ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጡ ወጣቶች በገፍ የምርጫ ካርድ እየተሰጠ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል              አሻራ ሚዲያ30 /8/ 2013 ዓ.ም ባህር ዳር በአዲስ አበባ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ…

ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጡ ወጣቶች በገፍ የምርጫ ካርድ እየተሰጠ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል አሻራ ሚዲያ30 /8/ 2013 ዓ.ም ባህር ዳር በአዲስ አበባ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ…

ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጡ ወጣቶች በገፍ የምርጫ ካርድ እየተሰጠ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል አሻራ ሚዲያ30 /8/ 2013 ዓ.ም ባህር ዳር በአዲስ አበባ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያ 17 ላይ ከአዲስ አበባ ውጭ በገፍ ለመጡ ወጣቶች በሕገ ወጥ ሂደት የመራጮች ካርድ እየታደለ መሆኑን የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የምርጫ ጣቢያዎች የክትትል ቡድን አስታውቋል። የክስተቱን በምስል ለመቅረፅ የሞከሩት የባልደራስ የአካባቢው ተወካይ አቶ አንተነህ ደሳለኝ በፖሊስ ታስረዋል። ወጣቶቹ የመጡት ኮድ 3፡27401 ኦሮሚያ በሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ተሳፍረው ነው ተብሏል። የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 4፡03548 የሆነ ፒካፕ የመንግሥት ተሽከርካሪ ደግሞ አይሱዙውን እያጀበ የምርጫ ጣቢያው ድረስ አድርሷቸዋል። የአካባቢው ኗሪዎች ወጣቶችን እንደማያውቋቸውና እንግዳ እንደሆኑም ተናግረዋል። በተያያዘ ዜና በከተማዋ ለሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ የኗሪነት መታወቂያዎች እየታደሉ ነው። የቤት ቁጥርና መሰል መስፈርቶችን ሳይጠይቁ ነው መታወቂያ እየታደሉ ያለው። እደላው በምርጫ እንዲሳተፉ በሚል ከበላይ አካል በመጣ ትዕዛዝ እንደሆነ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ባለሙያ ተናግረዋል። ይህ የሆነው የአማራ ተወላጅ የጎዳና ተዳዳሪዎች ተመርጠው በኮሮና መከላከል ሰበብ ወደ ባሕር ዳር ከተሸኙ ከወራት በኋላ እንደሆነ የባልደራስ ሚዲያ ክፍልን ጠቅሶ የዘገበው አሚማ ነው ፡፡ ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት:- ዩትዩብ፤ https://www.youtube.com/channel/UCsfBw4xrhJzdMTzhWk_uX2A… ቴሌግራም፤ https://t.me/asharamedia24 Twitter https://twitter.com/AsharaMedia?s=09

Source: Link to the Post

Leave a Reply