ከአወማ እና አተማ ጥምረት የተሰጠ ህዝባዊ ጥሪ‼ ================= ፍፁም በጋራ ቆምን‼️ ዕለተ እሁድ የካቲት 23 ሺ ስምንት መቶ ሰማኒያ ስምንት ነው ።በብዙ ሺዎች የሚቆጠረው…

ከአወማ እና አተማ ጥምረት የተሰጠ ህዝባዊ ጥሪ‼ ================= ፍፁም በጋራ ቆምን‼️ ዕለተ እሁድ የካቲት 23 ሺ ስምንት መቶ ሰማኒያ ስምንት ነው ።በብዙ ሺዎች የሚቆጠረው የወራሪው የጣሊያን ወታደሮች በከባድ መሳሪያዎች የታገዘውን ጦርነት ከሀገራችን ጋር ያደረጉት ።አባታችን አፄ ምንሊክ ነፍጠኛውን እና ትምክተኛውን ጦራቸውን ለክብር ፣ለነፃነት የሚደረገው ጦርነት ውጊያ ላይ በከፍተኛ ወኔ አሰለፉ ።ውጊያው በአድዋ ተራራ ነበር ።ጠላት የጣሊያን ጦር የአፈር ራት ሆነ ።መሬት ላይ አሰከሬናቸው እንደ ምድር አሽዋ ተዘራ ።በታላቁ ንጉሳችን የሚመራው የሀገራችን ጦር ድሉን ተቀዳጀ ።ንጉሰ ነገስቱ ፤ነገስታቱ እና መኳንንቱ በፌሽታ ላይ ሆኑ ።… ኢትዮጵያውያንም ተደሰቱ ። በአድዋ ተራራ ላይ አያቶቻችን ያገኙት ድል በመታሰቢያነት በዛሬው ዕለት በተለያዩ የአማራ ከተሞች በድምቀት አከበርን ።ድሉ የፋኖነት ውጤት ነውና የፋኖነትን የከፍታ መንፈስ በመላበስ ዳግም አድዋ ለመፍጠር የመንፈስ ስንቅ አነገብን ።በዚህም የአማራ ወጣቶች ማህበር (አወማ) እና የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) የሚከተሉትን የአማራ ህዝብ የዘመናት ጥያቄዎቻችን ለማስመለስ ፤ደራሽ ችግሮቻችን ለመፍታት በጋራ ለመስራት በፍፁም ጥምረት በጋራ ቆምን ።በፍፁም ቁርጠኝነት የሚከተሉትን እንሰራለን ፦ 1).የአማራን ህዝብ ህልውና ማስጠበቅ 2).የአማራን ህዝብ ታሪካዊ ርስቶች ማስመለስ 3).ለህዝባችን ዘላቂ ደህንነትን መፍጠር 4).ከታሪካዊ ርስቶች ውጪ የሚኖረው የአማራ ህዝብ በማንነቱ ተከብሮ እንዲኖር ማድረግ 5).ከጠላቶቻችን ለሚደረጉ ጦርነቶች ህዝባችንን ማዘጋጀት(ጊዚያዊ ) 5).ህዝባዊ ንቅናቄ በሁሉም የአማራ ከተሞች ማካሄድ (ጊዚያዊ ) በመሆኑም ለመላው የአወማ አባላትና ደጋፊዎች ፤ለመላው የአተማ አባላትና ደጋፊዎች ፤ለመላው የአማራ ክልል የፀጥታ ተቋማት አባላት እንዲሁም ለመላው የአማራ ህዝብ በቅርቡ ለምናደርገው ህዝባዊ ንቅናቄ አጋር ትሆኑን ዘንድ የከበረ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።ህዝባዊ ንቅናቄው እና ትግላችን ህዝባችን የማዳን ፣የመታደግ ፣የማስከበር እንዲሁም ፋኖአችንን የመጠበቅ ፤ልዩ ሃይሉን የመታደግ እንቅስቃሴ ነው ። ድላችን በህብረታችን‼️ ከአማራ ወጣቶች ማህበር (አወማ) እና ከአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) የካቲት 23:2014 ዓ.ም አድዋ❗️

Source: Link to the Post

Leave a Reply