
በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው ኤርትራዊው ኪዳኔ ዘካሪያስ ሀብተማርያም ሱዳን ውስጥ በዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል ተያዘ። ኢንተርፖል የኤርትራዊውን ሕገ-ወጥ ሰው አዘዋዋሪ በቁጥጥር ሥር ማዋል የቻለው ያገኘውን መረጃ መሠረት በማድረግ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ሌሎች አገራት በወሰዱት እርምጃ መሆኑን አስታውቋል። ግለሰቡ ኢትዮጵያ ውስጥ በሌለበት የተፈረደበት ሲሆን፣ ሁለት ጊዜ በኢንተርፖል የእስር ማዘዣ ወጥቶበታል።
Source: Link to the Post