
ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያውን የመንገደኞች ጉዞውን ወደ ትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀለ አደረገ። የፈደራል መንግሥቱ ሠራዊት መቀለን ለቆ መውጣጡን ተከትሎ ተቋርጦ ለ18 ወራት የቆየው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ እነሆ መልሶ ጀምሯል። ዛሬ ረቡዕ ታኅሣሥ 19/2015 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተነሳው የተጓዦች አውሮፕላን በትግራይ መዲና መቀለ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ ደርሷል።
Source: Link to the Post