ከአፈር ማዳበርያ ስርጭትና ከወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ ጋር በተያያዘ ያለአግባብ የተመዘበረ 46ሚሊዮን ብር ማስመለሱ ዞኑ አስታወቀ።የጉራጌ ዞን ፍትህ መምርያ ያለአግባብ ተመዝብሯል ያለውን የመ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/BRCEcXGuSsgY0jWn5JtnSWwJw7RXnKFTCVy_GM_p2OknJRyKzjVZm4a0lIejhToJpbpa-wCwHo3F6fxMNMdihW-SAGol0chs09uNQQ6uWwYpo6QXsqCempKwOdeJgMjSydlAkU2vZSzSg3RCZDs6CMztM6NpKpghoa33rC7rkbNjBMDpF3Pee_BauQuCONaudEHoeIlHr9_RBUGBkAV1fTdLjZFLO4Umg8f_sknWTUJbu0OYtfm-X6lPmymmGemStoz1mC1TEVg51muDgWE1Free8Gf0TaFUp4XnmZcwedAttqoJItKFAkLaAFOXiEAWl3Z9paHra-3yPoOtyWuXrw.jpg

ከአፈር ማዳበርያ ስርጭትና ከወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ ጋር በተያያዘ ያለአግባብ የተመዘበረ 46ሚሊዮን ብር ማስመለሱ ዞኑ አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን ፍትህ መምርያ ያለአግባብ ተመዝብሯል ያለውን የመንግስትና የህዝብ ሃብት በክስ ማስመለሱን አስታውቋል።

በዞኑ ከአፈር ማዳበርያ፣ ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ መደበኛ ስርጭት፣ ከወጣቶች ብድር ተዘዋዋሪ ፈንድ ጋር ያለአግባብ የተመዘበሩ ከ46ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስትና የህዝብ ሃብት በክስና በድርድር ማስመለስ እንደተቻለ ታውቋል።

የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ኤሊያስ ሰብለጋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በዞኑ ባለፊት 6ወራቶች ከ7መቶ በላይ የወንጀል ምርመራዎች በማጣራትና ለፍርድ ቤት በማቅረብ ውሳኔ እንዲሰጥባቸው ተደርጓል ብለዋል።

እነዚህም የግድያ፣ የውንብድና የዘረፋ፣ ቀላልና ከባድ የስርቆት፣ የሴቶች አስገድዶ የመድፈር፣ የግድያና ሌሎችም ወንጀሎች መሆናቸውን ሃላፊው ተናግረዋል።

በዞኑ በባለፉት 6 ወራቶች የጸጥታ ችግሮች እንደነበሩ ገልጸው በተለይም የግድያ፣ የውንብድና የስርቆትና ሌሎችም በየደረጃው የተፈጸሙ ወንጀሎች ተገቢውን የህግ ምርመራ ተደርጎባቸው ውሳኔ እንደተሰጠባቸውም ጠቁመዋል።

ከዚህም ባለፈ በየደረጃው የተፈጸሙ ቀላልና ከባድ የሙስና ወንጀሎች ተጣርተው ለህግ እንዲቀርቡ መደረጉን አስረድተዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

የካቲት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply