ከአፋር የተሻገሩ የተባሉ ታጣቂዎች ትግራይ ዉስጥ 7 ሰዎችን መግደላቸው ተገለጸ፡፡ከዓፋር ክልል ዘልቀው ገቡ የተባሉ ታጣቂዎች በትግራይ ክልል ራያ ዓዘቦ በከፈቱት ጥቃት በትንሹ ሰባት ሰዎችን…

ከአፋር የተሻገሩ የተባሉ ታጣቂዎች ትግራይ ዉስጥ 7 ሰዎችን መግደላቸው ተገለጸ፡፡

ከዓፋር ክልል ዘልቀው ገቡ የተባሉ ታጣቂዎች በትግራይ ክልል ራያ ዓዘቦ በከፈቱት ጥቃት በትንሹ ሰባት ሰዎችን መግደላቸው ተነግሯል፡፡

ጥቃቱ የደረሰበት የራያ ዓዘቦ ወረዳ የጋራርሳ ነዋሪዎችና የአካባቢዉ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት፣ ከሟቾቹ አብዛኞቹ ሕፃናትና ልጆች ናቸዉ።
በነዋሪዎቹ አስተያየት መሠረት፣ ሟቾቹ ግጦሽ መሬት ላይ ተኝተዉ የነበሩ የከብት እረኞች ናቸዉ።

የጋራርሳ አካባቢ ነዋሪዎች እንዳሉት፣ አካባቢዉን ከአፋር ክልል ጋር በሚያዋስነዉ ድንበር አሁንም ድረስ በሁለቱ ክልሎች ሚሊሻዎች መካከል የተኩስ ልዉዉጥ ሲደረግ ነበር።

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ጥቃቱን አዉግዟል።

አስተዳደሩ ባወጣዉ መግለጫ ጥቃቱን የከፈቱትን ታጣቂዎች ለመለየት ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታዉቆ፣ ተጠርጣሪዎቹን ለፍርድ ለማቅረብ የዓፋር ክልላዊ መንግስት እና የፌደራል ፖሊስ ሐላፊነታቸው እንዲወጡ ጠይቋል።
ዘገባዉ የዶቼቨሌ ነው

Source: Link to the Post

Leave a Reply