You are currently viewing ከአቢ ደንጎሮ ከተማ በቅርብ ርቀት ውሃ ለመቅዳት ያቀኑ 4 ሴቶች በጦር ፣ በገጀራ፣ በቆንጨራ እና በሜንጫ ሊፈጸምባቸው ከነበረ ጥቃት በሚሊሾች ትብብር ተረፉ፤ በተቃራኒው ጥቃት ሊያደርሱ ሲሉ…

ከአቢ ደንጎሮ ከተማ በቅርብ ርቀት ውሃ ለመቅዳት ያቀኑ 4 ሴቶች በጦር ፣ በገጀራ፣ በቆንጨራ እና በሜንጫ ሊፈጸምባቸው ከነበረ ጥቃት በሚሊሾች ትብብር ተረፉ፤ በተቃራኒው ጥቃት ሊያደርሱ ሲሉ…

ከአቢ ደንጎሮ ከተማ በቅርብ ርቀት ውሃ ለመቅዳት ያቀኑ 4 ሴቶች በጦር ፣ በገጀራ፣ በቆንጨራ እና በሜንጫ ሊፈጸምባቸው ከነበረ ጥቃት በሚሊሾች ትብብር ተረፉ፤ በተቃራኒው ጥቃት ሊያደርሱ ሲሉ እጅ ከፈንጅ የተያዙ ባለገጀራዎች በፖሊስ ተለቀዋል አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሆሮ ጉድሩ ዞን ከአቢ ደንጎሮ ከተማ በቅርብ ርቀት ወደ ዴቢስ ቀበሌ መውጫ በኩል ውሃ ለመቅዳት ያቀኑ በማንነታቸው አማራ የሆኑ 4 ሴቶች በጦር፣ በገጀራ፣ በቆንጨራ እና በሜንጫ ሊፈጸምባቸው ከነበረ ጥቃት በሚሊሾች ትብብር ተርፈዋል፤ በተቃራኒው ጥቃት ሊያደርሱ ሲሉ እጅ ከፈንጅ ከእነ ጦራቸው የተያዙት በፖሊስ ተለቀዋል። ጥቅምት 5 ቀን 2014 ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ ውሃ ለመቅዳት በሚል ከአቢ ደንጎሮ ከተማ በቅርብ ርቀት ያቀኑ 3 ሴቶችን ጦር፣ ገጀራ፣ቆንጨራ፣ሜንጫ በያዙ የተደራጁ የኦነግ ሸኔ አባላት ሊፈጸምባቸው ከነበረው ጥቃት በመሮጥና ድንገት በደረሱ ሚሊሾች ትብብር ተርፈዋል። የውሃ መቅጃ ጀሪካቸውን በመቅደድ ላይ እያሉ የአማራ ሚሊሾች ደርሰው በቁጥጥር ስር በማዋል ወደ ወረዳው ፖሊስ ጣቢያ ወስደው እንዲታሰሩ ሲጠይቅ ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት ፈጥነው በአካባቢው የደረሱት የአማራ ሚሊሾች ወንጀሉን ለመፈጸም ሲንቀሳሰሱ የያዟቸውን 10 የኦነግ ሸኔ አባላትና ደጋፊዎችን ወደ ወረዳው ፖሊስ ጣቢያ የወሰዱ ቢሆንም በፖሊሶች ነቀፌታና ማስፈራሪያ የደርሶባቸው መሆኑ ተነግሯል። ሜንጫ እና ገጀራ ከያዙት በቅርብ ርቀት ጦር መሳሪያ የያዙ ሸኔዎች እንደነበሩም ተሰምቷል። “እናንተን ማን አሳሪ አደረጋችሁ? ሲጀመር ምን አገር አላችሁ?” በማለት ስልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም በጎሰኝነት እሳቤ ሚሊሾችን አንገራግረዋል ተብሏል። ንጹሃንን ሊጨፈጭፉ የመበሩ ባለቆንጨራ እና ባለ ገጀራዎቹ ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ በፖሊስ መለቀቃቸውን የገለጹት ምንጮች ሁኔታው አሳዛኝ ነው፤ የፖሊስ አካሄድ ጎሰኝነት የነገሰበት፣ ፍትህ ሞቶ የተቀበረበት ስለመሆኑ ማረጋገጫ ነው ሲሉ ምንጮች አውግዘውታል። በተያያዘ አንድ የኦሮሞ ሚሊሻ ኢዶክሳ ቀበሌ ላይ ጥቅምት 4 ቀን 2014 ሌሊት ላይ የጦር መሳሪያ ጠፍቶኛል፤ አማራዎች ነው የወሰዱት በሚል ሽፋን ለማስፈራራት እየተሞከረ ነውም ተብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply