ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ የትምህርት ዞን እንዲሆ መወሰኑ ትክክለኛ የተቋም መረጃን በአንድ ስፍራ ለማግኘት እንደሚያስችል ተገለጸ፡፡

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶክተር እንዱአለም አድማሴ ለአሐዱ እንደተናገሩት በትምህርት ዘርፉ የተበጣጠሱ አገልግሎት ሴክተሮችን ወደ አንድ ለማምጣት ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮሜዳ ባለዉ አካባቢ የትምህርት ዞን ብሎ በመሰየም በትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ ዉስጥ ተቋማቱ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ የተገልጋን እንግልት ለመቀነስ ስራዎች መጀመራቸዉን ተናግረዋል፡፡

በኤጀንሲዉ ዉስጥ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚደረጉት እነዚህ ተቋማት የትምህርት ጥራት፤ ተጠያቂነት፤ ተደራሽነት እንዲሁም ስለ ትምህርት ተቋማት ትክክለኛ እና የተሟላ አገልግሎት እንዲገኝ በማድረግ አኳያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸዉ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በዚህ ዓመት ተበታትነው የሚገኙ የትምህርት አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን ወደ ኤጀንሲዉ ግቢ በማምጣት ስራዎችን ለማስጀመር መታቀዱንም ገልጸዋል፡፡

*****************************************************************

ቀን 12/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ የትምህርት ዞን እንዲሆ መወሰኑ ትክክለኛ የተቋም መረጃን በአንድ ስፍራ ለማግኘት እንደሚያስችል ተገለጸ፡፡ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply