ከአዲስ አበባ 104 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ጥቃት ፈጸሙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአዲስ አበባ 1…

ከአዲስ አበባ 104 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ጥቃት ፈጸሙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአዲስ አበባ 104 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የሉና አትክልትና ፍራፍሬ እርሻ ሰራተኞች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቋል። ምንጮች እንደገለጹት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች፣ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ሊበን ጭቋላ ወረዳ ውስጥ የሚገኘውን የሉና እርሻ ለተለያዩ አገልግሎቶች ይጠቀምባቸው የነበሩ መሠረተ ልማቶችን አውድመዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የድርጅቱ ሥራ የተስተጓጎለ ሲሆን፣ በጥቃቱ የተደናገጡ በአካባቢው የሚገኙ ሌሎች ትልልቅ የአበባ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች ሥራቸውን ለማከናወን መቸገራቸው ተጠቁሟል፡፡ ከቆቃ ከተማ 14 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሉና እርሻ ይዞታ ውስጥ ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት በቦታው ላይ የተገኘ ቢሆንም፣ ከቀናት በኋላ መልሶ በመውጣቱ የሉና ሠራተኞች ተረጋግተው ለመሥራት ባለመቻላቸው ሥራው ሊስተጓጎል መቻሉንም ምንጮች ገልጸዋል ሲል ንስር ብሮድ ካስት ዘግቧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply