ ያደረሱት የንብረት ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ኢንስፔክተር በንብረት ላይ የደረሰዉ የጉዳት መጠን እየተጣራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ፓርኩ ሰፊ በመሆኑ በሁለት የጥበቃ እስካውት ብቻ ዝሆኑቹን መጠበቅ ከባድ ነው ያሉት አዛዡ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገበርኤል

መጋቢት 11ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply