You are currently viewing ከአራት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ አየርመንገድ አውሮፕላን አደጋ በደረሰበት ቦታ ላይ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    መጋቢት 2 ቀን 2015…

ከአራት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ አየርመንገድ አውሮፕላን አደጋ በደረሰበት ቦታ ላይ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 2 ቀን 2015…

ከአራት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ አየርመንገድ አውሮፕላን አደጋ በደረሰበት ቦታ ላይ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 2 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የዛሬ አራት ዓመት መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737 አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ጉዞ እንደ ጀመረ በምሥራቅ ሸዋ ጊንብቹ ወረዳ ልዩ ስሟ ሐማ ቁንጡሽሌ በተባለ ቦታ ላይ በደረሰበት አደጋ የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ጨምሮ 157 የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። በዚሁ ዕለት ሕይወታቸውን ያጡት 17 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የእነዚሁ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች በየዓመቱ አደጋው በተፈፀመበትና አስከሬናቸው ባረፈበት ቦታ መታሰቢያ እያደረጉ ቆይተዋል፡፡ እነዚሁ የአደጋው ሰለባ የሆኑ ቤተሰቦች በቦታው ላይ ለመታሰቢያ የሚሆን ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት 7 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ ቦታ ገዝተው ባቀረቡት ጥያቄ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ መልካም ፈቃድ ትናንት የ 4ኛ ዓመት መታሰቢያቸው በተከበረባት ቀን መጋቤ ጥበብ ቀሲስ ጌቱ ሞቲ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ልዩ ፀሐፊ ፣ መጋቤ ሐዲስ ቆሞስ አባ ገብረ ጻድቅ መኮንን የሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ፣ ሊቀ ትጉኃን መንክር አቤ፣ መልአከ ኃይል ቀሲስ ኃይለ መስቀል የጊንቢቹ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ፣ መምህራን ፣ዘማሪያን እንዲሁም ሕይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል። በመርሐ ግብሩ ላይ የማጽናኛ ዝማሬና ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል መባሉን ዳጉ ጆርናል ከቤተክርስቲያኗ የዜና ምንጭ ካገኘዉ መረጃ ተመልክቷል፡፡ በመቀጠልም መጋቤ ጥበብ ቀሲስ ጌቱ ሞቲ ይህን ቅዱስ ዓላማ ወገኖቻቸውን ለማሰብ ቤተክርስቲያንን ለማነጽ መነሳሳታቸው እጅግ የሚበረታታ መሆኑና ዘመን የማይሽረው ታሪክን በወገኖቻቸው ስም እያስቀመጡ መሆኑን ገልጸው የብፁዕነታቸውን አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል ሲል ያጋራው ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply