ከአንድ ዓመት በላይ በባህር ዳር እስር ቤት እየማቀቅን የምንገኝ 4 የሰኔ 15 ተከሳሾች ለአቃቢ ህግ ምስክርነት እንድንቀርብ መጠየቁ አግባብነት የጎደለው ነው ሲሉ ተከሳሾች ቅሬታ አቀረቡ። አ…

ከአንድ ዓመት በላይ በባህር ዳር እስር ቤት እየማቀቅን የምንገኝ 4 የሰኔ 15 ተከሳሾች ለአቃቢ ህግ ምስክርነት እንድንቀርብ መጠየቁ አግባብነት የጎደለው ነው ሲሉ ተከሳሾች ቅሬታ አቀረቡ። አ…

ከአንድ ዓመት በላይ በባህር ዳር እስር ቤት እየማቀቅን የምንገኝ 4 የሰኔ 15 ተከሳሾች ለአቃቢ ህግ ምስክርነት እንድንቀርብ መጠየቁ አግባብነት የጎደለው ነው ሲሉ ተከሳሾች ቅሬታ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 8 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት በእስር ላይ የሚገኙ የጦር መኮንኖች የአቃቢ ህግ ምስክሮችን በ3 ዙር ቀጠሮዎች ሲከታተሉ መሰንበታቸው ይታወቃል። አቃቢ ህግ ምስክሮችን ለማቅረብ መጥሪያ ይጻፍልኝ ሲል ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት አቤቱታ ማቅረቡን ተከትሎ ለታህሳስ 12 ምስክሮችን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ተገልጧል። ይህን ተከትሎ በትናንትናው እለት ታህሳስ 7 ቀን 2013 ዓ.ም በጉዳይ አስፈጻሚ በኩል በሰኔ 15 የግድያ ወንጀል ተጠርጥረው 1 ዓመት ከ5 ወራት በላይ በእስር ላይ ለሚገኙ 4 ተከሳሾች ለአቃቢ ህግ ምስክርነት እንዲቀርቡ ተጠይቋል። ለአቃቢ ህግ ምስክርነት እንዲቀርቡ መጥሪያ የደረሳቸውም 4 ተከሳሾችም የአዴሃን የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ከበደን ጨምሮ፣ ኮሎኔል ፈንታሁን፣አምሳ አለቃ አየነው ታደሰና አምሳ አለቃ አሰፋ ጌታቸው ናቸው። “እናንተ የአቃቢ ህግ ምስክሮች ናችሁ፣ ታህሳስ 12 ቀርባችሁ የምስክርነት ቃላችሁን ትሰጣላችሁ” መባላቸው ግራ እንዳጋባቸው ነው ከተከሳሾች ለመረዳት የተቻለው። የምስክር ቃል ባልሰጠንበት አግባብ፣ታስረንና ተከሰን ባለንበት ሁኔታ እንዴት ለምስክርነት እንጠራለን በሚል በግርምት ይጠይቃሉ። ህግን ሽፋን በማድረግ ያላስፈላጊ ጫና ለመፍጠር እና እኛን ለመከፋፈል የታሰበ ሊሆን ይችላል ያሉት ተከሳሾቹ ፍ/ቤቱን አክብረው ሊቀርቡ እንደሚችሉ ገልፀዋል። ጠበቃ በሙሉ ታደሰ በበኩላቸው የአቃቢ ህግ ምስክሮች ዝርዝር ለጠበቆች ቀድሞ ስላልደረሰን በሚል ማብራሪያ ለመስጠት አልፈለጉም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply