ከአክሱም ከተማ 23 የወርቅና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መዘረፋቸዉ ተነገረ፡፡ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት 23 የወርቅ እና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መጥፋታቸው እንደተረጋገጠ የአክሱም ከተማ ባህ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/TNO2GXvo_4BPxKZO-6qVVxTxowYIwVC_HIjcgp6QbjrkggGV5_-GCVZRvPwKuI_GUpMmn2a2SI_Y9Sjgfma0czFRsV5Hrso7CmRZGX12IKQeGRaa7U5mlXukQsvQ_xT6AFrP3HWnO-J4lOktubtZ1g2LhaPXOmyj0CISXCE4CO-iYH1SsjkdA_m9viUzLmBKxm--sjY21vbw7e0RhiqgUULEJZFu6FPLnF9WW82YIY6N9XQYEr95DlLsJvyKZGS1Gn05ciDAJTNSZJYlBjcp-GdmH6SWr2xAw4MP19mi26C2yuri7GZsH0JL-kD_q5b6FgVsSsCttKa_EdYm43gLEw.jpg

ከአክሱም ከተማ 23 የወርቅና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መዘረፋቸዉ ተነገረ፡፡

በሰሜኑ ጦርነት ወቅት 23 የወርቅ እና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መጥፋታቸው እንደተረጋገጠ የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ገብረ መድህን ፍፁም ብርሀን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታዉቀዋል፡፡

አክሱም ከተማ በቱሪዝም እንቅስቃሴ ላይ የተመሰረተች ከተማ መሆኗን የገለፁት ሀላፊው በጦርነቱ ከወደሙት ቅርሶች ባለፈ የተዘረፉና የጠፉ 23 የወርቅ እና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

የነዚህ ቅርሶች መጥፋት በከተማዋ የቱሪዝም እንቀስቃሴ ላይ ጉልህ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳሳደረ አብራርተዋል፡፡

የጠፉትን ቅርሶች ማን እንደወሰዳቸው ማወቅ እንዳልተቻለ የገለፁት ሀላፊው እነዚህን ቅርሶች የማፈላለግ ስራ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

አቶ ገ/መድህን ፍፁም ብርሀን እንደገለጹልን፣ ጽሕፈት ቤታቸው በዋናነት እየሰራ ያለው ከፌደራል እና ከክልል ፖሊሶች ጋር በጥምረት በመሆን ቅርሶቹ ሀገር ውስጥ ካሉ ከሀገር እንዳይወጡ የማድረግ ስራ ነው፡፡

ሀላፊው በአክሱም ሀውልት ስር ውሃ እንደተኛበት አንስተው የቅርስ እና ጥበቃ ባለስልጣን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ሀውልቱን የመታደግ ስራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰበት የአክሱም አየር መንገድም በኢትዮጵያ አየር መንገድ አማካኝነት የእድሳት ስራው እየተሰራ እንደሆነ የገለፁት ሀላፊው በቅርቡ እድሳቱ ተጠናቆ ወደስራ እንደሚመለስም ጠቁመዋል።

በለአለም አሰፋ

ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply