
ከአርበኛ ዘመነ ካሴ የተላለፈ የመጨረሻ ጥሪ አደራ‼️‼️ መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ዛሬ ስሜት፣ የግልና የቡድን ፍላጎት፣ አለማወቅና በሌሎች ምክንያቶች ሊሸፍኑባችሁ ቢችሉ እንኳን ስለነገ አብዝቶ ከመጨነቅ የተነሳ የተፃፈ ጥሪዬን እነሆ:- ሀ) ለመለዮ ለባሾች በሙሉ መጋቢት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በአማራ ክልል ብዙ ቦታዎች ሥርዓቱን የሚቃወሙ እና የሥርዓቱን ለውጥ የሚጠይቁ ህዝባዊ ሰልፎች ይደረጋሉ። ታዲያ የሰልፉ ቀን አንዳንድ አለቆቻችሁ የሚሰጧችሁ ግዳጅ ምን ሊሆን እንደሚችል ይታወቃል። ሂድና ጎዳና ላይ ያገኘኸውን በለው፣ ጥረገው እንደሚሆን ያለፉት ከ30 የዘለሉ ዓመታት ልምዶችን ይነግረናል። እና አደራ ህዝባችሁን ጠብቁ። መሳሪያ ብትይዙም ባዶ ዕጃችሁን ምሰሉ። የዚህ አሳረኛ ህዝብ ልጆች መሆናችሁን በተግባር አረጋግጡ። ይህ ስርዓት ያልፋል። እመኑኝ ነገ እንደመስከረም ጉም በኖ ይጠፋል። እናንተ እና መከረኛው ህዝባችሁ ግን መኖር ትቀጥላላችሁ። መኖር እንቀጥላለን። ስለዚህ አፈር ግጦ አፈር መስሎ ያሳደጋችሁ ህዝብ ላይ እንዳተኩሱ። እንደ እንጨት በደረቀ ገላ አዝላ፣ የደረቀ ጡት እያጠባች ያሳደገች፣ ግን አማራ ስለሆነች ብቻ እሷ አታውቃቸውም ብዙ የሚያውቁት ጠላት ያላት ምስኪን እናታችሁ ገላ ላይ ዱላ እንዳታሳርፉ። የተለያየ ዩኒፎርም ወይንም ልብስ መልበሳችን ፤ ውሎ እና አዳራችን መለያየቱ የተለያየን ሰወች አያደርገንም። ሁላችንም በአንድ የሰከረ ዘመን የተፈጠርን የአንድ ድሀ ግን ኩሩ ማህበረሰብ ልጆች ነን። ወደድንም ጠላንም አንድ አፈር ያበቀለን ፣ ካንድ ወንዝ የተቀዳን ወንድም እና እህቶች ነን። ስለሆነም የሚያልፍ ስርዓት አዝዟችሁ ወላጆቻችሁን እንዳትበድሉ። የነገ መጠጊያ ቤታችሁን እንዳታቃጥሉ። በአዕምሯችሁ ውስጥ የጎጥ መፈክር ከተው፣ የመንደር ጥይት አስታጥቀው፣ ይሄን ምናምንቴ ሂድና በለው። የሚሏችሁን ደንቆሮ ካድሬዎች አትስሟቸው። እነሱ ጎጥ የሚባል ከብአዴን ሸለቆ የሚዛቅ የከበረ ማዕድናቸውን እየቸረቸሩ የሃምሳ ሚሊዮን ብር ቤት ይገዛሉ። የእናንተ ደመወዝ ላይ ግን ሃምሳ ብር አልተጨመረም። አይጨመርምም። ስለዚህ ለምን የቀጣፊ ቢበላ የማይጠግብ ፣ እምብርት የለሽ ካድሬ ዱላ ሆናችሁ ታገለግላላችሁ? ሂድና ህዝብን ግደል ሲልህ ኖ በጭራሽ፣ ዞር በል ከፊቴ፣ አንተ ቀጣፊ ካድሬ በለው። ሊያስገድድህ ከሞከረ ለህዝብ ግንባር ብለህ ጥይት መዘህ በአፉ አጉርሰው። መለዮ ለባሾች በአጠቃላይ አንገት ላይ የምትቆሙበት ሳይሆን ለህዝብ ህልውና ዘብ የምትቆሙበት ጊዜ ዛሬ ነው ። ነገ በአንድ ዩኒፎርም በአንድ ዩኒፎርም መልበሳችን አይቀርምና። አደራ!! አደራ!!! “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post