You are currently viewing “ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ተከልሏል በተባልነው በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ስሙ ጀሞ ተራራ መድኃኒያለም እና ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የምንኖር ዜጎች ቤታችን በኃይል እን…

“ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ተከልሏል በተባልነው በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ስሙ ጀሞ ተራራ መድኃኒያለም እና ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የምንኖር ዜጎች ቤታችን በኃይል እን…

“ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ተከልሏል በተባልነው በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ስሙ ጀሞ ተራራ መድኃኒያለም እና ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የምንኖር ዜጎች ቤታችን በኃይል እንዲፈርስ እየተደረገ ነው” ድረሱልን ሲሉ ጥሪ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) እንደሚሉት ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ተብሎ መንግስታዊ አገልግሎት ያገኙ ነበር። ይሁን እንጅ በጥቅምት ወር 2015 ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ክልል መካለላችን ተነግሮናል ይላሉ። ይህን ተከትሎም በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ቀጠና 4፣ 6፣ 8፣ 9 አካባቢ እና ጀሞ ተራራ መድኃኒያለም አካባቢ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ተካታችኋል፤ አዲሱ የወረዳው ስምም ገዳፈቻ መሆኑን እወቁ ተብሎ ተነገረን ብለዋል። በመቀጠልም ታህሳስ 10/2015 በጀሞ ተራራ መድኃኒያለም ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ከአስር ሽህ ያላነሱ የአካባቢው ነዋሪዎችን በመሰብሰብ በቅርብ ወራት የተሰሩ እና ሰው የሌለባቸውን ቤቶች እንደሚያፈርሱ ተነግሯቸዋል። በወቅቱ የስብሰባው ዙሪያ በታጠቁ የኦሮሚያ ኃይሎች የተከበበ ስለነበር የተለዬ ጥያቄ መጠየቅም ዋጋ ስለሚያስከፍል ሰምተው ወደ ቤታቸው እንደተመለሱ ያስታውሳሉ። በዚህም መሰረት ታህሳስ 19/2015 እየዞሩ ከኦሮሞ በስተቀር የአማራ፣ የጉራጌ፣ የስልጤ፣ የወላይታ እና የሌሎች ኢትዮጵያዊያንን ቤቶች ቀለም ቀብተዋል፤ መሳሪያ እና ስለት ነገር ካለ በሚል ፍተሻም አድርገዋል ይላሉ የአሚማ ምንጮች። በመቀጠልም በእለተ ሀሙስ ታህሳስ 20/2015 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ከ10 እስከ 15 እና 20 ዓመት ድረስ ገንብተው የኖሩበትን ቤት ጭምር እያፈረሱ መዋላቸው ተነግሯል። በተመሳሳይ ታህሳስ 21፣ 22 እና ታህሳስ 24/2015 በእለተ አርብ፣ ቅዳሜ እና ሰኞም አፍራሽ ግብረ ኃይል አሰልፈው ሲያፈርሱ እና ቆርቆሮውን እየጫኑ ሲወስዱ መዋላቸው ተገልጧል። በዚህም በቀላል ግምት ከ3,500 በላይ ቤቶች በኃይል እንዲፈርሱ መደረጉንና ለምን ይፈርሳል ብለው ጥያቄ በማንሳታቸውም የታሰሩ እና የተደበደቡ በርካታ ሰዎች እንዳሉም ጥይት ተተኮሰብን በሚል ከጥቃቱ እየሸሹ የነበሩ የአሚማ ምንጮች ተናግረዋል። በተያያዘ በእለ እሁድ ታህሳስ 23/2015 በኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰበታ ወለቴ ቀበሌ ከ700 ያላነሱ ቤቶችን እየለዩ ያፈርሱ ነበር ይላሉ የመረጃ ምንጮች። የተኩስ ልውውጥ ነበር፤ በጥቃቱም የተጊዳ ሰው ስለመኖሩ ሰምተናል ብለዋል። በስብሰባ ላይ የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮች በመምጣት:_ 1) ሰው ያለበት ቤት አንነካም፣ 2) ባዶ ቤት እናፈርሳለን፣ 3) ባዶ ታጥሮ የተቀመጠን ግቢ እናፈርሳለን፣ 4) መብራት እና ውሃ ላላገኘ እናስገባለን በማለት ካታለሉ በኋላ ጥረው ግረው በጥሪታቸው ሰርተው ብዙ ዓመት የኖሩበትን ቤት ሁሉ በማፍረስ ለኢትዮጵያዊያን ያላቸውን ንቀት እና አድሎአዊነት በግልጽ አሳይተዋል ብለዋል። “ከእንቅልፋችን ስንነሳ ኦሮሚያ ክልል አሉን” የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎች ታህሳስ 24/2015 ከሌሊቱ 11 ሰዓት ላይ ደግሞ ከኦሮሞ ውጭ የሆኑ ተወላጆችን ቤት ለማፍረስና ለማፈናቀል የለቡ መስተዳድር ዙሪያ ቀጠሮ መያዙ ተሰምቷል። የአቶ ስንታዬሁ ቸኮል ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ በሚል እንዳጋራው ከሆነ እንቁ ገብርኤል በተለምዶ ለቡ ባቡር ጣቢያ አካባቢ ተብሎ በሚጠራው 20 ዓመት እና ከዚያ በላይ የኖሩበትን ቤት መጤ በማለት ከኦሮሞ ዉጭ የሆኑ ተወላጆችን ቤት በማፍረስ ለማፈናቀል ቀጠሮ ተይዟል እና ሳይፈርስ ድረሱልን የሚል ጥሪ ማድረጋቸው ተመላክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply