You are currently viewing ከአዴሃን የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከመስከረም 20-22/01/2015 ዓ.ም በባ/ዳር ከተማ ባካሄደው ስብሰባ በተለያዩ የክልላችንና ሀገራ…

ከአዴሃን የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከመስከረም 20-22/01/2015 ዓ.ም በባ/ዳር ከተማ ባካሄደው ስብሰባ በተለያዩ የክልላችንና ሀገራ…

ከአዴሃን የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከመስከረም 20-22/01/2015 ዓ.ም በባ/ዳር ከተማ ባካሄደው ስብሰባ በተለያዩ የክልላችንና ሀገራችን ያለበትን ወቅታዊ እና ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ጥልቅ ውይይት አድርጓል። አዲኃን ከህወሃት ከሥልጣን መልቀቅ ቀደም ብሎ የአማራን ህዝብ ጥያቄወች በትጥቅ ትግል አማራጭ በመታገል ጨቋኙን ስርዓት ለማስወገድ መስዋዕትነት ሲከፍል ከቆየ በኋላ የህወሃትን መወገድ ተከትሎ በመጣው ሀገራዊ ለዉጥ ከፊል አባላቱን በአማራ ክልል የፀጥታመዋቅር ውስጥ በማስገባት ከፊሉን ደግሞ በህጋዊ ፓርቲ አባልነት በማስቀጠል የሰላማዊ ትግልን እያደረገ ይገኛል።በዚህ አሰላለፍም በሀገራችን ላይ የሚቀጣውን ማነኛውም የውስጥና የውጭ ጠላት ለመከላከል በሚደረግ ትግል ሁሉ በግንባር ቀደምትነትተሰልፎ ይገ…ኛል፡፡ የድርጅቷ አባላት ጦር ሜዳ ግንባር ድረስ በመሄድ ተዋግተዋል መስዋትነት ጭምር በመክፈል ወራሪ ሀይልን በመፋለም ላይ ይገኛሉ፡፡ስራ አስፈፃሚው በዉይይቱ እንዳረጋገጠው በአማራ ሕዝብ ላይ በተከፈተበት ዘርፈ ብዙ እና መዋቅራዊ ጥቃት ምክንያት በህዝቡ ላይእየደረሰ ያለው የዘር ማጥፋት፣ መፈናቀል፣ ጦርነት እና ወረራ እንዲሁም እስራት እና የመንቀሳቀስ መብትን መገደብ ጨምሮ በህዝቡ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ተባብሰው ቀጥለዋል። በተለይም በወለጋ ያለ ማቋረጥ የሚደረገው የዘር ጭፍጨፋ፣ በሰሜን ወሎ እና ሰሜን ጎንደር አካባቢ ለ3ኛ ግዜ የተከፈተው ጦርነት፣ የአማራ ህዝብ ወደ አዲስ አበባ የሚገባባቸው መንገዶች ላይ የሚደርስ መንገላታት፣ እንዲሁም እሥራት እንግልት በእጅጉ አሳስቦናል። በመሆኑም የአዴኃን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለህዝብ፣ ለመንግስት እና ለፖለቲካ ኃይሎች ቀጥሎ የተቀመጡትን ጥሪዎች ያቀርባል:- 1/ በየትኛውም የሀገሪቱ አከባቢ ዘርና ማንነት መሠረት ተደርጎ የሚሰነዘር ጥቃት በማስቆም ረገድ ትልቅ ኃላፊነት ያለበት የፌደራል መንግስት ኃላፊነቱን እንዲወጣ፥ በቀጥታምይሁን በተዘዋዋሪ በአማራው ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲፈፀም ምክንያት የሆኑ የፌደራል ና የኦሮምያ ክልል ባለስልጣናት ላይ ህጋዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃ እንዲወስድ፥ 2/ የአማራን ህዝብ ወክለን የምንቀሳቀስ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች በህዝባችን ላይ እየተቃጣ ያለው ሁለንተናዊ ጥቃት በጥልቀት በመገምገም እና የችግሩን ስፋት እና ጥልቀት የሚመጥን አረዳድ በመያዝ ከፖለቲካዊ መሽኮርመም እና አድር ባይነት ወጥተን እንደአደረጃጀታችን ባህሪ እና ቁመና በህዝባችን ላይ የደረሰውን ሰቆቃ ሊያስቆም የሚችል ጠንካራ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንድናደርግ ማሳሰብ እንወዳለን፡፡ 3/ በሀገራችን ዋና ከተማ እና የፌደራል መንግስት መቀመጫ የሆነችውን አዲስ አበባን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ አቅሟን በአንድ ብሔር ልሂቃን ስር ለመጠቅለል እየተሰራ ያለው ህገ ወጥ ተግባር እንዲቆም ፥ እንዲሁም ከተለያዩ የአማራ ግዛቶች ወደ አዲስ አበባ የሚደረግን ጉዞ በማስተጓጎል በህዝቡ ላይ ስነ ልቦናዊ ቀውስ ለማምጣት እና በገንዛ ከተማው ባይተዋር ለማድረግ የሚደረገው አፀያፊ ተግባር በአስቸኳይ እርማት እንዲሰጥበት እናሳስባለን። 4/ ከላይ የተነሱትንእና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የአመለካከት እና የተግባር አንድነት ፈጥሮ መታገል ይቻል ዘንድ የአማራ ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች የጋራ መድረክ ፈጥረው ምክክር የሚያደርጉበትን ሁኔታ መፍጠር ይቻል ዘንድ ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች የበኩላቸዉን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ እናቀርባለን። 5/ በመጨረሻም በሀገርም ሆነ በውጭ ላላችሁ የአማራ ተወላጆችና እና የትግላችን ደጋፊዎች በተለይም ለአማራ ህዝብ እና ለመላው ኢትዮጲያ ህዝብ እኩልነት እና ለፍትህ የምናደርገውን ትግል አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እያረጋገጥን ፓርቲያችንን በሞራል፣ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ ጭምር እንድትደግፉን እና ትግሉን እንድትቀላቀሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ለአማራ መታገል ለኢትዩጵያ መታገል ነው!!! መስከረም 27 ቀን 2015 ዓ.ም ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply