You are currently viewing ከአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 1 በተወሰደው በዱላ ማሪያም እና ሆሪሳ መዳህኒያለም የዜጎች ቤት ከመጋቢት 17 ሌሊት ጀምሮ ይፈርሳል መባሉን ተከትሎ በሽህ የሚቆጠሩ ወገኖች…

ከአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 1 በተወሰደው በዱላ ማሪያም እና ሆሪሳ መዳህኒያለም የዜጎች ቤት ከመጋቢት 17 ሌሊት ጀምሮ ይፈርሳል መባሉን ተከትሎ በሽህ የሚቆጠሩ ወገኖች…

ከአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 1 በተወሰደው በዱላ ማሪያም እና ሆሪሳ መዳህኒያለም የዜጎች ቤት ከመጋቢት 17 ሌሊት ጀምሮ ይፈርሳል መባሉን ተከትሎ በሽህ የሚቆጠሩ ወገኖች በጨለማ ጭምር እየለቀቁ መሆኑን ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 1 በተወሰደው በዱላ ማሪያም እና ሆሪሳ መዳህኒያለም መጋቢት 17/2015 ከሌሊት ጀምሮ ቤታችሁ ይፈርሳል የተባሉ ነዋሪዎች ንብረታቸውን በጨለማ ሁሉ እያሸሹ መሆኑን በማስታወቅ ድረሱልን ሲሉ እየተማጸኑ ነው። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የአካባቢው ምንጮች እንደሚሉት “ቤታችሁ እንዳይፈርስባችሁ እናደርጋለን” በሚል ከበላይ አመራሮች ጋር በመገናኘት የሰፈር ኮሚቴዎች ከእያንዳንዱ ነዋሪ 2,800 ብር አስከፍለዋል። የሰፈር ኮሚቴዎች ከሰሞኑ በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች በሚል ሁሉም የዱላ ማርያም አካባቢ ነዋሪ በነፍስ ወከፍ 300 ብር እንዲከፍል አድርገዋል። መጋቢት 17/2015 ጠዋት ላይ የሰፈር ኮሚቴዎች የተቦረቦረ መንገድን ለማልማት ስለሆነ ሁሉም ነዋሪ ለአስቸኳይ ስብሰባ እንዲወጣ በማለት በጥሩምባ እየዞሩ መቀስቀሳቸውን ተከትሎ ህዝቡ የወጣ ቢሆንም ሀሳባቸውን በመቀዬር ገበሬዎችን ብቻ ነጥለው በማስቀረት ሌላውን ወደየቤትህ ተመለስ ስለመባሉ ተሳታፊዎች ገልጸዋል። ይሁን እንጅ ከስብሰባ በኋላ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በገበሬዎች በኩል እንደአብነትም በአቶ ደረጀ ብርቱካን በኩል ” ሌሊት 10 ሰዓት ስለሚገቡ እቃችሁን አውጡ!” የሚል መልዕክት ተላልፏል ተብሏል። አራት ፓትሮ የኦሮሞ ታጣቂዎችም አመሻሹን ወደ አካባቢው ስለመግባታቸው የዐይን እማኞች ተናግረዋል። ነዋሪዎችም አቤቱታ የሚያቀርቡበትና የሚሰማን አካል የለም በሚል በተስፋ መቁረጥ ስሜት ከቆርቆሮ ውጭ ንብረታቸውን እየጫኑ በመውጣት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። ይህ ቤት የማፍረስ እቅድም በዋናነት የመጣው ሰፊ ቁጥር ያለውን አማራ ከአካባቢው ለማፈናቀል እና በኢኮኖሚ ለማዳከም ታስቦ የተደረገ ስለመሆኑ ነዋሪዎች ይናገራሉ። በጨለማው ጭምር ንብረታቸውን እያሸሹ ስለመሆኑ ታውቋል። በዚህ የማፍረስ እና የማፈናቀል ዘመቻ ቢያንስ ከ3 ሽህ በላይ አባዎራዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችል ተመላክቷል፤ ንብረታቸውንም በጥድፊያ እያወጡ ነው፤ በሌሊት ቆርቆሮ ሲንኳኳ ይሰማልም። የባጃጅ ክልከላ ጋር ተደርጎ በነበረበት ወቅትም የሰፈር ኮሚቴዎች ጭምር ስለምን ወደ መጣችሁበት አትሄዱም በሚል ነዋሪዎችን እንዲሸማቀቁ ሲያደርጉ እንደነበር ተወስቷል። ኤርቱ ሞጆ ላይ ከወራት በፊት የዜጎች ቤት ሲፈርስ አንዲት እናት ከእነ ህጻን ልጇ በጅብ የተበላችበት እንዲሁም መጋቢት 14/2015 ደግሞ ቄስ ዓባይ መለሰ የተባሉ አባት በድንጋይ እና በዱላ ተቀጥቅጠው የመገደላቸው እጅግ አሳዛኝ ዜና መዘገቡ ይታወሳል። ፎቶው_የዜጎች ቤት በስፋት እየፈረሰ ከሚገኝበት አካባቢ አንዱ ገላን ሲዳማ አዋሽ ሰፈር ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply