ከኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሚደርሰዉ የኤች አይ ቪ መድሃኒት መቆራረጥ እንዳለዉ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡ከኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሚደርሰዉ የኤች አይ ቪ መድሃ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/v515t9lLXrfb4Q_DAS4ytEfeK_kLJGm6jHWHiy3Ay7kSA7oKSgzVJU5fDAwJuRJBUJd-uFiu4zLWl7Zrx5CDH-A4XG1Qr1Yw4-mIH_p6PaCspOipDSqTt9GtzlPpIjuRjnjLj0gp4_HkZjKWfRYBMMwILwgnm_AmZ4n4iUIt5ZXiCYJHhmytFGZNeaONrFyISwTG4GR0XUncQV_EfNwVUVLQSOL0BxNYEbtj95Xtw5ryhjpfuvo_lNE81v06YRlFiXCbbW6NUWDl5h5BmxZVnt2O8x66AQzojeCfbEKvSjShOtf_zaCRW8rU3a7ahA_zIe5EdIiWtsEpSzFEJjoCIw.jpg

ከኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሚደርሰዉ የኤች አይ ቪ መድሃኒት መቆራረጥ እንዳለዉ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡

ከኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሚደርሰዉ የኤች አይ ቪ መድሃኒት አልፎ አልፎ መቆራረጥ እንዳለው የኦሮሚያ ጤና ቢሮ አስታውቋል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ ዶ/ር ጉሻ በለኮ የኤች አይ ቪ መድሃኒት አቅርቦት ‹‹ከሞላ ጎደል ጥሩ ነዉ››ያሉ ሲሆን፤ አልፎ አልፎ የመድሃኒት መቆራረጥ ይከሰታል ብለዉናል፡፡

‹‹ኤች አይ ቪ በጣም ሴንሴቲቭ ነገር ነዉ›› ያሉት ሃላፊዉ ፤ መድሃኒቱን ለሁለት ቀናት እንኳን ማቋረጥ ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል የሚታወቅ ነዉ ብለዋል፡፡

በ2015 የመጀመሪያዉ ግማሽ ዓመት የመድሃኒት አቅርቦት መቆራረጥ አስቸጋሪ ሆኖ ነበር ያሉት ዶ/ር ጉሻ ፤በዚህኛዉ ዓመት ግን ብዙም ችግር እንዳልነበር ነው የገለፁት፡፡

የመድኃኒት መቆራረጡ አገር ውስጥ ባለው የተለያየ ችግር ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ጉሻ ፤ ይህን ችግር ለመፍታት ከጤና ሚኒስቴር እና መድኃኒት አቅራቢ አገለግሎት ጋር እየሰራን ነው ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል ወደ 158ሺህ ሰዎች የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደማቸዉ ዉስጥ አለ ተብሎ እንደሚገመት ነግረውናል።

ባለፉት 6 ወራትም 7ሺህ አዳዲስ ሰዎች በኤች አይ ቪ መያዛቸዉን ገልፀዋል።

በእስከዳር ግርማ

የካቲት 01 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply