ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ!!       አሻራ ሚዲያ     ጥቅምት 26/2013ዓ.ም ባህርዳር  አገርና ህዝብን ለማጥፋት የተነሳውን የህወሃት ወንበ…

ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ!! አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 26/2013ዓ.ም ባህርዳር አገርና ህዝብን ለማጥፋት የተነሳውን የህወሃት ወንበ…

ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ!! አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 26/2013ዓ.ም ባህርዳር አገርና ህዝብን ለማጥፋት የተነሳውን የህወሃት ወንበዴ ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በመደገፍ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጎን እንሰለፋለን! ድርጅታችን የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ ቡድን በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግር እንደማያደርግ ቀድሞ በመረዳት ለስልጣን በበቃበት ቋንቋ ለማናገር የትጥቅ ትግል የጀመረ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። ዓላማውም ኢትዮጵያ በታሪኳ በመሳሪያ ሃይል የሚገዛን መንግስት በመሳሪያ ሃይል አውርዶ በተመሳሳይ መንገድ የሚገዛበት ሂደት ማብቃት አለበት፥ ሂደቱ ሊሳካ የሚችለውም ሆነ በህዝብ ዘንድ አመኔታ ሊያገኝ የሚችለው የአባት አያቶቻችን የአርበኝነት አርማ ስናነግብ ነው። በሚል ከተለያዩ የብሄርና አገራዊ ድርጅቶች በመዋሃድ በ1993 ዓም ተመስርቶ የወያኔው ቡድን የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል። ከገዥው ቡድን የወጣው የለውጥ ቡድን ጥሪ ተቀብሎ ወደ ሰላማዊ መንገድ በመግባትም ሰራዊቱ ለውጡ እንዳይደናቀፍና የአማራ ህዝብን በማንነቱ እየደረሰበት ያለውን መከራ ለመመከት ከመንግስት ጎን ለመቆም በመወሰን 200 የሚሆኑ አርበኞችን በልዩ ሃይል ውስጥ ታቅፈው በተለያዩ ወታደራዊ ግዳጆች ላይ በመሰማራት አስፈላጊውን መስዋዕትነት የከፈሉ ሲሆን፥ አሁንም በአማራ ክልል ሰርጎ የገባውን የህወሃት ቡድን በመፋለም ላይ ይገኛል። አገሪቱን እየመራ ያለው ቡድንም የዘገየ ቢሆንም በዚህ ዘረኛ ቡድን ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዙ የሚደግፍ መሆኑን እየገለጽን፥ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጎን ለመሰለፍ የወሰነ መሆኑን በታላቅ የአርበኝነት መንፈስ ዝግጁ መሆናችንን እናስታውቃለን። መንግስትም በትግል ላይ የነበርነው የሰራዊት አባላት ወደ መደበኛ ህይወታቸው እመልሳለሁ በሚል የገባውን ቃል ባያከብርም ፥ ቀድሞም በአርበኝነት የተነሳን፥ አርበኝነት ደግሞ የማይጠብቅ የማይጠይቅ አገርና ህዝብ አደጋ ላይ በወደቁ ጊዜ ፈጥኖ የሚደርስ መሆኑና ከአገር በላይ ደግሞ የሚበልጥ ባለመኖሩ ከመንግስት ጎን ለመሰለፍ ዝግጁ መሆናችንን እያስታወቅን የፌደራልም ሆነ የአማራ ክልል መንግስት ሁኔታዎችን እንዲያመቻችልን እንጠይቃለን። ውርሳችን አርበኝነት ትርፋች ታሪካዊነት ነው! የሚል መፈክርህን አንገበህ ለ18 ዓመታት ዋጋ የከፈልከው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን ለመሰለፍ ራስህን እንድታዘጋጅና በተጠንቀቅ ላይ እንድትሆን እያሳሰብን ቀጥዩን ሂደት የምናሳውቅ መሆናችንን እንገልጻለን። ውርሳችን አርበኝነት ትርፋችን ታሪካዊነት ነው!!! የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ጥቅምት 26/2013 ዓም

Source: Link to the Post

Leave a Reply