You are currently viewing ከአርበኛ ዘመነ ካሴ  የተላከው ደብዳቤ! የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ይህ ፁሑፍ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሰልፍ ከመጥራቱ ከአንድ ሳምንት በፊት በ28/05/2015 ዓ.ም የተፃፈ ነዉ።…

ከአርበኛ ዘመነ ካሴ የተላከው ደብዳቤ! የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ይህ ፁሑፍ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሰልፍ ከመጥራቱ ከአንድ ሳምንት በፊት በ28/05/2015 ዓ.ም የተፃፈ ነዉ።…

ከአርበኛ ዘመነ ካሴ የተላከው ደብዳቤ! የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ይህ ፁሑፍ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሰልፍ ከመጥራቱ ከአንድ ሳምንት በፊት በ28/05/2015 ዓ.ም የተፃፈ ነዉ። በአንድ ወንድሜ እጅ ሰንብቶ ዛሬ በ07/06/2015 ዓ.ም ወደ ሳተናው ሚዲያ የተላከ ነዉ። … ምንአልባት የማይገባኝ ፣ ለጉዳዩ የማልመጥን ሊመስልብኝ ይችላል በርግጥም ብዙ አባቶች እና በርካታ ሊቃዉንት በሞሉበት ሐገር የኔ በጉዳዩ ላይ አንዳች ነገር መናገር ፍፁም ድፍረት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የምንታገለዉ ስርዓት የስጋችን ብቻ ሳይሆን የመንፈሳችንም ጠላት እንደሆነ ከተረዳሁ አመታት ተቆጥረዋል እና ከሚሰማኝ እና ከማምንበት ጥቂት መስመሮችን ፅፌያለሁ፦ ዘመኑ የሰይፍ ነዉ ። ታዲያ ሰይፍ በሰይፍ እንጂ በልምጭ አይመከትም እና ሁሉም ሰይፋን ያንሳ። የቤተክርስቲያናች እና የህዝባችን ጠላት ሰይፍን ስሎ ጦሩን አሹሎ መጦ ቤተ ክርስቲያናችን ላይ በሰዉ ልጅ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ዉድመት እና ዉርደት እየደረሰ ባለበት በዚ ቅፅቨት በአፍ ታንቲራ እና በለምለም ልምጭ ለዉጥ አይመጣም። ሰይፍ ይዞ የመጣን አዉሬ የምታስቆመዉ ከፍ ሲል አንገቱን ዝቅ ሲል ሰይፍ የያዘበት እጁን ቆርጠህ መጣል ስችል ብቻ ነዉ። እንጂ ሰማይ ሙሉ እሳት የሚያዘንብን ጠላት ዉሃ በእፍኝ መርጨት አንድም ፍርሃት ነዉ ፣ አልያም ለምድርም ለሰማይም የማይሆን ከንቱነት ነዉ። በዚህ ዘመን እሳት በሳት እንጂ በዉሃ አይጠፋም። -መነኩሳት የመቋሚያችሁን የታችኛዉ ጫፍ አስቀጥቅጣችሁ አሹሉት እና የጠላትን ሆድ የሚዘረግፍ ደንበኛ ጦር አርጉት። ጠላትን በደሎትም በብረትም ተዋጉት። -አባቶች እንደ አንድ አባት ምሩን። ጥፋት ያወጀብንን ”መንግስት”መፍትሔ በመለመን አጉል አትድከሙ፤እኛንም አታዳክሙን ጊዜያችንንም አትብሉብን። ሐረሬዎች ሲተርቱ ”ከእባብ አምልጦ ወደ ፍኝት ሩጦ”ይላሉ። እባቡ ከጉድጓዱ ወጦ በይፋ የቤተክርስቲያናችን አንገት ላይ ተጠምጥሞ መላ አካሏን ነድፎ ሊገላት፣ኢትዮጵያንም በፍርሃት ሊያፈርሳት ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ ነዉ ታዲያ የእባቡን አናት መቀጥቀጥ ወገቡንም መቁረጥ እንጂ ለአቤቱታ ወደ እፍኝት መሮጥ ፍፁም ታካችነት ፣ ፍፁም ከንቱነት እና ወለፈንዲነት ነዉ። ይልቁንስ ምእመኑን በጠላት ሰይፍ እንዲሞት ሳይሆን ጠላትን በሰይፍ እንዲገል አዘጋጁት። ድፍረት እንደሆነ ባዉቅም አንድ ጥያቄ ልጠይቅ :- መነኩሴ ሞት ይፈራል እንዴ? የሞተ ሞትን ይፈራል? ፍርሃት አለማዊዩን ብቻ ሳይሆን ሰማያዊዩን ህይወታችንንም እየነጠቀን ነዉ። እና እናንተ በርትታችሁ ምመኑንም አበርቱት ሰማይትነቱን እናንተ ጀምሩት ምመኑ ለታሪክ በሚጣፍጥ አኳኋን ይጨርሰዋል። -የቤተክርስቲያናችን ልጆች ገድላችሁ ለመሞት እራሳችሁን አዘጋጁት። ታዲያ ጠላታችሁን በትክክል ለይታችሁ ይሁን። የቤተክርስቲያንን ጫፏን እንኳ እንዳታስነኩ የሌሎች ስጋዎቻችን ቤተ እምነቶችንም ጫፍ እንዳትነኩ። ግፈኛን አጥፉ ግፍ ማድረስንም ተጠየፉ። ትክክለኛ የቤተክርስቲያኗ ልጅነታችሁን በተግባርም በምግባርም አረጋግጡ። – ድንግል ማርያም እና ልጇን ከሚያፈቅር ፣ ፃድቃንን እና ሰማዕታትን ሃዋሪያት እና ነቢያትን ከሚያከብር ቤተሰብ ተወልጄ በአርባ ቀኔ በራሷ በኪዳነ-ምህረት እጅ ክርስትና ተነስቼ ፣ በእሷ እቅፍ አድጌ ፣ ብዙ መከራዎችን ተሻግሬ ዛሬ ላይ የደረስኩ ባተሌ ነኝ እና ይህንን የስጋችንም የነፍሳችንም ጠላት የሆነ ሃይል ላላጠፋ ለአንድ ቀን እንኳን ብሰንፍ ቅዱስ ሚካኤል ያጥፋኝ። – እናቴ ድንግል ማርያም ሆይ ለአንቺ ክብር መቆም የማልችል ደካማ ከሆንሁኝ ድንገት ወደ ትነት ቀይሪኝ። አንዲት ቤተክርስቲያን አንድ ሲኖዶስ አንድ ፓትሪያሪክ ዘመነ ካሴ ከባህርዳር ወህኒ ቤት ሳተናው እንደዘገበው “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply