ከኢትዮጵያ ባንክና ፋይናንስ ዘርፍ አሰራር ውስጥ የብልፅግና ፖለቲካ ጣልቃገብነት ያብቃ!!!

ኢትዮጵያ  በኤቲኤም ማሽኖች ስርጭትና ድርሻ  ከዓለም 179 አገራቶች 178ኛ ደረጃ አገኘች !!!    (ክፍል ሁለት)    ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

ለዲጂታል ባንኪንግ ፀሓይ ወጣች!   The Sun Is Rising on Digital Banking in  Ethiopian

በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ለሚገኙ አስተማሪዎችና ተማሪዎች ለውይይት የቀረበ ቁንፅል መነሻ ጥናት

የመንግሥት የፖለቲካ ጣልቃገብነት  ከባንክ አሰራር ውስጥ ይውጣ!!!

 • ኢትዮጵያ46 (ከአንድ በታች) ኤቲኤም ማሽን ለመቶ ሽህ ሰዎች  የነፍስ ወከፍ ድርሻቸው ነው፡፡
 • ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ 580 ወረዳዎች 37 በመቶው የአንድም ባንክ ቅርንጫፍ የሌላቸው መሆኑን ነው፡፡ ይህ ማለት ካሉት 18 ባንኮች በ580 ወረዳዎች ውስጥ አንድም ቅርንጫፍ የሌላቸው መሆኑን ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ 14,500 ቀበሌዎች ሲኖሩ፣ በእነዚህ ቀበሌዎች ውስጥ ማክሮ ፋይናንሶችና ኤጀንቶች ተደምረው መድረስ የቻሉት ሁለት ሺሕ ቀበሌዎች አይሞላም፡፡ ስለዚህ 13 ሺሕ ቀበሌዎች የፋይናንስ አገልግሎት ምን እንደሆነ አያውቁም ማለት ነው፡፡›› አቶ ተክለወልድ አጥናፉ …….(1)
 • ከሠላሳ አመት የባንክ ገዢነት በኃላ እንዲህ ዓይነት ሪፖርት ማቅረብ የሁሉም የባንክ ሹማምንቶች ችግሩን እንጂ መፍትሄውን የማያመላክቱ፣ ለሚሠሩት ተጠያቂነት የማይወስዱ፣ ለሚመጣው መንግሥት ሁላ አጎብድደው አንዴ የኢህአዴግ አንዴ የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ካድሬ በመሆን ዘመናቸውን የጨረሱ አድርባይ ምሁራን ለመሆናቸውና ለግል ጥቅማቸው ብቻ የሚሮሮጡ ለመሆናቸው  መኃላ አያሻም!!!
 • Limitations and Exceptions: Population-based ratios of the number of branches and ATMs assume a uniform distribution of bank outlets within a country’s area and across its population, while in most countries bank branches and ATMs are concentrated in urban centers of the country and are accessible only to some individuals.

የሰው ኃይል ልማት ሳይደረግ የሠላሳ ስድስት ወለል ፎቅ ግንባታ ያስጀመሩት የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ግብረ አበሮቻቸው  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በመሰየማቸው ያለፈው የባሌስትራ ወርቅ ቅብ የሙስና ስራቸው እና ሃገሪቱን በብድር እዳ ከተው ሳይጠየቁ ዛሬ የባንክ ሙያተኛውን የተተኪ ድርቀት በማለት እነዚህ የፖለቲካ ካድሬዎች በህወሓት፣ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደኢህዴን ካድሬነት ባንኮቹ እንደሚዘወሩ የጠፋቸው ይመስላል፡፡ ብዙ የባንክ ሙያተኛ የናንተን የበሰበሰ ፖለቲካ ውስጥ ስላልገባ ሥልጣን አልተሰጠውም እንጂ በሃገር ውስጥና ከባህር ማዶ ያሉ የባንክ ሙሁራንን አላሰራም ብለችሁ እንጂ የተተኪ ድርቀት ኖሮ አይደለም፡፡  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ዋና ቢሮ ባለ 46 ወለል ያለው ፎቅ የግንባታው ወጪ በ266.5 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ወይም 6 ቢሊዩን 129 ሚሊዩን 500 ሽህ  ብር ኮንትራክተር፤ የቻይና መንግስት የኢንጅነሪንግ ግንባታ ኮርፖሬሽን China State Construction engineering Corporation (CSCEC)፤ በአዲስ አበባ ከተማ ሥራው ተጠናቆ ለምርቃት ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲከኞች እንደ ምርጫ ቅስቀሳ ሸር ጉድ በማለት ለምረቃ በዓሉ ሃመሳ ሚሊዩን ብር በላይ በማውጣት በአገር አቀፍ ደረጃ ለማስመረቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ የሃገሪቱ ዜጎች ከአምስት ሚሊዮን ህዝብ በላይ  አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡

 

 • አቶ ተክለወልድ አጥናፉ እንዳሉት ‹‹ባንኩ ሥር ነቀል ለውጥ ያስፈልገዋል ከተባለ የሰው ኃይሉንም መፈተሽ አስፈላጊ በመሆኑ፣ የሰው ኃይል ፖሊሲውም እየታየ ነው፡፡ ቦርዱ ከዚህ ቀደም አንድ ሺሕ ተተኪ አፍርተናል የሚል ሪፖርት ተመልክቶ የነበረ ሲሆን፣ ወደ ውስጥ ሲገባ ግን የተተኪ ድርቀት ያለበት መሥሪያ ቤት መሆኑ ታይቷል፡፡ 67 ሺሕ ሠራተኛ ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ከዚህ ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑት ባለዲግሪ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ማስተርስ ያላቸውን ቢሆኑም የተተኪ ድርቀት አለበት፡፡ባንኩ አለበት ያሉትን የተተኪ ድርቀት ያሳይልኛል ብለው የጠቀሱት አንድ ባንኩን በፕሬዚዳንትነት የሚመራ መጥፋቱ ነው፡፡ አንድ ፕሬዚንት ማፍራት ባለመቻሉም ፕሬዚዳንት ከሌላ ባንክ ተለምነው መጥተዋል፡፡ ስለዚህ ቀጣይ የቦርዱ የፕሬዚዳንቱ የከፍተኛ ማኔጅመንቱ ዳይሬክተር እስከ ሦስት ዓመት ድረስ ተተኪ የማፍራት ሥራ ዋነኛ ጉዳይ ይሆናል፡፡››
 • ‹‹የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደስሙ ኢትዮጵያን መምሰል እንደሚገባው አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ ባንኩ የአንድ ክልል ምክር ቤት ወይም ካቢኔ ሊሆን ስለማይችል ከሁሉም የተውጣጣ ሠራተኛ መኖር መሆን አለበት ብለዋል፡፡››አቶ ተክለወልድ አጥናፉ በባንክ ውስጥ የፖለቲካ ሥራ በማስጀመር በኢህአዴግ ዘመን  በህወሓት፣ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደኢህዴን የፖለቲካ ካድሬዎች በማጨቅ እንዲሁም በብልፅግና ዘመን የኦዴፓ፣ አዴፓ እና ደኢህዴን ካድሬዎች ባንኮቹን በእውቀት ሳሆን በካድሬነት እንደ ባጫ ጊና ዘረኛና ተረና ባንኩን በኦህዴድ ኦደፓ አባሎች ሞልቶ ሲሄድ ተክለወልድና ካቤኔዎቹ ሥር ነቀል የሚሉት የይስሙላ ለውጥ ነው፡፡ በወያኔ ዘመን የተደረገውን ኦዴፓ ብልፅግና በተራኛነት የኦሮሞ ካድሬዎች ባንኮቹን እንደሚዘውሩ እንኳን የባንክ ባለሙያዎች ህብረተሰቡም ያውቃል እንላለን፡፡ በባንክ ስር ነቀል ለውጥ እንዲመጣ ካስፈለገ የመንግሥት የፖለቲካ ጣልቃገብነት ከባንክ አሰራር ውስጥ ይውጣ እንላለን፡፡ ከኢትዮጵያ ባንክና ፋይናንስ ዘርፍ አሰራር ውስጥ በፊት ኢህአዴግ በኃለም የብልፅግና ፖለቲካ ጣልቃገብነት ይውጣ!!! ለዚህ ነው በኤቲኤም ማሽኖች ስርጭትና ድርሻ  ከዓለም 179 አገራቶች ኢትዮጵያ 178ኛ ደረጃ ያገኘችው !!! የኢትዮጵያ የባንክ ሙያተኞችም የሻገተ የፖለቲካ ካድሬ የሆኑ የባንክ አመራርን በትግላችሁ ፈንቅላችሁ ባንኮቹን ለማዳን ለህዝብ የገባችሁትን ቃል ኪዳን  በእውነተኛ የሥር ነቀል ትግል ማድረግ ይጠበቅባችኃል፡፡ የባንኩን የገማ የፖለቲካ ካድሬ አመራሮች አሰራር በማጋለጥ ዘረኛና ተረኛነትን ለልጆቻችሁ ላለማስተላለፍ  በሥር ነቀል ትግል ለመፋለም ብዕራችሁን አንሱ እንላለን!!!

 

በአውቶማቲክ ቴለር ማሽኖች (ኤቲኤም) አስራአንድ ጠቀሚ አሰራሮች ለዓለም ህዝብ አበርክተዋል፡፡ እነሱም  ፈጣን አገልግሎት፣ ተስማሚ፣ ሃያ አራት ሰዓት የሚሠራ፣ የደንበኛው አድራሻ ቦታ የትም ቢሆን የማይገደው፡፡ በተጨማሪ በኤሌክትሮኒክ ባንኪንግ ባንኩ አገልግሎት በመስጠት  አስተማማኝና ዘለቄታዊ አገልግሎት በርካሽ ዋጋ ይሰጣል፡፡ ለምሳሌ፡- በጡብና ሞርታል የባንክ አገልግሎት ዘመን አንድ ደንበኛ የአገልግሎት ወጪ አንድ ዶላር ሲሆን ደንበኛው በስልክ ከተገናኘ ስልሳ ሣንቲም ይከፍላል፡፡ በዘመናዊው ኤሌክትሮኒክ ባንኪንግ የገፅ ለገፅ አገልግሎት ወጪው ዚሮ ነጥብ ዚሮ ሁለት ሣንቲም  ብቻ ነው፡፡  ‹‹The Electronic banking has been around for some time but in form of Automatic Teller Machines (ATMs) and telephone transactions. More recently, it has been transformed by the Internet and mobile technologies, the new delivery channels for banking services with 11 benefits to both customers and banks. Access is fast, convenient, and available around the clock, whatever the customer’s location. Additionally through Electronic banking, the banks are able to provide services more efficiently and at substantially lower costs. For example, a typical customer transaction costing-about $1 in a-traditional- “brick and mortar” bank branch or $0.60 through a phone call costs only about $0.02 online (Crane, 1996).››

በ2009 ዓ/ም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት አውቶማቲክ ቴለር ማሽኖች (ኤቲኤም) 1,700 (አንድ ሽህ ሰባት መቶ) ብቻ ናቸው፡፡ ከአጠቃላይ የህዝብ ብዛት ጋር ሲካፈል አንድ ኤቲኤም ማሽን 54,117 (ለሃምሳ አራት ሽህ አንደ መቶ አስራሰባት) ሰዎችን ያገለግላል፡፡ በዓለም አገሮች አማካይ አንድ ኤቲኤም ማሽን 2,325 (ለሁለት ሽህ ሦስት መቶ ሃያ አምስት) ሰዎች ያገለግላል፡፡ ኢትዮጵያ ሃገራችን ለ110 (መቶ አስር) ሚሊዮን ህዝብ የአለም አማካይ ላይ ለመድረስ 47,312 (አርባ ሰባት ሽህ ሦስት መቶ አስራ ሁለት) ተጨማሪ ኤቲኤም ማሽኖች አገራችን ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል ማለት ነው፡፡ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ከመቆለል ኤቲኤም ማሽኖች አገራችን ውስጥ አስገብቶ በማሰራጨት የብዙ ቅርንጫፍ ባንኮች ሥራ በመስራት ባገለገሉ ነበር እንላለን፡፡ ‹‹ There are about 1,700 ATMs in Ethiopia, making the ATM to population ratio 1: 54,117, well below the world average of 1:2325.Jan 24, 2017 (https://addisfortune.net › columns › atm-woes-plague-cust…)››

በአሜሪካ ሃገር 470,135 ኤቲኤም ማሽኖች ሲኖሩ 181,741 በባንክ ኃብትና ንብረት ሲሆኑ 278,394 የነፃ የግል ዘርፍ ሃብት ነው:: (Currently, there are approximately 470,135 ATMs in the U.S., with 191,741 bank-owned and 278,394 independent.) በኢትዮጵያም የባንኮችና የግል ዘርፍ ኤቲኤም ማሽኖች እንዲኖሩ በማድረግ ልዩነቱን ማጥበብ ይቻላል እንላለን፡፡

ደቡብ ኮሪያ 282 ኤቲኤም ማሽኞች ለመቶ ሽህ ሰዎች፣ ካናዳ 205፣ ፖርቱጋል 185፣ ጀርመን 118   ኤቲኤም ማሽኞች ለመቶ ሽህ ሰዎች የስርጭት ድርሻ አላቸው፡፡ በቻይና 1.1 (አንድ ነጥብ አንድ) ሚሊዮን ኤቲኤም ማሽኖች ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ 0.46 (ከአንድ በታች)  ኤቲኤም ማሽን ስርጭት  ለመቶ ሽህ ሰዎች  ይደለደላል፡፡ 
ኤቲኤም ማሽኖች ስርጭትና ድርሻ  ከዓለም 179 አገራቶች ኢትዮጵያ 178ኛ ደረጃ አገኘች !

 • በ2013ዓ/ም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መረጃ መሠረት በሃገሪቱ ለዘመናዊ የባንክ አገልግሎት የሚጠቀምባቸው በዚህ መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት አውቶማቲክ ቴለር ማሽኖች (ኤቲኤም) 3,083 (ሦስት ሽህ ሰማንያ ሦስት) አድጎል፡፡ ከአጠቃላይ የህዝብ ብዛት ጋር ሲካፈል አንድ ኤቲኤም ማሽን 35,680 (ለሠላሣ አምስት ሽህ ስድስት መቶ ሰማንያ) ሰዎችን ያገለግላል፡፡ በዓለም አገሮች አማካይ አንድ ኤቲኤም ማሽን 2,325 (ለሁለት ሽህ ሦስት መቶ ሃያ አምስት) ሰዎች ያገለግላል፡፡ ተጨማሪ 47312 (አርባ ሰባት ሽህ ሦስት መቶ አስራሁለት) ኤቲኤም ማሽን የግሉ ዘርፍ ከአስር ሽህ  እስከ ሃያ ሰባት ሽህ ዶለር  ገዝቶ በማስገባት የዓለም አማካይ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰው በሚበዛባቸው በተመረጡ የከተማ ቦታዎች ውስጥ ለግሉ ዘርፍ በሆቴሎች፣ ግሮሰሪዎች፣ ሱፐርማርኬቶች፣ ሬስቶራንቶች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች፣ ነዳጅ ማደያዎች ወዘተ አዲስ ኤቲኤም ማሽን የሥራ ዕድል መፍጠር ይችላሉ እንላለን፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የግሉ ዘርፍ ኤቲኤም ማሽኖች አስገብቶ እራሱንም አገሩንም እዲጠቅም ማድረግ፣ በአንድ ኤቲኤም ማሽን የሚገኘውን የኮሚሽን ገቢ በወር ከ14,400 (አስራ አራት ሽህ አራት መቶ) እስከ 24,000 (ሃያ አራት) ሽህ ብር ገቢ ማስገኘቱን በማሳወቅ፣
 • This means if your ATM does 3 – 4 transactions per day you could earn between $180 and upto $360 or more per month. If your ATM falls in the average usage of 6 – 7 per day, and you charged $2.50 you would earn between $15 – $17.5 per day, at $3.00 you would earn over $20 per day or between $360 – $600 per month. አንድ ዶለር 42.30 ተሰልቶ 15228 ብር እስከ 25380 ብር በወር የግሉ ዘርፍ ሊያገኝ ይችላል፡፡ 47312 (አርባ ሰባት ሽህ ሦስት መቶ አስራሁለት) ኤቲኤም ማሽን የግሉ ዘርፍ  ወደ አገር ቤት ካስገባ በዚሁ መጠን ለጠባቂና ለዘበኛ የሥራ እድል ይፈጥራል፡፡

በ2013 ዓ/ም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መረጃ መሠረት በሃገሪቱ ለዘመናዊ የባንክ አገልግሎት የሚጠቀምባቸው በዚህ መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት አውቶማቲክ ቴለር ማሽኖች (ኤቲኤም) 3,083 (ሦስት ሽህ ሰማንያ ሦስት) አድጎል፡፡ ከአጠቃላይ የህዝብ ብዛት ጋር ሲካፈል አንድ ኤቲኤም ማሽን 35,680 (ለሠላሣ አምስት ሽህ ስድስት መቶ ሰማንያ) ሰዎችን ያገለግላል፡፡ በዓለም አገሮች አማካይ አንድ ኤቲኤም ማሽን 2,325 (ለሁለት ሽህ ሦስት መቶ ሃያ አምስት) ሰዎች ያገለግላል፡፡

በአውቶሜትድ ቴለር ማሽኖች (ኤቲኤም) ከመቶ ሽህ አዋቂዎች (Automated teller machines (ATMs) (per 100,000 adults)) ከ179 የዓለም አገራቶች ደረጃ፣ የኢትዮጵያ 178ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ (ከሠንጠረዡ መመልከት ይቻላል)ኤቲኤም ማሽኖች ኮንቲውተራይዥድ የሆነ የቴሌኮሙኒኬሽን ስትራቴጂክ ፕላን ሲሆን ለፋይናንሻል ኢንስቲቲውሽኖች ደንበኞቹ በህዝባዊ ቦታዎች በማመቻቸት የሚሠጠው የገንዘብ ግብይይት አገልግሎት ነው፡፡ Definition: Automated teller machines are computerized telecommunications devices that provide clients of a financial institution with access to financial transactions in a public place.

ከጡብና አዳፍኔ ዘመን ወደ ዲጂታል ባንኪንግ ዘመን ለመሸጋገር በ2013ዓ/ም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መረጃ መሠረት በሃገሪቱ ለዘመናዊ የባንክ አገልግሎት የሚጠቀምባቸው አውቶማቲክ ቴለር ማሽኖች (ኤቲኤም) 3,083 (ሦስት ሽህ ሰማንያ ሦስት) እንደደረሰ ተገልፆል፡፡ በዚህም መሠረት በአንድ አገር የሚገኙ የኤቲኤም ማሽኖች  ስርጭት ለመቶ ሽህ ሰዎች የሚሠጡት አገልግሎት የሚመዘንበት መረጃ የሃገሪቱ ደረጃ የሚያሳይ ሪፖርት ነው፡፡ በዚህም መሠረት ሲሠላ በሃገሪቱ ውስጥ የሚገኘው ኤቲኤም ማሽኖች ቁጥር ሲባዛ ለመቶ ሽህ ሰዎች ሲካፈል ለጠቅላላው የህዝብ ብዛት አዋቂ ሰዎች ያካትታል፡፡ ስለዚህ 3,083 x 100,000=308,300,000/ሲካፈል ከጠቅላላ የህዝብ ቁጥር አዋቂ ሰዎች ይሆናል 0.46 ሆኖ የመቶ ሰባ ስምንተኛ ደረጃ ተሠጥቶታል፡፡

Statistical Concept and Methodology: Data are shown as the total number of ATMs for every 100,000 adults in the reporting country. Calculated as (number of ATMs)*100,000/adult population in the reporting country. …….(2)

 • ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት መቶ አስር ሚሊዮን ጋር ሲካፈል አንድ ኤቲኤም ማሽን 35,680 (ለሠላሣ አምስት ሽህ ስድስት መቶ ሰማንያ) ሰዎችን ያገለግላል፡፡ በዓለም አገሮች አማካይ አንድ ኤቲኤም ማሽን 2,325 (ለሁለት ሽህ ሦስት መቶ ሃያ አምስት) ሰዎች ያገለግላል፡፡ ተጨማሪ 47312 (አርባ ሰባት ሽህ ሦስት መቶ አስራሁለት) ኤቲኤም ማሽን የግሉ ዘርፍ ከአስር ሽህ  እስከ ሃያ ሰባት ሽህ ዶለር  ገዝቶ በማስገባት የዓለም አማካይ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡ፎቅ ከመገንባትና ሠራተኛ ከመቅጠር ወጪ አስወግዶ ኤቲኤም ማሽን በማስፋፋት ወደ ዲጂታል ባንኪንግ ቴክኖሎጂ ዘመን መሸጋገር የተሸለ አማራጭ ነው እንላለን፡፡
 • በኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንት ይህን ተጨማሪ 47312 (አርባ ሰባት ሽህ ሦስት መቶ አስራሁለት) ኤቲኤም ማሽን የግሉ ዘርፍ ከአስር ሽህ  እስከ ሃያ ሰባት ሽህ ዶለር  ገዝቶ በማስገባት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የንግድ ፍቃድ እየሠጠ በመላ ሃገሪቱ  ኤቲኤም ማሽን እንዲስፋፋ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
 • የ47312 ኤቲኤም ማሽን የግዢ ወጪ የአንዱ ኤቲኤም ማሽን ዋጋ በአስር ሽህ ዶላር ሲባዛ 473120000 ዶላር ወይም 19397920000 (19 ቢሊዮን 397 ሚሊዮን 920 ሽህ) ብር ይገመታል፡፡ (አንድ ዶላር በ41 ብር ሂሳብ ተሰልቶ)
 • የ47312 ኤቲኤም ማሽን የግዢ ወጪ የአንዱ ኤቲኤም ማሽን ዋጋ በሃያ ሰባት ሽህ ዶላር ሲባዛ 1277424000 ዶላር ወይም 52374384000 (52 ቢሊዮን 374 ሚሊዮን 384 ሽህ) ብር ይገመታል፡፡ (አንድ ዶላር በ41 ብር ሂሳብ ተሰልቶ)
 • የሃገር ውስጥና ዲያስፖራው ወገን ኤቲኤም ማሽን አስገብተው ራሳቸውንና ሃገራቸውን እንዲጠቅሙ ማድረግ የጊዜው አንገብጋቢ የዲጂታል ባንኪንግ የእድገት ጥያቄ ነው እንላለን፡፡
 • ተጨማሪ 47,312 (አርባ ሰባት ሽህ ሦስት መቶ አስራ ሁለት) ኤቲኤም ማሽን የግሉ ዘርፍ ወደ አገር ቤት ካስገባ በዚሁ መጠን ለባለኃብቱ፣ለጠባቂና ለዘበኛ በጠቅላላው (150,000) ለመቶ ሃምሳ ሽህ ሰዎች የሥራ እድል ይፈጥራል፡፡

Development Relevance: Access to finance can expand opportunities for all with higher levels of access and use of banking services associated with lower financing obstacles for people and businesses. A stable financial system that promotes efficient savings and investment is also crucial for a thriving democracy and market economy. There are several aspects of access to financial services: availability, cost, and quality of services. The development and growth of credit markets depend on access to timely, reliable, and accurate data on borrowers’ credit experiences. Access to credit can be improved by making it easy to create and enforce collateral agreements and by increasing information about potential borrowers’ creditworthiness. Lenders look at a borrower’s credit history and collateral. Where credit registries and effective collateral laws are absent – as in many developing countries – banks make fewer loans. Indicators that cover getting credit include the strength of legal rights index and the depth of credit information index.

General Comments: Country-specific metadata can be found on the IMF’s FAS website at  http://fas.imf.org.

2013 / በኢትዮጵያ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት

በኢትዮጵያ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት ደንበኞች ቁጥር መጨመር የዲጂታል ባንኪንግ ቴክኖሎጂ እውቀት በደንበኞች ዘንድ መስፋፋቱን አመላካች ነው፡፡ በኢትዮጵያ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት በኤቲኤም፣ በሞባይል፣ በኢንተርኔትና መሰል ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በመጠቀም ደንበኞች ወደ ቅርንጫፍ ባንኮች ሳይመጡ  የተለያዩ አገልግሎቶች ማግኘት ችለዋል፡፡ የባንክ ኢንዱስትሪው የዲጂታል ባንክ አገልግሎት እንዲስፋፋና የተጠቃሚዎች የደንበኛ ቁጥር ብዛት መጨመር አዲስ ምዕራፍ ከፍቶል፡፡ በዚህም የተነሳ የተጠቃሚዎች ቁጥር በማደጉም የሚንቀሳቀሰው የገንዘብ መጠን እየጨመረ ሄዶል፡፡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መረጃ መሠረት  የዲጂታል ባንክ አገልግሎት ደንበኞች የሚደረገው የገንዘብ እንቅስቃሴ ከፍተኛውን ደረጃ መያዙን አሃዙ ያስያል፡፡ በዓለማችን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሽታ መዛመት የተነሳ ወደ ቅርንጫፍ ባንክ ሠራተኞች ዘንድ ከመሄድ ደንበኞች ታቅበዋል፡፡ በኮቪድ መከሰት ምክንያት የዲጂታል ባንኪንግ አጠቃቀም በህብረተስብ ዘንድ ተጠናክሮ ቀጥሎል፡፡ በኢትዮጵያ ዲጂታል ቴክኖሎጂ እንዲስፋፋ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት  ማሽኖች ኤቲኤም፣ ሞባይል፣ በኢንተርኔት ወዘተ ኢንቨስትመንት ጠቀሜታ ከባንኮች ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ግንባታ አስር እጅ ይልቃል እንላለን፡፡ በኢትዮጵያ የዲጂታል ፋይናንስ ቴክኖሎጂ አገልግሎትና አጠቃቀም የባንኮች አፈፃፀም መረጃ መሠረት፡-

 • ‹‹በሚያዝያ 2012 ዓ/ም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ የተንቀሳቀሰ ገንዘብ 38(ሠላሳ ስምንት ) በመቶ ድርሻ የነበረው ሲሆን፣ ወደ ቅርንጫፍ በመምጣት ደንበኞች ማንቀሳቀስ የቻሉት የገንዘብ መጠን ደግሞ 62 (ስልሳ ሁለት) በመቶ ነበር፡፡
 • በሚያዝያ 2013 ዓ/ም የዘጠኝ ወራት ሪፖርት መሠረት፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ የተንቀሳቀሰ ገንዘብ 62 (ስልሣ ሁለት) በመቶው በጂጂታል ቴክኖሎጂ የተንቀሳቀሰ ሆኖል፡፡ ወደ ቅርንጫፍ በመምጣት የተንቀሳቀሰው ደግሞ 38 (ሠላሣ ስምንት) በመቶ በመሆኑ የታየው ለውጥ ከፍተኛ የሚባል መሆኑን ጠቁመው፣ ይህም ቅርንጫፍ በመቅረብ ገንዘብ ሲያንቀሳቅሱ የነበሩ ደንበኞች ወደ ዲጂታል አገልግሎት መግባታቸውን ያሳያል ብለዋል፡፡  ደንበኞች ማንቀሳቀስ የቻሉት የገንዘብ መጠን ደግሞ 62 በመቶ ነበር፡፡››

በ2013ዓ/ም የዚህ ገንዘብ እንቅስቃሴ መብዛት ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን የጠቀሱት አቶ አቤ፣ በዚህ አገልግሎት የሚጠቀሙ ደንበኞች ቁጥርም እያደገ መምጣቱን አክለዋል፡፡

 • የባንክ ቴክኖሎጂን ከማሳደጉና ከዲጂታል የባንክ አገልግሎት ዕድገት ጋር ተያይዞ ያሉ ወቅታዊ አሃዛዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የኤቲኤም ካርድ የሚጠቀሙ ደንበኞች ከስድስት ሚሊዮን በላይ መድረሳቸው አንዱ ነው፡፡
 • የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ደግሞ6 ሚሊዮን ስለመድረሱ የሚያመለክተው የባንኩ መረጃ፣ የዲጂታል ባንኪንግ ሌላው አገልግሎት የሆነው የኢንተርኔት ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር ደግሞ 30 ሺሕ መድረሱ ተገልጿል፡፡
 • ከሞባይል ባንኪንግ ጋር ተያያዥነት ባለው በሲቢኢ ብር (ዋሌት) ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር ወደ5 ሚሊዮን መድረስ መቻሉና በአብዛኛው ተጠቃሚዎችም ባለፉት አንድ ዓመታት አገልግሎቱን የተቀላቀሉ ናቸው፡፡
 • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ1666 በላይ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን፣ ለዘመናዊ የባንክ አገልግሎት የሚጠቀምባቸው የኤቲኤም ማሽኖቹን ቁጥር 3083 አድርሷል፡፡ የፖስ ማሽኖቹ ደግሞ 4386 መድረሱን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡ በባንኩ የሒሳብ ደብተር የከፈቱ ቆጣቢዎች ደግሞ ወደ 30 ሚሊዮን ደርሰዋል፡፡
 • የኤቲኤም ማሽኖች ውስጥ እስከ ሁለት መቶ ሽህ ዶላር አስተማማኝ ቦታ ላይ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ ሌሎች ቦታዎች አስር ሽህ ዶላር ሌብነትን ለመከላከል ትንሽ ገንዘብ ይቀመጣል፡፡ የኤቲኤም ማሽኖቹን ገንዘብ የሚሞሉት ባንኮች ናቸው፡፡ የግሉ ዘርፍ ከባንክ ኮሚሽን በእያንዳንዱ ግብይይት ወቅት ያገኛሉ፡፡
 • An ATMyoureceive a higher commission per surcharge transaction.
 • Who fills money in ATM machines? In general, ATMsat banks are refilled by the bank itself; however, there are different options of refilling the machine in case of standalone ATMs. So, if you have installed an ATM at your business location and wondering who’ll be refilling it with cash once it runs out of cash, we have got you covered.Apr 23, 2019
 • How much money is kept in an ATM? The average ATM can hold as much as $200,000, though few normally do. In off hours, most machines contain less than $10,000. Even so, big score ATM thefts have likely only made the crime more popular.
 • በአዲሱ የገበያ ጥናት መሠረት የኤቲኤም ማሽኖች በ2037 እኤአ ይጠፉና በአጠቃላይ ገንዘብ አልባ ህብረተሰብ ይመሠረታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ (Recent research from Expert Market foresees the complete disappearance of all ATMsby 2037, while bank branches, at this rate, have just over 22 years left. The idea that we’re on the road to a completely cashless society isn’t new, but it is accurate.Jan 29, 2019)……….(3)

 

ምንጭ፡

 

(1) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር መጨመሩን አስታውቋል/5 May 2021

(2) Countries ranked by Automated teller machines (ATMs) (per 100,000 adults) (indexmundi.com)

(3) ATMs machine – Google Search

 

Leave a Reply