ከአዲስ አበባ መቀሌ ከነገ ጀምሮ ዳግም በረራ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ፥ ተቋ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/J6oCLAArGg_1boGy5y7JwUkfre4b6UEgjMgrDhJ_ZBnmTQig_Eil4cofyOxf35_DRtz-WNVIfaQQ90Jx823hPMxKTc-RzV5fnCW8ZN3_QveYVYPTOX5DQahQWPXz1xGj_iJGxtRll28goLGx2FJxl9UbO23tDacGbq_rXk3O0Rk5zT_01C_6_8QMMgDWALm5UxzCXklsSP-L-eCAAUo88g8ZR4Pzkaf5u--1eLj9M2uTHjiifq8YEE3D3PyUX1w5i9QNzHcdGFUKHokfjxwMQVKeFXo0dQMRbhgv-ukwW3Let93V6c_8sYdXyfhmCV_i6rJBPzfNZnYTge0JyndBBw.jpg

ከአዲስ አበባ መቀሌ ከነገ ጀምሮ ዳግም በረራ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ፥ ተቋርጦ የነበረው ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ የአየር ትራንስፖርት በነገው ዕለት ይጀምራል፡፡

በፌዴራል መንግስቱና በህወሓት መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የአቬየሽን ሰራተኞች ወደ መቀሌ አቅንተው የመቀሌ አየር መንገድ ለበረራ ምቹ ሁኔታ ላይ መሆኑን አረጋግጠዋልም ነው ያሉት።

በመሆኑም ነገ በሚጀምረው በረራ በቀን አንድ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ፥ የደንበኞቹ ፍላጎትን መሰረት በማድረግም የበረራው ቁጥሩ ከፍ ሊል የሚችልበትን ሁኔታ እንደሚፈጠርም ነው ዋና ስራ አሰፈጻሚው የገለፁት፡፡

ተቋርጦ የነበረውን የበረራ እንቅስቃሴ በሁሉም የትግራይ ክልል የበረራ መዳረሻዎች ለማስጀመር ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ዋና ስራ አስፈጻሚው አንስተዋል፡፡

ነገ የሚጀምረው በረራም ከሌላው ወገኑ ጋር ግንኙነቱ ተቋርጦ የነበረውን የትግራይ ህዝብ ዳግም እንዲገናኝ ለማድረግ ትልቅ እድል የሚፈጥር እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply