
ባለፈው የካቲት ወር መጨረሻ ገደማ በምሥራቃዊ ኡጋንዳ ከሚገኘው ሴሬሬ ከሚባለው አካባቢ ከ250 በላይ ሰዎች የደረሱበት ሳይታወቅ መሰወራቸው መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ከሳምንት በኋላ ግን ወደ ኢትዮጵያ ማቅናታቸው ተሰምቶ ለምን የሚል ጥያቄ ተነስቷል። ጉዟቸውም በአካባቢያቸው ከሚከሰት የምጽአት ቀን ጥፋት ለመሸሽ እንዲሁም ለሃይማኖታዊ ተልዕኮን ምክንያት ያደረገ ነው እየተባለ ነው። ኡጋንዳውያን ከአገራቸው ተሰውረው እንዴት ደቡብ ኢትዮጵያ ሊደርሱ ቻሉ?
Source: Link to the Post